Channel Avatar

ወልደሰንበት woldesenbet ቅዱስ ሚካኤል ፣ ጠባቂየ ። @UCWnWBd5n5ax79GPShO8XhhQ@youtube.com

3.5K subscribers - no pronouns :c

መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦ


Welcoem to posts!!

in the future - u will be able to do some more stuff here,,,!! like pat catgirl- i mean um yeah... for now u can only see others's posts :c

ወልደሰንበት woldesenbet ቅዱስ ሚካኤል ፣ ጠባቂየ ።
Posted 7 months ago

✝️እንኳን ለሊቀ መላዕክት ቅድስ ገብርኤል✝️ ✝️ዓመታዊ በዓል አደርሳችሁ አደረሰን✝️

✝የቅዱስ ገብርኤል የክብር ስግደት ✝

ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ወደኔ ና 3X
ሊቀ መልአኩ ሆይ ወደኔ ና 3X
መልአከ መጋቤ ሐዲስ ሆይ ወደኔ ና 3X
እሰገድ ለገብርኤል 3X
ምስጋና ይሁን ለገብርኤል 3X
ስብሐት ይሁን ለገብርኤል 3X
ውዳሴ ይገባሌ ለገብርኤል 3X

አብሳሪው ገብርኤል፥ የአብ መልእክተኛ
አብሳሪው ገብርኤል፥ የወልድ ባለሟል
አብሳሪው ገብርኤል፥ የመንፈስ ቅዱስ አገልጋይ
አብሳሪው ገብርኤል፥ አብሳሪ ድንግል
አብሳሪው ገብርኤል፥ የካህናተ ሰማይ ጎደኛ
አብሳሪው ገብርኤል፥ የሚካኤል ወዳጅ
አብሳሪው ገብርኤል፥ የመኃይማንን ከለላ
አብሳሪው ገብርኤል፥ አጽናኝ መልአክ
አብሳሪው ገብርኤል፥ አማላጅ ተራዳኢ
አብሳሪው ገብርኤል፥ እሳተ ነበልባል
ኦ የራማው ንጉሥ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ፥ ክብርና ምስጋና ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘላለመ ዓለም አሜን
ይሄ ሊንክ በመንካት በድምፅ አብረን መስገድ እንችላለን እንኳን አደረሳችሁ።
https://youtu.be/i84-vo-y74E


+   👏 #ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ገብርኤል  👏    +
                    #ታህሳስ_19

✝️ የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም ላይ ቍጣ ሞላበት፥ የፊቱም መልክ ተለወጠባቸው፤ እርሱም ተናገረ፥ የእቶንም እሳት ይነድድ ከነበረው ይልቅ ሰባት እጥፍ አድርገው እንዲያነድዱት አዘዘ።

🔥 ሲድራቅንና ሚሳቅንም አብደናጎንም ያስሩ ዘንድ፥ ወደሚነድድም ወደ እቶን እሳት ይጥሉአቸው ዘንድ በሠራዊቱ ውስጥ ከነበሩት ኃያላን አዘዘ ። የዚያን ጊዜም እነዚህ ሰዎች ከሰናፊላቸውና ከቀሚሳቸው ከመጐናጸፊያቸውም ከቀረውም ልብሳቸው ጋር ታስረው በሚነድድ በእቶን እሳት ውስጥ ተጣሉ።

✝️የንጉሡም ትእዛዝ አስቸኳይ ስለሆነ የእቶኑም እሳት እጅግ ስለሚነድድ፥ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም የጣሉአቸውን ሰዎች የእሳቱ ወላፈን ገደላቸው።

🔥እነዚህም ሦስቱ ሰዎች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ታስረው በሚነድደው በእቶኑ እሳት ውስጥ ወደቁ።የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከደነፆር ተደነቀ ፈጥኖም ተነሣ፤ አማካሪዎቹንም፦ ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን? ብሎ ተናገራቸው። እነርሱም፦ ንጉሥ ሆይ፥ እውነት ነው ብለው ለንጉሡ መለሱለት።

✝️ እርሱም፦ እነሆ፥ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ፤ ምንም አላቈሰላቸውም፤
#የአራተኛውም_መልክ_የአማልክትን_ልጅ_ይመስላል ብሎ መለሰ። የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር ወደሚነድደው ወደ እሳቱ እቶን በር ቀርቦ፦

🔥እናንተ የልዑል አምላክ ባሪያዎች፥
#ሲድራቅና #ሚሳቅ  #አብደናጎም፥ ኑ ውጡ ብሎ ተናገራቸው። ሲድራቅና ሚሳቅም አብደናጎም ከእሳቱ መካከል ወጡ። መሳፍንቱና ሹማምቶቹም አዛዦቹና የንጉሡ አማካሪዎች ተሰብስበው እሳቱ በእነዚያ ሰዎች አካል ላይ ኃይል እንዳልነበረው፥ የራሳቸውም ጠጕር እንዳልተቃጠለች፥ ሰናፊላቸውም እንዳልተለወጠ፥ የእሳቱም ሽታ እንዳልደረሰባቸው አዩ።

✝️ ናቡከደነፆርም መልሶ፦ #መልአኩን_የላከ_ከአምላካቸውም_በቀር_ማንንም_አምላክ_እንዳያመልኩ_ለእርሱም_እንዳይሰግዱ_ሰውነታቸውን_አሳልፈ_የሰጡትን_የንጉሡንም_ቃል_የተላለፉትን_በእርሱ_የታመኑትን_ባሪያዎቹን_ያዳነ_የሲድራቅና_የሚሳቅ_የአብደናጎም_አምላክ_ይባረክ።

✝️ እኔም እንደዚህ የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም አምላክ ላይ የስድብን ነገር የሚናገር ወገንና ሕዝብ በልዩ ልዩም ቋንቋ የሚናገሩ ይቈረጣሉ፥ ቤቶቻቸውም የጕድፍ መጣያ ይደረጋሉ ብዬ አዝዣለሁ አለ።
      ( ትንቢተ ዳንኤል 3 ፥ 19 - 30 )

