ብሬማን ፊልም ፕሮዳክሽን ሃበሻዊ ለዛ የተላበሱ፣ አዝናኝ እና ቁም ነገረኛ ዝግጅቶችን ያሰናዳል ወደ ተመልካችም ያቀርባል።አላማ አድርጎ ከተነሳበት በጥበቡ ዘርፋ እምርታዊ አሰተዋጾ በማበርከት እና በአንጋፋዎች እና በወጣቶች መካከል ያለውን የዘመን ቅብብሎሽ እንደ ድልድይ ሆኖ በማጠናከር ረገድም ጉልህ ሚና እየተጫወተ ሲሆን፣ወጣት ከያኒያንን ከማብቃት፣ተስፈኛ ጀማሪዎችን ከህልማቸው በማገናኘት፣ለህዝብ ከማስተዋወቅ፣ተተኪ ከማፍራት፣አቅም እና ችሎታ ኖሯቸው ተደራሽ ያልሆኑ የጥበብ ቤተሰቦችን ዳግም ወደ ተመልካች እንዲቀርቡ እድል በመፍጠር፣ ድንቅ ጅማሮ ኖሯቸው ድጋፍ ለሚሹም አጋር በመሆን ለኪነ-ጥበቡ አለም ብቁ ባለሞያዎችን በማበርከት አኳያም በብዙ የሚያስመሰግኑ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።
ከዚህም ባለፈ በየሞያ ዘርፋቸው የሚሰሩለትን ማህበረሰብ ከማገልገል በላይ ለብዙሃኑ አርአያ መሆን የቻሉ ባለውለታዎችን የሞያ ዘርፍ ሳያግደን እናመሰግናለን፣እዘክራለን እንዲሁም እናከብራለን።
ከፊልም፣ከሙዚቃ፣ ከፕራንክ እና ከተያያዥ የጥበብ ስራዎች በተጨማሪም በአዕምሮ ህመም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በመስራት ማህበራዊ ሃላፊነትን በመወጣት ላይ ይገኛል።
Bireman Film Production provides Habesha taste contents, entertaining and serious productions for the audience.It has also playing a significant role in the development of the arts and as a bridge between the elite and the youth, connecting young people with their dreams and introducing them to the public.
Welcome!