አንጋፋዋ ጋዜጠኛ የምወድሽ በቀለ አረፈች።
የብዙ አቅመ ደካሞች ጧሪ እና ደጋፊ የነበረችው ደራሲና ጋዜጠኛ የምወድሽ በቀለ ለአጭር ጊዜ ባጋጠማት ሕመም በሕክምና ስትረዳ ቆይታ ነሐሴ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ሌሊት አርፋለች።
የምወድሽ በቀለ የፖሊስና እርምጃው ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆና ረጅም ዓመታት አገልግላለች።
በድርሰትና በስነ ግጥም ስራዎቿም በርካታ አበርክቶዎች የነበሯት ነበረች፤ በ1979 ዓ.ም አብዮታዊ ግጥሞች ከሚለው ስራዋ ጀምሮ ወደ 16 መፃሕፍትን አሳትማለች።
የኢትዮጵያ ሴት ደራሲያት ማሕበርን በፕሬዘደንትነት ዘለግ ላሉ አመታት መርታለች።
የኢትዮጵያ ሴቶች ማሕበራት የቦርድ ሰብሳሰቢ ሆና አገልግላለች።
ሴቶች ይችላሉ Women can do it የተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት መስራችና ዋና ዳይሬክተርም ነበረች።
በሕይወት ዘመኗ በርካታ ሽልማቶችንም ባበረከተቻቸው አስተዋፅኦዎች አግኝታለች። የ2016 ዓ.ም የበጎ ሰው ሽልማትን ጨምሮ ሌሎችንም አግኝታለች።
ነሐሴ 19 ቀን 1951 ዓ.ም አዲስ አበባ የተወለደችው የምወድሽ በቀለ የአራት ልጆች እናትና የ5 የልጅ ልጆች አያት ነበረች።
40 - 2
Mese today የመዝናኛ ቻናል ነው። የመዝናኛ መረጃዎች፣ የመሴ አዝናኝ ውሎና አጫጭር ወቅታዊና አነጋጋሪ ጉዳዮችን በየዕለቱ ያቀርባል ።በየዕለቱ ሰላማችሁ ይብዛ። እወዳችኋለሁ ።
Joined 22 August 2025