    ~~~
            #ገብርኤል ሆይ
የአብ አካላዊ ቃል መሳክወ ብርሀን ለሚሆኑ ጆሮችህ
              ሰላም እላለው
የውበታቸው ጸዳል የበረሃ አበባ ለሚመስለውም ጉንጮችህ
               ሰላም እላለው
               ገብርኤል ሆይ
ከጭንቅና ከመከራ ለማውጣት የተላክህ መልአክ ነህና
#ሠለስቱ_ደቂቅ በእሳት ጉድጓድ በተጣሉ ጊዜ
ሁለቱ ክንፎችህን ጋርደህ ከመቃጠል እንዳዳንሃቸው
እእኔንም አገልጋይህን በረድኤትህ ኃይል አድነኝ ።
                 ~~       
                            🙏
🔥 ከሚነደው እቶን እሳት ሠለስቱ ደቂቅን የታደገ 🔥
            #ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ገብርኤል
        ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ ይሰውረን
                             🙏

11 - 0

ወልደሰንበት woldesenbet ቅዱስ ሚካኤል ፣ ጠባቂየ ።
Posted 9 months ago

+ 🍂 #አብ_ወልድ_መንፈስ_ቅዱስ በአነዋወር አንድ +
በገጽ ሦስት ሦስት ናቸው ።
~ ~ ~
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በአካል ሦስት
#በመለኮት_አንድ_ናቸው ።
~ ~ ~
አብ በአካሉ ፍጹም ነው
ወልድም በአካሉ ፍጹም ነው
መንፈስ ቅዱስም በአካሉ ፍጹም ነው
እሊህ ሦስቱ አካላት በመለኮት አንድ ናቸው ።
~ ~ ~
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
ኃያልና የሚያስፈራዓይኑ እንደ እሳት የሚነድ እሱ አንድ ቅዱስ ነው።
~ ~ ~
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
የራስ ጸጉሩ አንደበረድ የነጻ
እንደ ሰርዲኖስ እና ኢያሰጲድ ዕንቊ የከበረ እሱ አንድ ቅዱስ ነው።
~ ~ ~
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
የመቅደሱ አጥር በእሳት የታጠረ እሱ አንድ ቅዱስ ነው ።
~ ~ ~
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
በጠላት ፊት የማይበገር እሱ ጽኑዕ አዳራሽ ነው ።
~ ~ ~
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
ጠፈርን ያለምሰሶ መሬትን ያለ መሠረት ፈጥሮ ያለ ድጋፍ በቃል ብቻ ያፀና እሱ አንድ ቅዱስ ነው ።
~ ~ ~
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
ሁሉን በየወገኑ የሚገዛ እሱ አንድ ቅዱስ ነው።
~ ~ ~
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
#መንግሥቱ_የማያልፍ_ግዛቱም_ለዘለዓለም_የሚኖር_እሱ_አንድ_ቅዱስ_ነው።
~ ~ ~
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
የሦስትነቱ ሥርዓት የማይለወጥና ለሦስትነቱ ምስጋና የሚገባው እሱ አንድ ቅዱስ ነው።
~ ~ ~
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
መባርቅት የሚላኩለት ነጎድጓድ የሚያመሰግኑት እሱ አንድ ቅዱስ ነው።
~ ~ ~
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
አንድ ሲሆን ሦስት ሦስት ሲሆን አንድ የሚሆን እሱ አንድ ቅዱስ ነው ።

🍀 🍀 🍀 🍀 🍀
ዓለምን ካለመኖር ወደመኖር ያመጣ እሱ
እግዚአብሔር ነው።
ቁጣውን በቸርነቱ ባሕር የሚያሰጥማት እሱ
እግዚአብሔር ነው ።
የመቅሠፍቱን እሳት በይቅርታው ውሃ የሚያጠፋ እሱ
እግዚአብሔር ነው ።
የማይቀየም የዋህ ንስሐን የሚወድ እሱ
እግዚአብሔር ምስጉን ነው ።
ኃጢአትን በቸርነቱ ጥላ የማሸፍን እሱ
እግዚአብሔር ነው።
አበሳን በቸርነቱ ጒድደጓድ የሚደፍን እሱ
እግዚአብሔር ምስጉን ነው ።
በደልን በትዕግስቱ መጋረጃ የሚጋርድ እሱ
እግዚአብሔር ምስጉን ነው።

✝️ 🙏 🙏 🙏 ✝️
ለእሱ ለብቻው ምስጋና ይገባል ።
#ለመንግሥቱም እዘዝ ይገባል ።
#ለሦስትነቱ ክብር ይገባል ።
#ለከኃሊነቱ ኃይል ይገባል ።
#ለመለኮቱ ሥልጣን ይገባል ።

ለዘለዓለሙ አሜን
🙏
°°°°°°°°°°°°°°°°°°
/ የረቡዕ ሠይፈ ሥላሴ /

ዲ/ን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
t.me/deacongetabalewamare

75 - 1

ወልደሰንበት woldesenbet ቅዱስ ሚካኤል ፣ ጠባቂየ ።
Posted 9 months ago

🌹 #ሱላማጢስ_ከስደት_ተመልሳለች 🌹
#የኛስ_መመለሻችን_መቼ_ይሆን ?

🍂 #ኅዳር_ስድስት ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አዝላ ከአረጋዊ ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ሦስት ዓመት ከመንፈቅ በስደት ከኖሩ በኋላ ቅዱስ ገብርኤል ለዮሴፍ እንዲህ አለው ፦

❝ ሕፃኑን የሚሹት ሄሮድስና ሠራዊቱ ሞተዋልና እናቱንና ሕፃኑን ይዘህ ወደ ሀገርህ ተመለስ ❞ ( ማቴ 2 ፥ 19 ) ባለው ጊዜ አረጋዊ ዮሴፍ እናትና ልጁን ይዞ ሰሎሜን አስከትሎ ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ከስደት ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሱ ደብረ ቁስቋም በተባለ ቦታ ያረፉበት ተራራ ነው ።

ዐምስት ሺ ዐምስት መቶ ዘመን ሙሉ ሰላም ላጣ ለአዳም ሰላም የሆነች
❝ ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ❞ ተብሎ እንዲመሰገን ምክንያት የሆነች የሰላም አናት የሰላም እመቤት ድንግል ማርያም
🌹#ሱላማጢስ_ከስደት_ተመልሳለች 🌹

🍂 እኛስ መቼ ይሆን ዛሬ በኀጢአት ስደት ያለን ብዙዎች ነን የሠራነው ኀጢአት ከእግዚአብሔር ፊት ከቤተ ክርስቲያን ደጅ ያሳደደን ብዙዎች ነን በትዕቢት ልብ ተይዘን ትላንት ካስቀደስንባት ፣ ከቆረብንባት ከቀደስንባት ከተማርንባት ካስተማርንባት ደጅ የተሰደድን #መመለሳችን_መቼ_ይሆን ?

