Channel Avatar

አርያም ሚዲያ - Aryam Media @UCxNkKTpjI0Vt2bvwsU-EOsQ@youtube.com

129K subscribers - no pronouns :c

ውድ የአርያም ሚዲያ ቤተሰቦች እንኳን ወደዚህ መንፈሳዊ ቻናል መጡ፡፡ +++++++++++++++


Welcoem to posts!!

in the future - u will be able to do some more stuff here,,,!! like pat catgirl- i mean um yeah... for now u can only see others's posts :c

አርያም ሚዲያ - Aryam Media
Posted 1 month ago

ውድ የአርያም ሚዲያ ቤተሰቦች እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ፡፡

ይህንን የደስታ በዓል ምክኛት በማድረግ አዲስ መዝሙር ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡ ይህ የመጀመሪያ ሥራችን እንደመሆኑ ለሌሎች ሥራዎችም እንድንበረታ አስተያየታችሁን በመስጠት ላይክ እና ሼር በማድረግ ያግዙን ስንል እንጠይቃለን፡፡

https://youtu.be/d98R39hvkh4
https://youtu.be/d98R39hvkh4
https://youtu.be/d98R39hvkh4

መልካም በዓል

850 - 11

አርያም ሚዲያ - Aryam Media
Posted 1 month ago

ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሩፋኤል

ጳጉሜን ሦስት ቀን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከምታከብራቸው በዓላት አንዱ የሊቀ መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል በዓል ነው፤ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል በዚህች ዕለት ዓመታዊ ክብረ በዓሉ ይከበራል፡፡ በድርሳነ ቅዱስ ሩፋኤል እና በወርኃ ጳጉሜን ሦስት ቀን የሚነበበው ስንክሳርና የተጻፉት ድርሳናት እንዲህ ያስተምሩናል፤ አንዲት ክርስቲያን ሴት በቅዱስ ሩፋኤል ሰም በባሕር መካከል ባለች ደሴት ቤተ ክርስቲያን አሳነጸች፤ ሊቀ ጳጳሱ አባ ቴዎፍሎስ በዚህች ዕለት ቅዳሴ ቤቱን አከበረ፤ ከደሴቲቱ ሥር የነበረ ግዙፍ ዓሣአንበሪም ባሕሩን ባናወጠው ጊዜ በደሴቲቱ የታነጸቸውን ቤተ ክርስቲያኗን ሊያፈርስ ደረሰ፤ በውስጧም ለበዓል ተሰብስበው የነበሩ ምእመናን በጸሎት ወደ ቅዱስ ሩፋኤል ተማጸኑ፡፡

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤልም ከእግዚአብሔር ተልኮ መጣ፤ ሕዝቡን ታደገ፤ ከደሴቲቱ ሥር ያለውንም ግዙፍ ዓሣአንበሪው እንዳይንቀሳቀስ በጦር ወጋው፤ ‹‹እግዚአብሔር አዞሃልና ከቦታህ ሳትናወጽ ጸጥ ብለህ ቁም!›› አለው፤ ጸጥ ብሎም ቆመ፡፡ ሕዝቡም ከባሕሩ ከመስጠም፣ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኒቱም ከመፍረስ ተረፉ፤ ቅዱስ ሩፋኤል ይህን ድንቅ ተአምር አድርጎ፣ ከፈጣሪው አማልዶ፣ ለጠሩት ፈጥኖ የደረሰበትን ይህን በዓል ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዓመቱ መጨረሻ ባለችው ወርኃ ጳጉሜን በሦስተኛ ቀን በድምቀት ታከብሯለች፡፡ (ስንክሳር ዘወርኃ ጳጉሜን ሦስት ቀን)

በዚህች ዕለት ከሚከበሩ በዓላት ሌላኛው በመጽሐፍ ቅዱስ በመጽሐፈ ጦቢት እንደተጻፈው ቅዱስ ሩፋኤል በመልካም ምግባሩ፣ በምጽዋት ሥራው ለሚታወቀው ለጦቢት በችግሩ ጊዜ በሰው አምሳል ተገልጦ፣ እንደ ሠራተኛ ተቀጥሮ በማገልገለል ልጁ ጦቢያን ከዓሣአንባሪ ፣ ሣራ የተባለችን ሴት ያሠቃያት ከነበረው ርኩስ መንፈስ፣ ጦቢትን ከዓይን ሕመሙ የፈወሰበት የቅዱስ ሩፋኤል ተራዳኢነት፣ የጦቢት መልካም ምግባር፣ የእግዚአብሔር ቸርነት የተገለጠበት መታሰቢያም በዓል ነው፡፡ (መጽሐፈ ጦቢት አንድምታው መግቢያ) ይህች ዕለት ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል የተሾመበት መታሰቢያውም ነው፤ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ እኛንም በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ጸሎት ይጠብቀን፤ አሜን!!!

