Channel Avatar

Chernet Senai Media / ቸርነት ሰናይ ሚዲያ @UCvfxFdhb_mRaQ3IrHeXgOvA@youtube.com

125K subscribers - no pronouns :c

Chernet Senai is a gospel singer from the Ethiopian Orthodox


Welcoem to posts!!

in the future - u will be able to do some more stuff here,,,!! like pat catgirl- i mean um yeah... for now u can only see others's posts :c

Chernet Senai Media / ቸርነት ሰናይ ሚዲያ
Posted 4 days ago

ለሶስት ቀናቶች የሚቆይ የ 100 ብር ቻሌንጅ በወላይታ ላለችው ለገጠሪቱ ቤተክርስቲያን!
++++++++++++++++++++++++++++++++
አሳዛኝ ክስተት
መስከረም 2 ቀን 2017 ዓ/ም ታቦተ ህጉ አልከበረም

ሞጊሳ አርቤ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን።

በወላይታ ሀገረ ስብከት በኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ በሞገሳ አርቤ ቀበሌ ለ12 ዓመት ቤተክርስቲያን መሥሪያ ቦታ አጥተው ከአንድ ግለሰብ በተሰጠ 250 ካሬ ሜትር የወደፊቱን ተስፋ በማድረግ የተተከለው የገባሬ መንክራት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ከዓውደ ምሕረቱ ውጪ ያለው ይዞታ የግለሰብ በመሆኑ የተገመተው ብር 350,0000 በወቅቱ ባለመከፈሉና በመዘግየቱ ሰኔ 30 በብዙ ድካምና መግባባት እስከ መስከረም ድረስ ለመክፈል ቃል የተከበረ ቢሆንም ባለመከፈሉ ግለሰቡ ለመንግስት አመልክቶ በማሳገዱ ምክንያት የቅዱስ ዮሐንስ ንግሠ በዓል በሐዘንና በለቅሶ ሳይከበር ቀርቷል።
ስለዚህ ኦርቶዶክሳዊያን የቅዱስ ዮሐንስ ልጆች ወዴት አላችሁ ሁላችንም 100 ብር በማዋጣት እያዘኑ ያሉ ጥቂት ምዕመናንን ተስፋ እንሆናቸው ዘንድ በመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ስም እማጸናችኃለሁ።
ንግድ ባንክ- 1000376526821
ሞጊሳ አርቤ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን።
ስልክ-0916841205
Zelle-2022461636
ሟር..................

561 - 11

Chernet Senai Media / ቸርነት ሰናይ ሚዲያ
Posted 1 week ago

እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ አሸጋገረን!
(ትንቢተ ዳንኤል ምዕ. 2)
----------
20፤ ዳንኤልም ተናገረ እንዲህም አለ። ጥበብና ኃይል ለእርሱ ነውና የእግዚአብሔር ስም ከዘላለም እስከ ዘላለም ይባረክ፤

21፤ ጊዜያትንና ዘመናትን ይለውጣል፤ ነገሥታትን ያፈልሳል፥ ነገሥታትንም ያስነሣል፤ ጥበብን ለጠቢባን እውቀትንም ለአስተዋዮች ይሰጣል።

22፤ የጠለቀውንና የተሠወረውን ይገልጣል፤ በጨለማ ያለውን ያውቃል፥ ብርሃንም ከእርሱ ጋር ነው።

23፤ ጥበብንና ኃይልን የሰጠኸኝ፥ እኛም የለመንንህን ነገር አሁን ያስታወቅኸኝ፥ አንተ የአባቶቼ አምላክ ሆይ፥ የንጉሡን ነገር አስታውቀኸኛልና እገዛልሃለሁ አመሰግንህማለሁ።

889 - 9

Chernet Senai Media / ቸርነት ሰናይ ሚዲያ
Posted 2 weeks ago

የጭንቀታችን መፍትሄ በመምህር ምሕረተአብ አሰፋ ግሩም ትምህርት!
https://youtu.be/YTinw5FGQ4c?si=hvmPz...

48 - 0

Chernet Senai Media / ቸርነት ሰናይ ሚዲያ
Posted 3 weeks ago

ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሐገራችንን ኢትዮጵያን በምልጃው በቃልኪዳኑ ይጠብቅልን!