መቼ ይሆን ? ከሥጋ ወደሙ የተሰደድን ከልጅነት ጊዜያችን በኋላ ፣ ከትዳራችን በኋላ ፣ ከአገልግሎታችን በኋላ ሥጋ ወደሙን መቀበል ያቆምን ከሕይወት ምግብ የተሰደድን ሥጋችን እየደለበ ነፍሳችን የቀጨጨችብን #መመለሳችን_መቼ_ይሆን ?

🍂 ከአገልግሎት የተሰደድን ትላንት እንዘምር ፣ እንማር እናስተባብር የነበርን አገልጋዮች ዛሬ የት ነን ? #መመለሳችን_መቼ_ይሆን ?

#ወዳጄ_በቤተ_ክርስቲያን_አለሁ_እንጂ_ነበርኩ_አያድንምና ያለነው የነበርንበት ቦታ ካልሆነ ወደ ነበርንበት እንመለስ በደልን እንጂ በደለኛን ወደ ማይጠላ አምላክ እንመለስ የት ናችሁ ስንባል ከምናፍርበት ቦታ እንዳንገኝ ወደ ደገኛይቱ ቤት ወደ ቤተ ክርስቲያን እንመለስ ።
✏️ Daweit Tesfay

ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሳሉት
ለሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ቤ/ክ (ቨርጂኒያ)

ዲ/ን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ

60 - 3

ወልደሰንበት woldesenbet ቅዱስ ሚካኤል ፣ ጠባቂየ ።
Posted 9 months ago

+ + አቤቱ ጌታዬ #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሆይ + +
ከቤተ ያዕቆብ የወጣ የዘይት ዛፍ
ከዕሴይ ሥር የወጣ የሃይማኖት በትር፤
ከዳዊት ግንድ የበቀለችም አበባ ነኽ (ኢሳ ፲፩፥፩)፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
በቅዱሳን አንደበት አንተ የሚጣፍጥ ስም ነኽ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
በእውነት ለሚጠሩኽ አንተ የሚጣፍጥ ዕሳቤ ነኽ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
አንተ መንፈሰ ኮከባቸው ለደበዘዘባቸው መመኪያ የኾንኽ የአጥቢያ ኮከብ ነኽ (ዘኊ ፳፬፥፲፯፤ ራእ ፳፪፥፲፮)፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በቅዱሳን ገጽ ላይ ዘወትር የሚያበራ የጽድቅ ፀሓይ ነኽ (ሚል ፬፥፪)፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከቊጣው የተነሣ የጨለማ አበጋዞች የደነገጡለት፤ ከማግሣቱም የተነሣ የምድር ተራሮች የተንቀጠቀጡለት ከይሁዳ ነገድ የተገኘ አሸናፊ አንበሳ ነኽ (ራእ ፭፥፭)

___
+ #አቤቱ_ጌታዬ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሆይ
ከሕፃንነቴ ዠምረኽ ተስፋዬ አንተ ነኽ፤

+ በማሕፀንኽ አንተ ሰወርኸኝ በኹሉም ጊዜ አንተ ዕሳቤዬ ነኽ ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የመድኀኒቴ ቀንድ አንተ ነኽ

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የራሴ አክሊል አንተ ነኽ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
ለአፌ ጣፋጭ የኾንኽ የሕይወት እንጀራ አንተ ነኽ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለጒረሮዬ
መልካም የኾንኽ የመድኀኒት ጽዋዕ አንተ ነኽ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
ያልተሸመነም ያልተፈተለም ልብስ አንተ ነኽ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
ዕጥፍ የኾንኽ ወርቅ የተገኘኽም ዕንቊ ነኽ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
የበዛ ምናን የተረፈም መክሊት አንተ ነኽ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ስለ አዳምና ስለ ልጆቹ ስትል መከራን የተሸከምኽ አንተ ነኽ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በሔዋንና በልጆቿ ስሕተት ምክንያት የመስቀልን ሕማማት የተሸከምኽ አንተ ነኽ፤

+ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ስለ ሰው ልጆች በደል ስትል የመስቀልን ችንካሮች የተቀበልኽ አንተ ነኽ፤

+ አቤቱ አንተ በኹሉም ላይ ጌታ ነኽ፤
ሥልጣንኽም በኹሉም ላይ ነው፤
ታላቅነትኽም ከኹሉም በላይ ነው፤
የኹሉም ጌታ ተባልኽ፤
በኹሉም ዘንድ ተጠራኽ፤

__
+ አንተ #ሊቀ_ካህናት ነኽ፤
+ አንተ ንጉሠ ነገሥት ነኽ፤
+ አንተ ታላቅ መምህር ነኽ፤
+ አንተ የእረኞች አለቃ ነኽ፤
+ አንተ የምትናገር በግ ነኽ፤ አንተ ፍሪዳ ላም ነኽ፤
+ አንተ የአንበሳ ልጅ አንበሳ ነኽ፤
+ አንተ የሕይወት ውሃ ምንጭ ነኽ፤
+ አንተ #የመድኀኒት_ቀንድ ነኽ፤
+ አንተ የጽድቅና የሕይወት መንገድ ነኽ፤
+ አንተ የጽድቅ ፀሓይ ነኽ፤
+ አንተ የብርሃን ኮከብ ነኽ፤
+ አንተ #የሕይወት_እንጀራ ነኽ፤
+ አንተ የመድኀኒት ጽዋ ነኽ፤
+ አንተ የሰው ልጅና የእግዚአብሔር ልጅ ነኽ፤
___
ይኽነን ኹሉ ስለ እኛ ፍቅር ስትል ተጠራኽበት) በማለት አምላኩ ኢየሱስ ክርስቶስን ያመሰገነው ምስጋና እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሲነበብ፣ ሲተረጐም፣ ሲመሰጠር ይኖራል፡፡

ዮሐንስ በራዕዩ ላይ በኲረ ሙታን (ራእ ፩፥፭)፤
የምድር ነገሥታት ገዢ (ራእ ፩፥፭)፤
የታመነው ምስክር (ራእ ፩፥፭)፤
የይሁዳ አንበሳ (ራእ ፭፥፭)፤
የታረደው በግ (ራእ ፭፥፲፪)፤
የታመነና እውነተኛ (ራእ ፲፱፥፲፩)፤
የእግዚአብሔር ቃል (ራእ ፲፱፥፲፫)፤
ፊተኛውና ኋለኛው (ራእ ፳፪፥፲፫)፤
የነገሥታት ንጉሥ የጌቶች ጌታ (ራእ ፲፱፥፲፮)፤
አልፋና ኦሜጋ (ራእ ፳፪፥፲፫) ፊተኛውና ኋለኛው (ራእ ፳፪፥፲፫)፤
የዳዊት ሥርና ዘር (ራእ ፳፪፥፲፮)፤
የሚያበራ የንጋት ኮከብ (ራእ ፳፪፥፲፮)
-------------------------------------------
/ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /

#ጌታችን_አምላካችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሆይ
ዘወትር እናመሰግንህ ዘንድ
ውሳጣዊ አዕምሯችንን ብሩህ አድርግልን ።
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

ሠዓሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሣሉት

83 - 8

ወልደሰንበት woldesenbet ቅዱስ ሚካኤል ፣ ጠባቂየ ።
Posted 1 year ago

እንኳን ለሊቀ መልአክ ቅዱስ ዑራኤልበአል አደረሰን
ይሄን የክብር ስግደት አብረን እንስገድ አሜን😇💚💛❤🙏

+    #ቅዱስ_ዑራኤል    +  
+
ዑራኤል ሆይ እግዚአብሔር ኃይሉን የሚገልጽበት
መልክአ ብርሃናት አንተ ነህ ።
          🍂  +     +     +
በዕለተ ስቅለት
በደመ ወልድ ዋህድ ዓለምን ለመቀደስ
ከሁሉ ይልቅ አንተ ተሰይመሀልና
ስለክብርህ የሰማይ መላእክት አደነቁ ።
       🍂     +     +      +
አቤቱ በወልድ የከበረ ደሙ መረጨት ዓለምን ትቀድስ ዘንድ
ከተራራ ከቦታ ወደ ቦታ በመዘዋወር የመለኮትን ደም የረጨህ
#ዑራኤል ሆይ
ለዓይን ደስ የምታሰኝ የጥበብ መፍለቂያ ምንጭ አንተ ነህና
ከእግዚአብሔር በተሰጠህ ክንፈ ረድኤት ስተከንፍ መጥተህ
አፋጣኝ እርዳታ አድርግልን ።
        🍂    +      +     +
https://youtu.be/JnAeoM5Zovc

14 - 0

ወልደሰንበት woldesenbet ቅዱስ ሚካኤል ፣ ጠባቂየ ።
Posted 1 year ago

🌹 የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ 🌹

🔥 መንፈሳቸውን ያረከሱ ሰዎች ከእርሱ ሊቀምሱት የማይቻላቸው በእውነት ቁርባን ነው ።

🔥በበግ በጊደር በላም ደም እንደ ነበረው እንደ ቀደሙት አባቶች መሥዋዕት አይደለም አሳት ነው እንጂ

❖ የቀደመው መሥዋዕት
- ጊዚያዊ ነው
- ኃላፊ ነው
- ምሳሌ ነው
-አፍአዊ ነው
✝ የሐዲስ ኪዳን መሥዋዕት
- ዘላለማዊ ነው
- ኢኃላፊ ነው
- አማናዊ ነው
- ውሳጣዊ ነው

👉 " የላምና የፍየል ደም በረከሱትም ላይ የሚረጭ የጊደር አመድ የሚያነጻና የረከሱትንም ሥጋቸውን የሚቀድሳቸው ከሆነ ፥
✤ ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም ሕያው እግዚአብሔርን እናመልከው ዘንድ ሕሊናችንን ከሞት ሥራ እንዴት ይልቅ ያነጻ ይሆን። "
( ዕብ 9 ፥ 13 , 14 )

🔥 ፈቃዱን ለሚሠሩ ልቡናቸውን ላቀኑ ሰዎች የሚያድን እሳት ነው ስሙን ለሚክዱ ለዓመጸኞች ሰዎች የሚባላ እሳት ነው።

🔥 አሳታውያን የሚሆኑ ሱራፌልና ኪሩቤል ሊነኩት የማይቻላቸው በእውነት እሳት ነው።

✦ ከሱራፌል አንዱ ወደ እኔ ተላከ፤
👉 በእጁም ከመሠዊያው በጒጠት የወሰደው ፍም ነበረ።
አፌንም ዳሰሰበትና " እነሆ ይህ ከንፈሮችህን ነክቶአል ፤ በደልህም ከአንተ ተወገደ ፤ ኃጢአትህም ተሰረየልህ " አለኝ
( ኢሳ 6 ፥ 6 )

🔥🌹🔥🌹🔥🌹🔥🌹

ማርያም ሆይ ስለዚህ እንወድሻለን ከፍ ከፍም እናደርግሻለን
አውነተኛ የጽድቅ መብልንና እውነተኛ የሕይወት መጠጥን
ወልደሽልናልና
🙏
( ቅዳሴ ማርያም )

+ + + + + + + + + +

🌹 አነ ውእቱ ሕብስተ ሕይወት ዘለአለም 🌹
#የሕይወት_እንጀራ_እኔ_ነኝ

🌸አባቶቻችሁ በምድረ በዳ መና በሉ ሞቱም፤

🌸ሰው ከእርሱ በልቶ እንዳይሞት ከሰማይ አሁን የወረደ እንጀራ ይህ ነው።

🌸 ከሰማይ የወረደ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ ።

🌸 ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል ፤

🌸 እኔም ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው።

እንግዲህ አይሁድ ፤ ይህ ሰው ስጋውን ልንበላ ይሰጠን ዘንድ
እንዴት ይችላል ? ብለው እርስ በእርሳቸው ተከራከሩ።

🙏 ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው።

🌸 እውነት እውነት እላችኋለው ፤ የሰውን ልጅ ስጋውን ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ
👉 በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም።

🌸ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት
አለው።👉 እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለው።

🌹 ሥጋዬ እውነተኛ መብል ፤ ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነው።

👉 ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠ፦
🌹 በእኔ ይኖራል።
🌹 እኔም በእርሱ እኖራለሁ።
( ዮሐ. 6 ፥ 48 - 56 )


አምላካችን ሆይ አንደቸርነትህ ነው እንጂ እንደ በደላችን አይሁን
🙏 ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም ያድርሰን🙏

34 - 2

ወልደሰንበት woldesenbet ቅዱስ ሚካኤል ፣ ጠባቂየ ።
Posted 1 year ago

🍂 ✞ #አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ✞ 🍂
ተአምራቱና ትሩፋቱ እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነ ቅዱስ አባት ተጋዳይ አባ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የእረፍቱ ቀን መታሰቢያ ሆነ፡፡
📍 ...... #መጋቢት_5....... 📍