1.6K - 24

አርያም ሚዲያ - Aryam Media
Posted 2 months ago

#ቡሄ #ደብረታቦር #እንኳን_አደረሳችሁ
#ቡሄ ማለት ምን ማለት ነው ? #ችቦ ለምን እና መቼ ይበራል? #ሙልሙል ልምን ይታደላል? በቡሄ ወቅት #ጭራፍ ለምን ይጮሃል ?

#ቡሄ
ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡ ወቅቱ የክረምት ፤ጨለማ አልፎ የብርሃን የሚወጣበት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልም “ቡኮ/ሊጥ” ተቦክቶ ዳቦ የሚጋገርበት “#ሙልሙል” የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል፡፡
፨፨፨

#ጅራፍ
በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምስጢር፤ በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ምስጢራዊ ሞቱ ነው፡፡ ጅራፍ መገመድ(መጥለፍ) እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ዓይነት ምስጢር የያዘ ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡ የመጀመሪያው ግርፋቱንና ሞቱን እናስብበታለን፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ፤ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል፤ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡
የጅራፍ ትውፊታዊነት /ውርስ/፣ መጽሐፋዊ ትምህርትና ምስጢር ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ጨዋታውን በተራራማ አካባቢ፣ ከመኖሪያ ቤት ርቆና፣ በሜዳ ማድረጉ ጠቃሚ ነው፡፡ ጅራፍን #በርችት መቀየር የሚያመጣውን የምስጢር ተፋልሶ ብቻ መመልከት ከማኅበራዊ ጎጂ ገጽታው በላይ እንድናስወግደው ያስገድደናል፡፡
፨፨፨


#ችቦ
ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነው፡፡ በመሆኑም ችቦ ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን፡፡ የዚህ ትውፊታዊ አመጣጥ በብርሃኑ ድምቀት የቀኑን መምሸት ያልተረዱ እረኞች በሜዳ ቀርተዋልና ወላጆች ከመንደር ችቦ ለኩሰው ልጆቻቸውን ፍለጋ ሔደዋልና ታሪኩን እያዘከርን በዓሉት እናከብራለን፡፡ የችቦው መንደድም ሌላ ትርጉም አለው፡፡ አንድ ምእመን ለሌላው ምእመን መካሪ አስተማሪ መሆኑን፣ መከራ እየተቀበለም አርአያ፣ ምሳሌ፣ ብርሃን መሆኑን ያሳያል፡፡ በሃይማኖትም አርአያ ምሳሌ ይሆንላቸዋል፡፡ ከዚህ ጋርም ተያይዘዞ ችቦ #በ13 ምሽት ይበራል ፣ብርሃኑ የተገለጠው በዚችው ዕለት ነውና ፡፡
፨፨፨

#ሙልሙል
በችቦ ብርሃን ልጆቻቸውን ፍለጋ የወጡ ወላጆች ዳቦ ጋግረው ይዘውላቸው ወጥተዋል፡፡ ስጦታው ቤተሰባዊነትን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን መግለጫ ነው፡፡ ወደ ቤታችን “ ቡሄ ” እያሉ ለሚመጡ አዳጊዎችም፤ ዘምረው እንዳበቁ የሚሰጥ “ሙልሙል” ዳቦ አለ፡፡ ሕፃናቱም ሊዘምሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ አይደለም፡፡ ሕፃናቱ
የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት “የምሥራች” ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋርያት በገቡበት አገር አስተምረው አጥምቀው የጸጋ ልጅነትን አሰጥተው በረከት አድለው እንደሚሔዱም፣ ልጆችም ዘምረው፣ አመስግነው፣ መርቀው “ውለዱ ክበዱ፣ ሀብት አግኙ፣ የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ
….” ይላሉ፡፡
በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከእነዚህ ምስክር ካላቸው ትምህርቶቹ፣ ምሥጢር ከሚራቀቅባቸው ትርጓሜያቱና ከትውልድ ትውልድ በቅብብል በተላለፈው ቅዱስ ትውፊት ጋር ሃይማኖታዊ ባሕል ሆኖ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡ ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን አዳጊዎች ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ይዘው እንዲያድጉ ጥቆማ በመስጠት፣ ግጥም በመግጠምና
ምሥጢሩን በማብራራት የመጀመሪያዎቹ ባለድርሻዎች ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ፣ ፌዝና ሥላቅ የተቀላቀለባቸው ይሆናሉ፡፡ ሕፃናቱም ዝማሬውን ሲጀምሩ “ከሰጡን እንነሣ ከነሱን እናርዳ” ብለው ይጀምሩታል፡፡ ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን በማለት፡፡ አሳሳቢው ነገር ደግሞ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛነት የቀየሩ ሁኔታዎች መታየታቸው ነው፡፡