ፈጥነህ ቅረበን ጊዮርጊስ
ለአምላክህ የታመንክ እስከሞት
አክሊልን አገኘህ ፍጡነ ረድኤት
መዝሙሩን ለማድመጥ ሊንኩን ይጫኑ
https://youtu.be/OIh8NKjpG9E
https://youtu.be/OIh8NKjpG9E
https://youtu.be/OIh8NKjpG9E
Subscribe Our Channel and stay updated! 🔔
ቻናላችንን ሰብስክራይብ ላይክ ኮሜንት ሼር በማድረግ በየቀኑ አዳዲስ መንፈሳዊ ዝማሬዎችን ይከታተሉ!

555 - 8

Chernet Senai Media / ቸርነት ሰናይ ሚዲያ
Posted 3 weeks ago

በአትላንታ መካነ ሰላም ቅዱሰ ሚካኤል ወቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ⛪ አይቀርም!

630 - 0

Chernet Senai Media / ቸርነት ሰናይ ሚዲያ
Posted 3 weeks ago

ተወዳጁና ታዛዥ ወንድማችን እኔን ጨምሮ ለብዙ ዘማርያን መዝሙሮቻችን በክራር በማሳመር እንዲሁም ዜማ በመስራት የሚታወቀው ወንድማችን አንተነህ ተ/ማርያም(አንትዬ) አሁን ደግሞ ጥዑም የሆኑ ዝማሬዎችን በመንፈሳዊ ዕቃዎች በማቀነባበር በራሱ ቲዩብ መቶልናል ሁላችንም የተዋህዶ ልጆች ሰብስክራይብ በማድረግ እናበረታታው! https://youtu.be/_G8AuRCNkQM?si=2IUnB...
ሰብክራይብ ሼር.............

67 - 0

Chernet Senai Media / ቸርነት ሰናይ ሚዲያ
Posted 4 weeks ago

እንኳን አደረሳችሁ
እናታችን ቅድስት ኪዳነምሕረት ሁላችንንም በያለንበት በምልጃዋ በቃልኪዳኗ ትጠብቀን።

"ይኸው ዘምራለሁ"
https://youtu.be/RDl4e2BufAI
"ስለረዳሽኝ እመቤቴ"
https://youtu.be/RjqKbJ4Ej84
"ሰባቱ የእሳት መጋረጃዎቹ"
https://youtu.be/iCuRJ_W73qs
"ክብርት ነሽ"
https://youtu.be/kklDFU-jAcI
"ነይ ነይ ሱላማጢስ"
https://youtu.be/MUOe5m4x4iA
"እመቤቴ ምርኩዜ ረዳቴ"
https://youtu.be/gYFZiG6tsNk
"ብሶቴን ላንቺ እንግራለሁና"
https://youtu.be/bALJWIN8A7I
"ማርያም እጣን ናት"
https://youtu.be/Uy0M89DeIh8
"ከተለዩ የተለየሽ"
https://youtu.be/cJg9aFGRfgw
ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
ሼር...ሼር...ሼር.............ያድርጉ

29 - 0

Chernet Senai Media / ቸርነት ሰናይ ሚዲያ
Posted 4 weeks ago

ቡሄ_በሉ

ቡሄ በሉ (፪) - - ሆ ልጆች ሁሉ - - ሆ
የኛማ ጌታ - - ሆ የዓለም ፈጣሪ - - ሆ
የሰላም አምላክ - -ሆ ትሁት መሀሪ -ሆ
በደብረ ታቦር - - ሆ የተገለጠው - ሆ
ፊቱ እንደ ፀሐይ - ሆ በርቶ የታየው -ሆ
ልብሱ እንደብርሃን -ሆ ያንፀባረቀው -ሆ

ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና(፪)
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን(፪)