+ 🍂 ይህም ቅዱስ አባት በተወለደባት ቀን ድንቅ የሆነ ስራን ሰራ ተነስቶ ከእናቱ እቅፍ ወርዶ ከጨለማ ወደ ብርሀን ላወጣኸኝ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን እያለ ለስላሴ ሰግዷልና ምስጋናም አቅርቧልና።

📍+ ህፃኑም ሶስት አመት በሆነው ጊዜ የእግዚአብሔር መልክተኛ ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ህፃኑን ከእናቱ እቅፍ አንስቶ ብዙ ባህታውያን ወዳሉበት ገዳም ወስዶ በደጅ አኖረው ወደ አበምኔቱ ወደ አባ ዘመደ ብርሀንም ገብቶ ስለ ህፃኑ እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ነገረው።

📍+ በዚያን ጊዜም ነገሩ እውነት እንደሆነ ይረዳ ዘንድ አባ ዘመደ ብርሀን ተነስቶ ወደ ደጅ ወጣ። መልአኩም እንደ ነገረው ህፃኑ ከበር ተቀምጦ ፈገግታን ተሞልቶ አገኘው። እጅግም
በፍቅር በስነስርአት አሳደገው። የዳዊትን መዝሙርና ቤተ ክርስቲያን የምትቀበላቸውን መፃህፍት ሁሉ ብሉይንና ሀዲስን አስተማረው። ከዚያም በኃላም ክህነት ይሰጠው ዘንድ ስሙ አብርሀም ወደሚባል ጳጳስ ወሰደው ጳጳሱም በአየው ጊዜ ደስ አለው። የዲቁና ማእረግንም ሾመው እንደ ቀዳሜ ሰማእት እስጢፋኖስም ፀጋንና ሞገስን የተመላ ሆነ።

+ ከጥቂት ቀኖች በኃላም በጌታችን ትእዛዝ ቅስና ተቀበለ። በፆም በፀሎት በስግደት በብዙ ትጋትም እየተጋደለ በበረሀ ውስጥ ብቻውን ኖረ። በበረሀም ብዙ ዘመናትን ሲኖር ነፍሱን "ነፍሴ ሆይ እወቂ በእግዚአብሔር ፊት ራቁትሽን ትቆሚ ዘንድ እንዳለሽ እንግዲህስ ፅኚ በርቺ ታገሺ!" ይለት ነበር። ቆዳው ከዐጥንቱ እስቲጣበቅ ያለ መብልና ያለ መጠጥ በእንዲህ ያለ ግብር በገድል ተጠምዶ ኖረ።ከእፅዋት ፍሬዎች ወይም ከእንጨት ስሮች አልተመገበምና ለስጋውም የሚጠቅም ምንም ምን ምክንያት አልፈለገም።

📍 ለ #ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ እግዚአብሔር እንዲህ አለው ከእንግዲህ በአለም ካሉ ሰዎች ከካህናት ከመነኮሳት ወይም ከምእመናን ህዝባውያን እንዳያውቁህ አደርግልሀለሁ። እንዳንተ ካሉ በቀር አንተ ራስህ ብትፈቅድ እንጂ መላእክትም ይጎበኙሀል። የብርሀን ሰረገላም ይሁንልህ መድረስ ወደምትሻበት ሁሉ ብረር እኔንም ማየትና በፈለግህ ጊዜ ከአባቴና ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ በሶስትነቴ ታየኛለህ። አሁንም ወደ ኢትዮጵያ ምድር ሂድ በዚያም ከደይን የምታወጥቸው ነፍሳት አሉህ አለው።

🍂+ ከዚህም በኃላ ስልሳ አንበሶች ስልሳ ነብሮች በፊት በኃላ አጅበውት ወደ ኢትዮጵያ ምድር ተጓዙ። የእግዚአብሔር መልእክተኛ ቅዱስ ገብርኤልም ከአንበሶችና ከነብሮች ጋር በነፋስ ሰረገላ አሳፍሮ ይመራው ነበር። ወደ ምደረ ከብድም አደረሰው ከዚያም ወደ ልዩ ተራራ ወደ ደብረ ዝቋላ ወሰደው።

🍂+ አባታችንም በባህሩ ቁሞ ምስራቁን ምዕራቡን ሰሜኑን ደቡቡን አራቱን ማእዘን ተመለከተ።የኢትዮጵያ ሰዎች የሚሰሩትን ኃጢአታቸውን በአይኖቹ ፊት የተገለጠ ሆኖ አየ። በራሱም ተዘቅዝቆ ተወርውሮ ወደ ባህሩ ውስጥ ገባ እሊህን የእጅህ ፍጥረቶች የሆኑትን ካልማርካቸው ከእዚህ ባህር እንዳልወጣ በእግሮቼም እንዳልቆም በህያው ስምህ እምላለሁ እያለ ማለ እንዲሁም ሆኖ አርባ ቀን አርባ ሌሊት ኖረ።

📍 #ስምህን_የጠራውን

📍 #መታሰቢያህን_ያደረገውን_እምርልሀለሁ

የሚል ቃል በመልአክ አማካይነት ወደ አባታችን መጣ። አባታችንም መልአኩን መላውን የኢትዮጵያን ሰው ካልማረልኝ ከዚህ ባህር አልወጣም አለው መልአኩም ከአጠገቡ ሄደ።

🍂 #አባታችን_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስም በዚያ ባህር ውስጥ መቶ ዓመት ኖረ ስጋው ሁሉ አለቀ ደሙም በባህሩ ውስጥ ፈሰሰ አጥንቶቹም እንደበረዶ ነጭ ሆነው ታዩ። አጋንንትም ከአራቱ ማእዘን በየቀኑ ሰባት መቶ ሽህ ሶስት መቶ ሽህ እየሆኑ በመምጣት በቀስታቸው ይነድፉታል እስከ መቶ አመትም አጥንቶቹን በሻፎ ድንጋይ ይፍቁታል ይህን ሁሉ መከራ በትእግስት ሲቀበል ኖረ።

ከዚህም በኃላ ጌታችን ወደርሱ መጥቶ ከባህሩ ዳር ቆመ። አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስንም መላውን የኢትዮጵያ ሰው ምሬልሀለሁና ተነስተህ ውጣ አለው ያንጊዜም ወጣ አጥንቶቹም እንደ ወንፊት ቀዳደሰ የተበሳሱ ሆነው ተገኙ ጌታም ዳሰሰውና ጤነኛ አደረገው ወደ ምድር ከብድም ሰደደው።