ዳቦ /ሙልሙል/ ትምህርቱንም፣ ምስጢሩንም፣ ትውፊቱንም በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል ከዚም ጋር ተያይዞ ሰንበት ት/ት ቤታችን ለበረካታ ዓመታት ሰወረድ የመጣውን የዝማሬ ሥርዓት ለአጥብያው ምእምን በየቤቱ በመሄድ የብሄን ዝማሬ ከነሥርዓቱ በመዘመር አገልግሎት ይሰጣል ፤የደብር ታቦርን በዓል በተመለከትም የወረቀት ጽሑፎችን ይበትናል በዝማሬ መኃል ያድላል ፡፡
ቤተክርስቲያን የምሥጢር ግምጃ ቤት ናት፤ የምታከናውነውን ሁሉ ከበቂ መረጃ ጋር ነው ተግባራዊ የምታደርገው፡፡

1.7K - 27

አርያም ሚዲያ - Aryam Media
Posted 2 months ago

🙏🙏🙏 ከመጀመሪያው ሰብስክራይበር ጀምሮ እዚህ እስከምንደርስ ድረስ አብራችሁን የነበራችሁ የቀድሞዋ ''ተዋሕዶ 23'' የአሁኗ ''አርያም ሚዲያ'' እዚህ እንድትደርስ ላደረጋችሁልን ሁሉ እግዚአብሔር አምላክ ያክብርልን:: ከዚህም በዝተን 1,000,000 እንደምንገባ ተስፋ እናደርጋለን :: 🙏🙏🙏

731 - 17

አርያም ሚዲያ - Aryam Media
Posted 5 months ago

ዓርብ ስቅለት (የድኅነት ቀን)

ሊቀ ማእምራን ብርሃነ መስቀል አጠና 

ዓርብ ስቅለት የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ስለኾነ ‹የድኅነት ቀን› ይባላል፡፡

ጌታችን ሲሰቅልም የሚከተሉት ሰባት ተአምራት ተፈጽመዋል፤

፩. ፀሐይ ጨለመ፤

፪. ጨረቃ ደም ኾነ፤

፫. ከዋክብት ረገፉ፤

፬. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ተቀደደ፤

፭. አለቶች ተፈረካከሱ፤

፮. መቃብራት ተከፈቱ፤

፯. ሙታን ተነሡ (ማቴ. ፳፯፥፶፩-፶፬)፡፡

ጌታችን በመስቀል ላይ ሳለ የሚከተሉትን ሰባት ዐበይት ቃላት አሰምቶ ተናግሯል፤

፩. ‹‹ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ (አምላኪየ አምላኪየ ለምን ተውኸኝ?)››፤

፪. ‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትኖራለህ››፤

፫. ‹‹አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁትምና ይቅር በላቸው››፤

፬.እመቤታችንን ‹‹ሴትዮ ሆይ፣ እነሆ ልጅሽ››፤ ደቀ መዝሙሩንም‹‹እናትህ እነኋት›› በማለት የቃል ኪዳን እናትነትና ልጅነት ማከናወኑ፤

፭. ‹‹አባት ሆይ በአንተ እጅ ነፍሴን አደራ እሰጣለሁ››

፮. ‹‹ተጠማሁ››፤

፯. ‹‹ዅሉ ተፈጸመ›› (ማቴ. ፳፯፥፵፭-፵፮፤ ሉቃ. ፳፫፥፵፫-፵፮፤ ዮሐ. ፲፱፥፲-፴)፡፡

ከስድስት ሰዓት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ጨለማ ኾኖ ከቈየ በኋላ ከዘጠኝ እስከ ማታ እንደ ተለመደው ብርሃን ኾኖአል፡፡ ‹‹ወፍና ሠርክ ይበርህ ብርሃነ ፀሐይ›› እንዲል (ዘካ. ፲፬፥፯)፡፡ በዚህ ዕለት ሰባት መስተፃርራን (ጠበኞች) ታረቁ፤ ተስማሙ፡፡ እነዚህም፡- ሰውና እግዚአብሔር፣ ሰውና መላእክት፣ ሕዝብና አሕዛብ፣ ነፍስና ሥጋ ናቸው (ኤፌ. ፪፥፲፤ ቈላ. ፩፥፳)፡፡ ጌታችን ጠዋት በሦስት ሰዓት ተገረፈ፤ በስድስት ሰዓት ተሰቀለ (ማቴ. ፳፯፥፩-፴፯፤ ሉቃ. ፳፫፥፩-፵፬፤ ዮሐ. ፲፱፥፩)፡፡