ያዕቆብ ዮሐንስ-ሆ እንዲሁም ጴጥሮስ-ሆ
አምላክን አዩት - - ሆ ሙሴ ኤልያስ - ሆ
አባቱም አለ - - ሆ ልጄን ስሙት - - ሆ
ቃሌ ነውና - - ሆ የወለድኩት - - ሆ
አዝ======
ታቦር አርሞንኤም-ሆ ብርሃን ታየባቸው ሆ
ከቅዱስ ተራራ ሆ ስምህ ደስ አላቸው- ሆ
ሰላም ሰላም - - ሆ የታቦር ተራራ - - ሆ
ብርሀነ መለኮት - ሆ ባንቺ ላይ አበራ -ሆ
አዝ======
በተዋህዶ - - ሆ ወልድ የከበረው - ሆ
የእግዚአብሔር አብ ልጅ - - ሆ ወልደማርያም ነው - -ሆ
ቡሄ በሉ - - ሆ ቡሄ በሉ - - ሆ
የአዳም ልጆች - - ሆ ብርሃንን - - ሆ ተቀበሉ - -ሆ
አዝ======
አባቴ ቤት - - ሆ አለኝ ለከት - - ሆ
እናቴ ቤት - - ሆ አለኝ ለከት - - ሆ
ከአጎቴም ቤት - - - ሆ አለኝ ለከት - ሆ
ተከምሯል - - ሆ እንደ ኩበት - - ሆ
አዝ======
የዓመት ልምዳችን - - ሆ ከጥንት የመጣው - - ሆ
ከተከመረው - ሆ ከመሶቡ ይውጣ - ሆ
ከደብረ ታቦር - - ሆ ጌታ ሰለመጣ - ሆ
የተጋገረው - ሆ ሙልሙሉ ይምጣ - ሆ
አዝ======
ኢትዮጵያውያን - -ሆ ታሪክ ያላችሁ - ሆ
ባህላችሁን - ሆ ያዙ አጥብቃችሁ - ሆ
ችቦውን አብሩት -ሆ እንዳባቶቻችሁ -ሆ
ምስጢር ስላለው -ሆ ደስ ይበላችሁ -ሆ
አዝ======
አባቶቻችን - - ሆ ያወረሱን - - ሆ
የቡሄን ትርጉም - - ሆ ያሳወቁን - - ሆ
እንድንጠብቀው - ሆ ለእኛ የሰጡን - ሆ
ይህን ነውና - - ሆ ያስረከቡን - - ሆ
አዝ======
ለድንግል ማርያም ሆ አሥራት የሆንሽ ሆ
ቅዱሳን ጻድቃን - - ሆ የሞሉብሽ - - ሆ
በረከታቸው - - ሆ ያደረብሽ - - ሆ
ሁሌም እንግዶች - ሆ የሚያርፉብሽ -ሆ
ሀገረ እግዚአብሔር -ሆ ኢትዮጵያ ነሽ ሆ
አዝ======
ለሐዋርያት - - ሆ የላከ መንፈስ - - ሆ
ዛሬም ለኢትዮጵያ -ሆ ጸጋውን ያፍስስ ሆ
በበጎ ምግባር - ሆ እንድንታነጽ - - ሆ
በቅን ልቦና - ሆ በጥሩ መንፈስ - - ሆ
በረከተ ቡሄ - ሆ ለሁላችን ይድረስ - ሆ
= = = = = =
ዓመት ዓውዳመት ድገም እና ዓመት ድገም እና
በጋሽዬ ቤ ድገም እና ዓመት ድገም እና
ያውርድ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ወርቅ ይፍሰስበት ድገም እና ዓመት ድገም እና
በእማምዬ ቤት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ይግባ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ማርና ወተት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ይትረፍረፍ በእውነት ድገም እና ዓመት ድገም እና
= = = = = =

እንዲሁ እንዳላችሁ - -በፍቅር አይለያችሁ - - በፍቅር
ላመቱ በሰላም - - በፍቅር ያድርሳችሁ - - በፍቅር
ክርስቶስ በቀኙ - - በፍቅር ያቁማችሁ - - በፍቅር
የመንግስቱ ወራሽ - - በፍቅር ያድርጋችሁ - - በፍቅር
እንዲሁ እንዳለን - - በፍቅር አይለየን - - በፍቅር
ለዓመቱ በሰላም - - በፍቅር ያድርሰን - - በፍቅር
አማኑኤል በቀኙ - - በፍቅር ያቁመን - - በፍቅር
የመንግስቱ ወራሽ - - በፍቅር ያድርገን - - በፍቅር
= = = = = =

የቅዱሳን መላክት የፃድቃን ሰማዕታት
ረድኤት በረከት ይግባ በሁሉም ቤት
በሁሉም ቤት(፪) ይግባ በረከት(፪)
እንቁም በሃይማኖት ፀንተን በትጋት
የአስራት አገር የአበው ቀደምት
የቅዱሳን አባቶች ትውፊት
ይገባልና ልንጠብቅ በእውነት
ባህላችንን የአባቶች ትውፊት (፫)

474 - 0

Chernet Senai Media / ቸርነት ሰናይ ሚዲያ
Posted 1 month ago

በአትላንታ መካነ ሰላም ቅዱሰ ሚካኤል ወቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ⛪ አይቀርም!

