Channel Avatar

አረንዛው ዳሞት (Arenzaw damote) @UCZvpywKCZTa1RQnygWynWYw@youtube.com

3.6K subscribers - no pronouns :c

ይህ የአማራ ፋኖ በጎጃም የራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም የአረንዛው ዳሞት ብርጌድ የሚዲያ ክፍል


Welcoem to posts!!

in the future - u will be able to do some more stuff here,,,!! like pat catgirl- i mean um yeah... for now u can only see others's posts :c

አረንዛው ዳሞት (Arenzaw damote)
Posted 4 weeks ago

[ለመንግስት ሰራተኞች የተላለፈ ጥሪ ]
ከአማራ አብራክ ወጣችሁ ለጭራቁ መንግስት ለብልፅግና ወንበር አስጠባቂዎች የሆናችሁ የፀጥታ አካላት እና የመንግስት ሰራተኛች በሙሉ ትግላችንን ከጀመርን እነሆ አንድ አመት አሳልፈን የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንገኛለን ። ስለሆነም የሰው በላው ጭራቅ ስርዓት ከፈራረሰ አንድ አመት አልፎታል ። በዚህም መሰረት ህዝባችንን ከገጠር እስከ ከተማ ፋኖ በማህበራዊ ልማት ፣ በፍትህ አገልግሎት ፣ በፀጥታ አገልግሎት እና በመሰል ጉዳዮች ስናገለግል ቆይተናል እያገለግልንም እንገኛለን ። አሁን የሚቀረው የመጨረሻውን ምዕራፍ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ብልፅግና የሚባለውን ሰው በላ ጭራቅ መንግስት ልንቀብረው ዶማውን ፣ አካፋውንም ፣ ጦሩንም ፣ መሳሪውንም አዘጋጅቶ የመጨረሻዋን ፊሽካ እስኪነፋ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል !!! ስለሆነም ይህ ከመሆኑ በፊት ለፀጥታ እና ለመንግስት ሰራቶኞች ከወገናችሁ (ከተገፋው ህዝብ )ጋር ትሰለፉ ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባለን ። አማራ አማራን አይገለውም ! እንዲሁም ፋኖ የህዝብ ልጅ ነው ። በሚለው መርሀችን እስከዛሬ እናንተን ከጉዳት ስንጠብቅ ቆይተናል ። ፋኖ ጭራቁ መንግስት እንደሚያወራው ሳይሆን ለተገፋት፣ ለተበደለ ህዝቦች እየታገለ እና ፍትህ እያስጠበቀ ይገኛል ። ይህንን ደግሞ እንኳን አማራ የሆነ በሙሉ ፤ ኢትዮጵያ የሆነ በሙሉ ከዛም አልፎ የአለም ህዝብ ይመሰክራል ። እናንተም ይህን ተረድታችሁ ከጭራቁ ከሰው በላ መንግስት እራሳችሁን እንድታገሉ እና ከተገፋው ህዝብ ጎን እንድትቆም እንደ አማራ ፋኖ በጎጃም ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም (5ተኛ) ክፍለ ጦር የአረንዛው ዳሞት ብርጌድ ሚዲያ ክፍል መልዕክቱን አስተላልፋል ።

አዲስ ትውልድ !
አዲስ አስተሳስብ !
አዲስ ተስፋ !

ድል ለአማራ ፋኖ

45 - 0