በዘጠኝ ሰዓት ጌታችን በውኃው ተጠምቀን፣ ደሙን ተቀብለን የእግዚአብሔር ልጆች እንኾን ዘንድ ከቀኝ ጎድኑ ጥሩ ውኃ፣ ትኩስ ደም አፈሰሰልን (ዮሐ. ፲፱፥፴፬)፡፡ በዐሥራ አንድ ሰዓት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከመስቀል አውርደው ሽቶ እየረበረቡ በድርብ በፍታ ገንዘው ቀበሩት (ሉቃ. ፳፫፥፶-፶፬፤ ዮሐ. ፲፱፥፴፰-፵፪)፡፡ ቅድስት ነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዳ ነፍሳትን ነጻ አወጣች (፩ኛ ጴጥ. ፫፥፲፱)፡፡ በዚህ ጊዜ በርሃነ መለኮቱ በሲኦል ተገለጠ፡፡ ስለዚህም ‹‹ንሴብሖ ለእግዚአብሔር›› እየተባለ ይዘመራል፡፡ ከሆሣዕና አንሥቶ ተከልክሎ የነበረው ኑዛዜ ይናዘዛል፤ ጸሎተ ፍትሐት ይደረጋል

802 - 7

አርያም ሚዲያ - Aryam Media
Posted 5 months ago

#ሕማማት_ማግሰኞ
በዚህ ዕለት ጌታችን በቤተ መቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረ ዕለቱ ‹የትምህርት ቀን› ይባላል፡፡ ክርስቲያን የኾነ ዅሉ ከሥጋዊ ነገር ርቆ በዚህ ሰሞን የሃይማኖት ትምህርት ሲማር፣ ሲጠይቅ መሰንበቱ መጽሐፋዊ ሥርዓት ነው፡፡

በዚህ ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሥልጣኑ ተጠይቋል፡፡ ጠያቂዎቹ የካህናት አለቆችና የሕዝብ አለቆች ሲኾኑ፣ ጥያቄውም፡- ‹‹በማን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን የሰጠህ ማነው?›› የሚል ነበር፡፡ ይህ ጥያቄ ጌታችን ሰኞ ዕለት ሁለት ነገሮችን ማከናወኑን ተከትሎ የተነሣ ጥያቄ ነው፡፡ ይኸውም ጌታችን ሲያደርጋቸው የነበሩ ተአምራትና ድንቅ ድንቅ ሥራዎች የካህናት አለቆችን ስላስቀኗቸው ጌታችንን ከሮማ መንግሥት ባለ ሥልጣናት ጋር ለማጋጨት የቀየሱት ስልት ነው፡፡ ጌታችን በቤተ መቅደስ የነበሩትን ነጋዴዎችን አባሯል፤ መደባቸውን ገለባብጧል፡፡ ነጋዴን ማባረርና መደብን ማስለቀቅ መንግሥታዊ ሥራ ነው፡፡ ጌታችን ‹‹በራሴ ሥልጣን›› ቢላቸው ፀረ መንግሥት አቋም አለው በማለት ከሮማ መንግሥት ዘንድ ለማሳጣት ነበር ዕቅዳቸው፡፡

ጌታችን ግን የፈሪሳውያንን ጠማማ አሳብ ስለሚያውቅ ‹‹የዮሐንስ ጥምቀት ከየት ነው? ከሰማይ ነው ወይስ ከምድር?›› ሲል ጠይቋቸዋል፡፡ ጌታችን ፈሪሳውያን ላቀረቡለት ጥያቄ ቀጥተኛ ምላሽ አልሰጠም፡፡ ምክንያቱም ጥያቄው ለከሳሾቹ ዓላማ መሳካት አመቺ ኹኔታን ስለሚፈጥር ጥያቄውን በጥያቄ መልሶላቸዋል፡፡ እነርሱም ‹‹ከሰማይ ነው›› ቢሉት ‹‹ለምን አላመናችሁበትም?›› እንዳይላቸው፤ ‹‹ከሰው ነው›› ቢሉት ደግሞ ሕዝቡ ዮሐንስን እንደ አባት ይፈሩት፣ እንደ መምህር ያከብሩት ነበርና ሕዝቡ እንዳይጣሏቸው ስለፈሩ ‹‹ከወዴት እንደ ኾነ አናውቅም›› ብለው መለሱለት፡፡ እርሱም ‹‹እኔም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ አልነግራችሁም›› አላቸው፡፡ ይህን ጥያቄ መጠየቃቸውም እርሱ የሚያደርጋቸውን ተግባራት ዅሉ በራሱ ሥልጣን እንዲያደርግ አጥተውት አልነበረም፤ ልቡናቸው በክፋትና በጥርጥር ስለተሞላ ነበር እንጂ፡፡