655 - 2

Chernet Senai Media / ቸርነት ሰናይ ሚዲያ
Posted 1 month ago

[ደብረ ታቦር]
♥❖ ይኽ በዓል ከጌታችን 9ኙ ዐበይት በዓላት አንደኛው ሲኾን በዓሉ በየዓመቱ ነሐሴ 13 ላይ በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡ ታሪኩ በ3ቱ ወንጌላት ላይ የተጻፈ ሲኾን ጌታችን አምላችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሌሎቹን ሐዋርያትን ከእግረ ደብር (ከተራራው ሥር) ትቶ የምስጢር ደቀ መዛሙርት የሚባሉት፣ በእምነት በተስፋ በፍቅር የሚመሰሉት፤ ዳግመኛ በነገደ ሴም በነገደ ካም በነገደ ያፌት የተመሰሉት ሦስቱን (ጴጥሮን፣ ያዕቆብን፣ ዮሐንስን) ይዟቸው ወደ ታቦር ተራራ ወጣ።

💥 የሞተውን ሙሴን ከ1644 ዓመታት በኋላ አምጥቶ፤ የተሰወረውን ኤልያስንም ከብሔረ ሕያዋን አምጥቶ የሕያዋን አምላክና የሙታን አሥነሺያቸው ርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ መኾኑን የገለጸበት ታላቅ ምስጢር የተከናወነበት ነው፡፡ (ማቴ 17፡1-9)።

♥❖ ጌታ 8ቱን ሐዋርያት ይዟቸው ያልወጣበት በይሁዳ ምክንያት ነው ምክያቱም ከምስጢረ መንግሥቱ ቢለየኝ ከሞቱ ገባኹበት ባለ ነበርና ነው፤ ነገር ግን በተራራው ላይ ለ3ቱ የተገለጸው ምስጢር ከተራራው ሥር ላሉት ከይሁዳ በስተቀር ተገልጾላቸዋል፤ ለእኛም እንደ ሐዋርያት ምስጢሩን ጥበቡን ይግለጽልን፡፡

♥❖ ብዙ ተራሮች ሳሉ የታቦር ተራራን የመረጠበት
1)አስቀድሞ የጌትነት ክብሩ በዚያ ተራራ ላይ እንደሚገልጽ ነቢዩ ዳዊት በመዝ 88፡12 ላይ፦ “ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚኣከ ይትፌሥሑ” (ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ይደሰታሉ) በማለት ጌታ በዚያ ተራራ ላይ ብርሃኑን ሲገልጽ የብርሃኑ ነጸብራቅ እስከ አርሞንኤም ተራራ ድረስ እንደሚታይ የተናገረውን ትንቢት ለመፈጸም ነው፡፡

♥❖ ሌላው ታቦር በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ 12 ጊዜያት ሲጠቀስ በተለይ በመሳ 4 እና 5 ላይ እንደተጻፈው አስቀድሞ በብሉይ ኪዳን የእስራኤል ጠላት የነበረው ሲሳራን መስፍኑ ባርቅ በተራራው ላይ ድል ነሥቶበት ነቢይቱ ዲቦራም በተራራው ላይ በደስታ አመስግናበታለች ዘምራበታለች። በተመሳሳይ መልኩ የእስራኤል ዘነፍስ የክርስቲያኖችን ጠላት የኾነውን ዲያብሎስን የኹላችን ፈጣሪ ንጉሠ ነገሥት ኢየሱስ ክርስቶስ በተራራው ላይ አምላክነቱን ገልጦ ድል ስለነሣው ነቢያት ሐዋርያት ምእመናን የሚያመሰግኑት ስለኾነ ለምሳሌነቱ ተስማሚነት ያለውን የታቦርን ተራራን መርጦታል፡፡

❤ በሲና ተራራ የአባቱን ክብር እንዳየን የርሱን ክብር ደግሞ በብሩህ ደመና በታቦር ገልጦታል።

♥❖ ለምን ሙሴንና ኤልያስን ከነቢያት መኻከል መረጠ? ቢሉ፦
ሀ) በማቴ 16፡13 ላይ ሐዋርያትን ስለማንነቱ እንደጠያቃቸው እንደመለሱለት ኹሉ በእውነት ጌታችን የሙሴና የኤልያስ በአጠቃላይ የነቢያት ፈጣሪ የእግዚአብሔር ልጅ መኾኑን ሲገልጽላቸው ነው።