🍂 ከዚያም ወደ ላይ ወጥቶ ከፀሀ ከሰማይ በታች እስከ ሰባት አመት ኖረ። ዳግመኛም ወደ ምድረ ከብድ ተልኮ እንደ አምድም የተተከለ ሆኖ ሰባተረ አመት ቆሞ ኖረ። ወደ ሰማይም ሲመለከት ቅንድቦቹን አልከደነም ራሱንም ወደ መሬት ዝቅ አላደረገም ነበር እጆቹም ወደ ሰማይ ተዘርግተዋል። እነሆ ሰይጣንም በቁራ ተመስሎ መጣ አይኖቹንም ወደ ሰማይ ያንጋጠጡ ሁለቱን አይኖቹን አንቁሮ አሳወረው። እርሱ ግን ምንም ሳያጓድል እስከ ሁለት ሳምንት ድረስ እንደ ቀድሞው በመትጋት ሲፀልይ ኖረ።

+🍂 ከዚህም በኃላ #ሚካኤልና_ገብርኤል መጥተው በፊቱ ቆሙ በሁለቱ አይኖቹ ላይም እፍ አሉበት ብርሀንም ተሰጥቷቸው እንደ ቀድሞው አዩ። ከሰማይ ታላቅ ኃይል ተሰጥቶሀልና ጠላቶችህን ትበቀላቸው ዘንድ ወደ ዝቋላ ሂድ አሉት ከዚያም መላእክት ከአጠገቡ ሄዱ። እርሱም ተነስቶ ወደ ዝቋላ ተጓዘ በጎዳናም ሲጓዝ ሶስት ሽማግሌዎች ከእንጨት ጥላ በታች ተቀምጠው አየ አባታችንም በአያቸው ጊዜ ልሰውራቸው ብሎ በልቡ አሰበ። እንርሱም ፈጥነው በእግዚአብሔር ዙፋን ተማጥነናልና ሶስታችንንም በጀርባህ እያዘልክ አንዳንድ ምእራፍ ሸኘን እንጂ አትተውን ብለው ተጣሩ። በመጣም ጊዜ ሁለመናቸውን ሽበት የከበባቸው የደከሙ ሽማግሎች ሁነው አገኛቸው አንደኛውንም አንስቶ በጀርባው አዘለው ወደ አንድ ምእራፍም አደረሰው ሽማግሌውም ከዚህ አሳርፈኝ አንተ ደክመሀል የማትበላ የማትጠጣ ስለሆንክ አለው አባታችንም ሽማግሌ ሆይ በምን አወቅከኝ አለ።

+ ሽማግሌውም ሂደህ ባልንጀሮቼን አምጣልኝ አለው ተመልሶ ሁለቱ ወደአሉበትም ደርሶ ሁለተኛውን ሽማግሌ በጀርባው አዝሎ ወደ ቀደመው ሽማግሌ አድርሶ አብሮ አስቀመጠው ሶስተኛም ተመልሶ ሶስተኛውን ሽማግሌ አዝሎ ሁለቱ ወዳሉበት አድርሶ በአንድነት አኖረው፡፡ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስም እነዚያን አረጋውያን እናነተ ከወዴትናችሁ መአዛችሁ ልብ ይመስጣል እጅግም ደስ ያሰኛል አላቸው።እነርሱ ግን ተነስተው ቆሙ አንድ ሲሆኑ ሶስት ሶስት ሲሆኑ አንድ መሆናቸውን ገለጡለት የአባቶች አለቃ አብርሀም እንደ አየ።

🍂 ያንጊዜም የእግዚአብሔርን የጌትነቱን ክብር አየ የእሊያ አረጋውያንም ፊታቸው ተንቦገቦገ ከፀሀይና ከመብረቅ ብልጭታም ሰባት እጅ በራ አባታችንም በምስጢራት ጎርፍ የተዋጠ ሆኖ ፈራ ተንቀጠቀጠ በምድር ላይም ወደቀ። ህልምን የሚአልምም መሰለው ከዚያም ጌታችን አባታችንን አነቃውና መቶ አመት ያህል ስጋህን ሲነዱፉህ አጥንቶችህን ሲፍቁህ የኖሩ አጋንንትን ታጠፋቸው ዘንድ ወደ ዝቋላ ተራራ ውጣ አለው።

እኔ እንደ ወሰድኩህ ባለማወቃቸው በባህር ውስጥ አለ በማለት በትእቢት ላይ ናቸው ሰባቱ ሊቃነ መላእክትም ይረዱሀል መባርቅትም በፊት በኃላ ሆነው ይከተሉሀል አለው።

🍂 ያን ጊዜ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ በመብረቅ ላይ ተጭኖ በረረ እነዚያ አጋንንት ወደአሉበትም ወረደ። ደመናትም ከበቡአቸው መላእክትም በእሳት ሰይፍ መተሩአቸው በመብረቅም አጨዱ አቸው አመድም ሆነው በነፋስ በተኑአቸው። የእነዚያም አጋንንት ቁጥራቸው ሰባት መቶ ሺህ እልፍ ከአንዱ ሺህ ነበር። ከዚህም በኃላ ጌታ ክርስቶስን የካዱ ወዳሉበት ወደ ምእራብ ሀገር ወሰደው። ነገስታቱና መሳፍንቱ መኳንንቱም በሚወጡበትና በሚገቡበት ጉዳና ላይ አቆመው 📍 ጌታችንም በዚች ጉዳና ብዙ መከራ ያገኝሀል ግን በርታ ታገስ ብሎት በዚያ ተወው። በዚያን ጊዜም የአርብ ንጉስ ጣዖታቱን አስይዞ መኳንንቱን ሰራዊቱን አስከትሎ በዚያች ጎዳና መጣ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስን በጎዳና ውስጥ በተገናኙት ጊዜ ጣኦታቱ ወድቀው ተሰባበሩ።

+ ንጉሱም አባታችንን በአየው ጊዜ አንተ ጠጉር ለባሽ ምንድነህ ሰው ነህን አለው።አባታችንም አዎን ክብር ያለው የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያው የሆንኩ ሰው ነኝ ብሎ ለከሀዲው ንጉስ መለሰለት። ንጉሱም ዳግመኛ አባታችንን በዚያ አይሁድ በሰቀሉት ታምናለህን አለው አባታችንም በሰው ፊት አምንበታለሁ።ስለ እኔ በተሰቀለው አላፍርበትም ስለ እኔ ብቻ የተሰቀለ አይደለም ስለ አንተና ከአንተ ጋራ ስለ አሉትም ነው እንጂ ንጉስ ሆይ የዘላለም ህይወትን ታገኛላችሁ እመኑበት አለው።