ዛሬም ቢኾን መልካም ሥራን በሠራን ጊዜ ከልዩ ልዩ ወገኖች የሚመጡ ፈተናዎች ለመልካም ሥራችን እንቅፋት ሊኾኑ እንደሚችሉ መገንዘብ አለብን፡፡ ብዙ ወገኖች ‹‹ለቅን አሳባችን ለምን ሰዎች ክፉ ነገር ይመልሱልናል?›› በማለት ሲጠይቁ ይሰማል፡፡ ለቅን አሳባችን ከዓለም ዘንድ ተቃራኒ ነገር እንደሚጠብቀን ለመረዳት ‹‹ዓለም የሚወደው የገዛ ወገኑን ነው›› የሚለውን የጌታችንን ትምህርት ልብ ይሏል፡፡ በዘመናችን አሳልፈው ሊሰጡን የሚፈልጉ ሰዎች ፈታኝ ጥያቄ እንደሚያቀርቡልንም ከወዲሁ ልንገነዘብ ይገባል፡፡

1.1K - 25

አርያም ሚዲያ - Aryam Media
Posted 6 months ago

✝✝✝ እንኳን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ *" በዓለ ዑደተ ሆሳዕና "* በሰላም አደረሳችሁ ✝✝✝

+*"+ በዓለ ሆሳዕና +"*+

=>ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከሆሳዕና ጀምሮ እስከ ዸራቅሊጦስ ድረስ ያሉ ዐበይት በዓላትን ሁለት ጊዜ ታከብራለች:: በዚህም መሠረት:-

1ኛው="ጥንተ በዓል" ሲሆን {"ጥንተ በዓል" ማለት በዓሉ : ተአምሩ (የማዳን ሥራው) የተፈፀመበት የመጀመሪያው ቀን ማለት ነው::}

2ኛው=ደግሞ "የቀመር በዓል" ይሠኛል::
መሠረቱ የቅዱሳን ሐዋርያት ቀኖና እና የአባታችን የድሜጥሮስ መንፈሳዊ ቀመር ነው::

+ስለሆነም ዓለም ከተፈጠረ በ5,534 ዓመት : የዛሬ 1,978 ዓመት : በዛሬዋ ዕለት (ዕለተ እሑድ) ስም አጠራሩ ከፍ ከፍ ይበልና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፍጹም ትሕትና በአህያዋና በውርንጫዋ ጀርባ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም (ቤተ መቅደስ) ገብቷል::

+ታላቅ የምስጋና መስዋዕትም ከመላዕክት : ከሐዋርያት : ከሕጻናት : ከአረጋውያን : ከፀሐይ : ከጨረቃ : ከከዋክብት : ከቢታንያ ድንጋዮች . . . በአጠቃላይ ከፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ቀርቦለታል:: ጌትነቱንም በገሃድ ገልጧል::

=>ከበዓሉ በረከት ይክፈለን:: እኛንም ለጣዕመ ምስጋናው የተዘጋጀን ያድርገን::

=>+"+ አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበልሽ:: አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በዪ:: እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው:: ትሑትም ሆኖ በአህያም: በአህያይቱ ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል:: +"+ (ዘካ. 9:9)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

1.5K - 15

አርያም ሚዲያ - Aryam Media
Posted 8 months ago

“ወንበሩ ላይ አስቀምጦ ምን ይመክሩናል አለኝ። ሰው ሁኑ አልሁት።”
#ብጹዕ_አቡነ_ጴጥሮስ (ዶ/ር) #የቅዱስ_ሲኖዶስ_ዋና_ጸሐፊ

#እውነት ነው አውሬና እንስሳ አፍ አውጥቶ ምክር ከጠየቀ ሰው ሁኑ ማለት ነው።

351 - 4

አርያም ሚዲያ - Aryam Media
Posted 8 months ago

ቅዱስ ዑራኤል በያለንበት ይጠብቀን

760 - 9