ለ) በዘፀ 33፡17-23 ላይ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ካለው ጥልቅ ግንኙነት የተነሣ “እባክኽ ክብርኽን አሳየኝ” ብሎ ልመናን አቀረበ፤ እግዚአብሔርም "ወአነብረከ ውስተ ስቊረተ ኰኲሕ ወእከድን እዴየ በላዕሌከ እስከ አኃልፍ" (በሰንጣቃው ዐለት አኖርሃለኍ፤ እስካልፍ ድረስ እጄን በላይኽ እጋርዳለኍ፤ ካለፍኍ በኋላ እጄን አንሥቼልኽ ጀርባዬን ታያለኽ፤ ፊቴ ግን አይታይም) ብሎታል (ዘፀ ፴፫፥፲፯-፳፫)፡፡

♥❖ ይኸውም ጀርባ በስተኋላ እንደሚገኝ ኹሉ በኋላ ዘመን አካላዊ ቃል ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ በታቦር ተራራ ላይ እንደሚገለጽለት ሲያመለክተው ነው።

♥❖ ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብም ስለ ታቦር በሚተነትነው መጽሐፉ ሙሴ በቃዴስ ባለው በመሪባ ውሃ ከእስራኤል ጋር በበደለው በደል ምክንያት ምድረ ርስት ኢየሩሳሌም እንዳይገባ አይቷት ብቻ በናባው ተራራ ላይ እንዲያርፍ ኾኗል (ዘፀ ፴፪፥፶፪፤ ዘፀ ፴፬፥፩-፰)፡፡

♥❖ ይኽ ለሙሴ አሳዛኝ ቢኾንም በኋላ ዘመን አካላዊ ቃል ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ሙሴ በፊት በሩቁ ያያት ግን ያልገባባት በምድረ ርስት በኢየሩሳሌም ያለች ታቦር ተራራ ላይ አምጥቶት በዘመነ ብሉይ በአካለ ሥጋ ያልገባባትን ርስት እንዲገባባት አድርጎታል፤ ይኸውም አዳምና ልጆቹ በአካለ ሥጋ ያጡትን ርስታቸው ገነትን በአካለ ነፍሳቸው ዳግመኛ ሊያገባቸው እንደመጣ የሚያመለክት መኾኑን በስፋት አስተምሯል፡፡

♥❖ ጌታችን በብሉይ ኪዳን ከነበሩት ከነቢያት ሙሴንና ኤልያስን በሐዲስ ኪዳን ከነበሩት ከሐዋርያት ሦስቱን በታቦር ተራራ ላይ ማውጣቱ፦

1) የታቦር ተራራ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ በመኾኗ ሲኾን በቤተ ክርስቲያናችን ብሉይ ኪዳንና ሐዲስ ኪዳን እንደሚነገሩ ለማመልከት

2) በተራራ በተመሰለች በጉባኤ ቤት ብሉይና ሐዲስ እንደሚነገሩ ለመግለጽ፡፡

3) ሌላው የታቦር ተራራ የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ስትኾን ይኸውም ጌታ ነቢያትንና ሐዋርያትን በተራራዋ ላይ መሰብሰቡ መንግሥተ ሰማያትን ነቢያትም ሐዋርያትም እንደሚወርሷን ለማመልከት

4) ሙሴ ያገባ ሲኾን ኤልያስ ድንግል ነውና መንግሥተ ሰማያትን ደናግልም ያገቡም እንደሚወርሷት ለማጠየቅ ነው፡፡

5) እንደ ያዕቆብ ዘሥሩግ ትርጓሜ ሙሴ ኦሪት ዘፍጥረትን ሲጽፍ፦ “በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ” (ዘፍ 1፡1) እንዳለ፤ ዮሐንስም “በመጀመሪያ ቃል ነበር” (ዮሐ 1፡1) ብሎ እንደ ሙሴ አምላክነቱን የሚመሰክር ነውና ሙሴ አስቀድሞ የጻፈልኝ፤ አኹንም ዮሐንስ አምላክነቴን የሚጽፍልኝ እኔ ነኝ ሲል ነው፡፡