🍂 ንጉሱም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ተቆጣ ሰራዊቱንም ጠርቶ በፍጥረት እሳትን አንድዱ ለተሰቀለው ለናዝሬቱ ሰው ባሪያው ነኝ የሚለውን ጠጉር ለባሽ ወስዳችሁ ጨምሩት አላቸው። የእሳቱም ነበልባል በረጅም ዛፍ መጠን ከፍ ከፍ እስከሚል አነደዱ። አባታችን ግን ንጉሱና ሰራዊቱ ሁሉ እያዩት አልፎ በፈቃዱ ወደ እሳቱ ገባ። እሳቱም እንደወንዝ ውኃ ሆነ ሰረዊቱም እጅግ አደነቁ እኩሌቶቹም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ። ንጉሱም ሲያደንቁ በአየ ጊዜ ፈፅሞ ተቆጣ ከሰባ ሰባት አርበኞቹ ጋራ በቁጣ ተነስቶ ያደነቁትንና ያመኑትን አንገታቸውን ቆረጠ ።

📍 በዚያችም ቀን የተቆረጡ አርባ መቶ ሺህ ሆነው ተቆጠሩ።ንጉሱም የአባታችንን አንገት ሊቆርጥ ሰይፉን መዞ ተወርውሮ ሄደ። ያን ጊዜም ከመብረቅና ከነጎድጓድ ጋራ ታላቅ ንውፅውፅታ ሆነ ንጉሱንም ከሰራዊቱ ጋራ አጠፋው ከከሀዲው ንጉስ ጋራ የሞቱት ቁጥራቸው አራት ሺህ እልፍ ሆነ።

ጌታችንም አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስን ጠላቶችህንና የኔንም ጠላቶች አጠፋሁልህ አለው።አባተችን ግን በመብረቅ የሞቱትን ሬሳቸውን ነፍሳቸውንም መላእክተ ፅልመት ወደ ስቃይ ሲወስዱአቸው በአየ ጊዜ መድኃኒታችንን እሊህን ስሁታን ማርልኝ ሰው ስሁትና ከዳተኛ ነውና አቤቱ አንተ ግን መሀሪ ይቅር ባይ ታጋሽም ነህ አለው።አባታችንም ይህን ሲናገር ጌታችን ተሰወረ።

🍂 #አባታችን_ገብረ_መንፈስ ቅዱስም ከዚያ ሄደ ታላቅ ገደልም አገኘ እግሮቹንም በገመድ አስሮ በገደሉ ውስጥ ተዘቅዝቆ ተሰቀለ።ሰይጣንም መጥቶ ያቺን ገመድ ቆረጣት ወደ ታችም ተወርውሮ ወረደ።ቅዱስ ሚካኤልም ቀድሞ አባታችንን ያዘው በእግርህ ላቁምህ ወይም በራስህ አለው በራሴ እቆም ዘንድ ተወኝ አለው ትቶት ሄደ።

📍 በዚያም በራሱ ቁሞ በጥርሶቹም ደንጊያ ነክሶ እስከ ሰላሳ አመት ኖረ አንጀቱና ናላው ሁሉ እየፈሰሰ አልቆ መላ አካሉ እንደእንጨት ቅርፊት ሆነ። ከሰላሳ አመትም በኃላ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባታችንን ገብረ መንፈስ ቅዱስ እያለ ሶስት ጊዜ ጠራው። እርሱም እነሆኝ ጌታዬ አለ ጌታችንም እነዚያን ከሀዱዎች ምሬልሀለሁ ከዚህ ተነሳ አለው።ያን ጊዜ የነከሰውን ደንጊያ ትቶ ተነሳ።ጥርሱም ተነቅሎ በድንጊያ ተተክሎ ቀረ። ክንፎችም ተሰጥተውት እየበረረ ከእግዚአብሔር ፊት ደረሰ ጌታውንም ከማርክልኝ ከስጋቸው ጋራ ተነስተው በመጠመቅ ክርስቲያኖች ይሁኑ ብሎ ለመነው። መድኃኒታችንም በሽተኞችን ልትፈውስ ሙታንን ልታስነሳ ስልጣን ሰጥቼሀለሁ አሁንም ወደተገደሉት ሄደህ በመስቀል ምልክት በላያቸው አማትብ ህይወት መድኃኒት በሆነ ስሜም አስነሳቸው አለው።ያን ጊዜም በድኖቻቸው ወዳሉበት ሂዶ አስነሳቸው አጥምቆም ክርስቲያኖች አደረጋቸው ከእርሳቸውም ሄደ።

ከዚህ ዓለም የሚለይበት በቀረበ ጊዜ እነሆ
#የክብር_ባለቤት_ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_እነሆ_ተገለጠለት። ስሙን ለሚጠራና መታሰቢያውን ለሚያደርግ እስከ #አስራ_አምስት ትውልድ የምህረት ቃል ኪዳን ሰጠው።

የእድሜውም ዘመናት
አምስት መቶ ስልሳ ሁለት ሲሆን በሰላም በፍቅር አረፈ። ጌታችንም ነፍሱን ተቀበለ አቅፎም ሳማት
በመላእክትና በቅዱሳን ሁሉ ምስጋና አሳረጋት።

🙏 ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን 🙏

እኛንም በቅዱስ አባታችን
በአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አማላጅነት ይማረን 🙏
በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን፡፡ 🙏

______________________

58 - 2

ወልደሰንበት woldesenbet ቅዱስ ሚካኤል ፣ ጠባቂየ ።
Posted 1 year ago

+ 📍 #ኪዳነ_ምሕረት 📍 +
#የካቲት_16
🍂 ይህችም የከበረች እመቤታችን ልጅዋ ንጹሕ ሥጋዋን ተዋሕዶ ከብቻዋ ኃጢአት በቀር የሰውነትን ሥራ ፈጽሞ ስለእኛ መዳን ወዶ ያደረገውን መከራ ተቀብሎ ሙቶ ተነሥቶ ከዐረገና በአባቱ ዕሪና ከተቀመጠ በኋላ እርሷን እናቱን ማርያምን በደቀ መዝሙሩ ዮሐንስ ዘንድ ትቷት ነበር እነሆ ልጅሽ እርሱንም እነሆዋት እናትህ ብሎ አደራ እንዳስጠበቀው ።

