in the future - u will be able to do some more stuff here,,,!! like pat catgirl- i mean um yeah... for now u can only see others's posts :c
___________ #ኦጋዴንና_ታንከኛው ___________
#ጄኔራል_ዋሲሁን_ንጋቱ
#The_Game_Changer
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ባለፈው ስለ #ካራማራው ድልና #የታንከኛው_ዕዛችን ካወራን በኋላ፤ የወቅቱ የታንከኛው ዕዛችን ዋና አዛዥ ስለነበሩት #ጄኔራል_ዋሲሁን_ንጋቱ አውርተን፤ የጄኔራሉን ኢንተርቪው እለቀዋለሁ ባልኩት መሰረት ብዙ ሰዎች በውስጥ መስመር ስትጠይቁኝ ከረማችሁ።
እነሆ #በሬድዮ ፕሮግራሜ #አፍሮቴይነር ላይ 41ኛውን የካራማራ ድል አስመልክቶ ያደረኩላቸውን ቃለ ምልልስ እንደዚህ ቀንጭቤ እንድትሰሙት አዘጋጅቻለሁና ከነሙዚቃው የ 12 ደቂቃ ቁምነገር ጋብዣችኋለሁ።
◈ፕሮግራም: #አፍሮቴይነር
◈ጣቢያ: ኤፍ ኤም አዲስ 97.1
◈አዘጋጅና አቅራቢ: አብይ ደምለው
ታሪካችንን እንወቅ! ጀግኖቻችንን እናክብር!
#አብይ_ደምለው
1 - 0
__________ #የሀገር_ፍቅር_ዘፈኖች __________
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ክፍል ፪
የ#አድዋና #ካራማራን አስመልክቶ በቀደመው #የደርግ ዘመን #በሠራዊቱ ልዩ ልዩ የሙዚቃ ክፍሎች፣ ሲቪል ባንዶችና ድምፃዊያን የተሰሩ የሙዚቃ ስራዎችን ለትውስታ ያህል እንድትሰሙ ራሴ ያዘጋጀሁትን እነሆ ጋበዝኳችሁ።
#አብይ_ደምለው
1 - 0
__________ #የሀገር_ፍቅር_ዘፈኖች __________
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ክፍል ፩
የ#አድዋና #ካራማራን አስመልክቶ በቀደመው #የደርግ ዘመን #በሠራዊቱ ልዩ ልዩ የሙዚቃ ክፍሎች፣ ሲቪል ባንዶችና ድምፃዊያን የተሰሩ የሙዚቃ ስራዎችን ለትውስታ ያህል እንድትሰሙ ራሴ ያዘጋጀሁትን እነሆ ጋበዝኳችሁ።
#አብይ_ደምለው
0 - 0
___________ #ሸረሃቢል_አህመድ ___________
#የኢትዮጵያ_ሬድዮ_አርማ
KING OF SUDANESE JAZZ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
አንዳንዴ በልጅነት የሰማናቸው ሙዚቃዎች በህሊናችን ተከትበው ለዘመናት በህሊናችን ጓዳ ውስጥ የራሳቸውን ጎጆ ቀልሰው የሚኖሩ አይጠፉም።
በተለይም የሙዚቃው ዘፋኝ፣ የዘፈኑ ርዕሰ (መጠሪያ) እና ሙሉ መረጃው ሳይኖረን ቀርተን ስንቶቹን እያሳደድን እንኖራለን።
ይህ ሙዚቃ ከተወዳጅነቱ ብዛት ከተለቀቀ ከ1965 ጀምሮ #የኢትዮጵያ_ሬድዮና #የለገዳዲ ሬድዮኖች መለያ እስከመሆን ደርሶ ነበር።
ለብዙዎቻችን በተለይም በወቅቱ ልጆች ለነበርነው፣ የሃገራችን ሙዚቃ እስኪመስለን አብረን አዚመነዋል። አነብንበነዋል።
ለነገሩ ሙዚቃው ከኛዎቹ የ1960ዎቹ አኩስቲክ (ከእነ #ግርማ_በየነ እና #ለማ_ደምሰው) አሬንጅመንቶች ጋር በእጅጉ ተቀራራቢ ስለሆነ የሃገራችን ሙዚቃ ቢመስለንም አይፈረድብንም።
ይባስ ብሎም #ተሾመ_ወልዴና #ዋቢ_አብዱረህማን ጭምር "አጂጉዳ" ብለው በጉራጊኛ ጭምር ሙዚቃውን ከልሰው ሰርተውታል።
እና እኔም እነሆ ለአመታት ሳስሰውና ስፈልገው ቆይቼ ለሱዳናዊው #የብሉ_ናይል_ባንድ አባል ጓደኛዬ መነሻውን ብልክለት ይኸው ከነ ሊንኩ ልኮልኝ አረፈው። የምር እንባዬ መጣ። #ኢትዮጵያ_ሬድዮና #የአረብኛው (External Service) ዝግጅት ክፍል ጆሮዬ ላይ መጥተው በትዝታ ወደኋላ ዘመትኩ።
ድምፃዊው የሱዳኑ ጃዝ ሙዚቃ ንጉስና የሱዳኑ #ካርሎስ_ሣንታና እስመባል የደረሰው አንጋፋው #ሸረሃቢል_አህመድ ሆኖ ተገኘ። #የሸረሃቢል ከ6 በላይ የሚሆኑ አልበሞቹ ያሉኝ ቢሆንም ይህንን ከእርሱ ስራዎች ጋር አዛምጄው አላውቅም ነበር።
#ኤል_ባምቢ የሙዚቃው ስያሜ ነው። ለጁምዓውም ሆነ ለዕለተ ገብርኤሉ ይህንን ስራ ብጋብዛችሁስ?
ግና የትውልዴ ሰዎች ትዝታችሁን ታወሩኛላች ብዬ እጠብቃለሁ። ስለ #ሸረሃቢል ግን በሰፊው እንመጣለን። በተለይም ኤርትራ ተሻግሮ ከበረከት መንግስተ_አብ ጋር ስለሰራቸው ስራዎች እናወጋለን።
#አብይ_ደምለው
1 - 0
#Afrotainer_Ethiopia & Afrotainer Media are #PanAfrican Multi_Media Companies working tirelessly for the betterment of the future of #Africa, through Media, Arts, Culture & Entertainment.
We strive for the creation of a brand new look-at of our continent through knowledge sharing, documentation & re-writing our own chapters inside the pages #African_History.
We enhance, introduce & promote African Creative products & industries through Mainstream & Social mediums with high quality Audio-Video Productions.
🚦PS: LIKE, SHARE & SUBSCRIBE Our channel for you will benefit more!
📌Follow Us On FB:
📌@Afrotainer Ethiopia
📌@Afrotainer Media
📌Mail: afrotainermedia@gmail.com
📌Telegram: @Afrotainer Ethiopia
📌What'sup: @Afrotainer Ethiopia
📌Web: www.afrotainerethiopia.com