6) ሙሴና ኤልያስ ይመሳሰላሉ፤ ይኸውም በሲና ተራራ 40 ቀንና ሌሊት እንደጾመ ኤልያስም በደብረ ኮሬብ 40 ቀንና ሌሊት የጾመ ነውና፨

7) ሙሴ ንጉሡ ፈርዖንን የገሠፀ እንደነበር ኤልያስም ንጉሡ አክዐብን የገሠፀ ነውና፨

8) ሙሴ ከንጉሡ ፈርዖን ፊት ሸሽቶ እንደሄደ ኤልያስም ከንግሥቲቱ ኤልዛቤል ፊት ሸሽቶ ሄዶ ነበር።

9) ዳግመኛም ሰማይኑን ዝናብ እንዳያዘንም በተሰጠው ሥልጣን ባሰረውና ከ3 ዓመት ከ6ወር ቆይታ በኋላ እንዲዘንብ በፈታው ኤልያስን እንዳመጣ ኹሉ የማሰር የመፍታት ሥልጣን ሥልጣነ ተሰጥቶት “እኔም እልሃለኹ፥ አንተ ጴጥሮስ ነኽ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥኻለኹ፤ በምድር የምታስረው ኹሉ በሰማያት የታሰረ ይኾናል፥ በምድርም የምትፈታው ኹሉ በሰማያት የተፈታ ይኾናል” (ማቴ 16፡18-19) ላለው ለጴጥሮስን ታላቅ ሰማያዊ ሥልጣን መስጠቱን ለማመልከት አምጥቷቸዋል፡፡

♥❖ በቤተ ክርስቲያንና በሀገራችን ያለው መንፈሳዊ አከባበር ደማቅ ነው፤ ይኽ በዓል በቤተ ክርስቲያን በማሕሌት በቅዳሴ በትምህርት የሚከበር በዓል ሲኾን በሀገርኛ የቡሄ በዓል ይባላል፤ ቡሔ ማለት ሊቁ ደስታ ተክለ ወልድ በመዝገበ ቃላት ላይ ሲገልጹት ቧ ብሎ በደብረ ታቦር የተገለጠው የጌታችንን የፊቱን ብርሃን ጸዳል የልብሱን እንደ በረዶ ነጭ መኾን ያስረዳል ስለዚኽ የብርሃን፣ ብርሃናዊ ማለት ነው፡፡

♥❖ በዚህ በዓል በታቦር የታየው የብርሃኑ ምሳሌ የሚሆን ችቦ ይበራል፤ ሌላው በዚኽ በዓል ሰሞን በገጠር ከተራራ ላይ እረኞች ሕጻናት ዥራፍ እየገመዱ ማስጮኻቸው ጌታ በተራራ ላይ ብርሃኑን በገለጸ ጊዜ አብ በደመና ኾኖ “እርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” ባለ ጊዜ ሐዋርያት በድምፁ ደንግጸው መውደቃቸውን ለማመለክት ነው፡፡

💥 ጌታችን ጌትነቱን ገልጦበታል። የአብ ድምፅ ተሰምቶበታልና ታቦር ተራራ ቅዱስ ነው። ቅዱስ ጴጥሮስም በመልእክቱ "ከገናናው ክብር፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይኽ ነው የሚል ያ ድምፅ በመጣለት ጊዜ ከእግዚአብሔር አብ ክብርንና ምስጋናን ተቀብሎአልና፤ እኛም በቅዱሱ ተራራ ከእርሱ ጋር ሳለን ይኽን ድምፅ ከሰማይ ሲወርድ ሰማን።" በማለት ገልጦታል (2ኛ ጴጥ 1:17-18)

♥❖ ሌላው ሙሉሙሉ ዳቦ መጋገሩ በትውፊት እንደምንረዳው ጌታ ብርሃኑን ሲገልጽ ብርሃኑ እስከ አርሞንኤም ተራራ ድረስ ያበራ ስለነበር እረኞች ሌሊቱ ኹሉ ቀን መስሏቸው እዛው ስለዋሉ ቤተሰቦቻቸው “ኅብስት” ይዘውላቸው ኼደዋልና የዚያ ምሳሌ እንደኾነ በአበው ትውፊት ይነገራል፡፡

💥[በደብረ ታቦር ላይ ብርሃኑን የገለጠው አምላካችን ክርስቶስ ምስጋና ይግባው]፡፡
[መልካም በዓል]
✍ መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ (በድጋሚ የተለጠፈ)

1.4K - 12