📍 ከዚያንም ጊዜ ጀምራ እመቤታችን ማርያም ትጸልይ ዘንድ ያለ ማቋረጥ ወደ ልጅዋ መቃብር ሁል ጊዜ ስትሔድ ኖረች ይኸውም ጎልጎታ ነው ። አይሁድም በአዩዋት ጊዜ ቁጣንና ቅናትን ተመልተው በድንጊያ ሊወግሩዋት ወደዱ እግዚአብሔርም ከዓይናቸው ሠወራት ከዚህም በኋላ ዳግመኛ መጥታ በዚያ እንዳትጸልይ ተማክረው ከመቃብሩ ዘንድ ጠባቂዎችን አኖሩ ።

እርሷ ግን በየዕለቱ መሔድን አላቋረጠችም ጠባቆችም አያይዋትም የልጅዋ የጌትነቱ መጋረጃ ሠውርዋታልና መላእክትም መጥተው ያገለግሏታል ጌታችንም ዘወትር ይጐበኛታል የምትሻውንም ይፈጽምላት ነበር ።

ከዚህም በኋላ መላእክት ወደ ሰማይ አሳረጓትና
📍 #የጻድቃንን_ማደሪያዎች አሳዩዋት አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብም ወዳሉበት አደረሱዋት ከአዳም ጀምሮ እስከዚያ ዕለት በአካለ ነፍስ ያሉ አባቶች ሁሉ አንቺን ከሥጋችን ሥጋን ከዐፅማችን ዐፅምን ለፈጠረልን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የአምላክ ልጅ ከአንቺ ሰው በመሆኑ በአንቺ ድህነት አግኝተናል ከጥፋትም የሕይወት ወደብ ሆነሽልናልና እያሉ ሰገዱላት ።

ከዚያም ወደ ተወደደ ልጅዋ የእሳት መጋረጃ ወደተተከለበት ወደ ጌትነቱ ዙፉን አደረሷት ጌታችንም እጇን ይዞ
ወደ ውስጠኛው መጋረጃ አስገብቶ ከጌትነቱ ዙፋን ላይ አውጥቶ ከእርሱ ጋር አስቀመጣት ያዘጋጀላትንም ዐይን ያላየው ጆሮ ያልሰማው በሰው ልቡና ያልታሰበ ተድላ ደስታን ሁሉ ነገራት ።

ከጌትነቱ ዙፋንም በታች የእስራኤል ንጉሥ #አባቷ_ዳዊትን የነቢያትና የመላእክት ማኀበር እንደ ግድግዳ ከበውት በመሰንቆ ሲያመሰግን አየችው እንዲህም ይላል ልጄ ስሚ በጆሮሽም አድምጪ ወገንሽን የአባትሽንም ወገን ርሺ ንጉሥ ደም ግባትሽን ወዷልና እርሱም ጌታሽ ነውና ።

📍 ዳግመኛም #የሥቃይን_ቦታ ያሳዩዋት ዘንድ መላእክት ከዚያ ውሰዷት ለሰይጣንና ለሠራዊቱ በእርሱ ጐዳና ለሚጓዙ ሁሉ ወደተዘጋጀ ወደጨለማው ዳርቻ አደረሷት እመቤታችን #ማርያምም_ወዮልኝ_ወደዚያ_እንዳይመጡ_ለሰው_ልጆች_ማን_በነገራቸው አለች መልአኩም አመቤቴ ቡርክት ማርያም ሆይ

እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ይኖራልና ለአንቺም ከአንቺ በኋላም በቃል ኪዳንሽ ለሚታመኑ አትፍሪ አላት ከዚህም በኋላ ወደ ቦታዋ መለሷት ።

ከዚያንም ጊዜ ጀምራ እመቤታችን ድንግል ማርያም
#ስለ_ኃጥአን እጅግ እያዘነች ኖረች እንደ ዛሬይቱም የካቲት ዐሥራ ስድስት ቀን በጎልጎታ ቦታ ቁማ ወደ ልጄ እንዲህ ብላ ለመነች

📍 #ልጄ_ሆይ
በእግዚአብሔር አባትህ በክርስቶስ ስምህ
ከአንተ ጋርም ህልው በሆነ አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ አማፅንሃለሁ ዓለም ሁሉ ሊሸከምህ የማይችል ሲሆን ዘጠኝ ወር
ከአምስት ቀን በተሸከመችህ ማሕፀኔ አማፅንሃለሁ

📍 #ልጄ_ሆይ
ያለ ሕማም ያለ ድካም ከእኔ በመውጣትህ በመወለድህ በአሳደጉህ ጡቶቼ በሳሙህ ከንፈሮቼ በአቀፉህ እጆቼ
ከአንተ ጋር በተመላለሱ እግሮቼ አማፅንሃለሁ ።
በውስጡ በተኛህበት በረት በተጠቀለልክበት ጨርቅ አማፅንሃለሁ የምወድህ ልጄ ሆይ በልቡናዬ የለውን ሁሉ ትፈጽም ዘንድ የልመናዬን ቃል ሰምተህ ወደእኔ ትመጣ ዘንድ ወዳንተ ፈጽሜ እማልድሃለሁ ።

📍 #የብርሃን_እናቱ_እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም እንዲህ ብላ በጸለየች ጊዜ እነሆ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወረደ ከእርሱም ጋር አእላፍት መላእክት አሉ በዙሪያውም ሁነው ያመሰግኑታል ፤

📍 #እርሱም እናቴ ማርያም ሆይ ምን ላድርግልሽ አላት እመቤታችንም ለተወዳጅ ልጅዋ እንዲህ ብላ መለሰችለት

📍 #ልጄ_ወዳጄ ሆይ ጌታዬና ፈጣሪዬ አለኝታዬና መጠጊያዬ በእናቴ ማሕፀንም ሳለሁ ባንተ ጸናሁ አንተም ጠበቅኸኝ ሁልጊዜም ስም አጠራሬ አንተ ነህ ።
አሁንም ጸሎቴንና ልመናዬን ስማኝ ቃሌንም አድምጥ
እኔ እናትህ እኔም አገልጋይህ የምለምንህ ይህ ነው

- መታሰቢያዬን ለሚያደርጉ
- በስሜ አቢያተ ክርስቲያን ለሚሠሩ ወይም
- የተራቆተውን ለሚያለብሱ
- የተራበውን ለሚያጠግቡ
- የተጠማውንም ለሚያጠጡ
- የታመመውን ለሚጐበኙ
- ያዘነውን ለሚያረጋጉ
- የተከዘውንም ደስ ለሚያሰኙ ወይም
- ምስጋናዬን ለሚጽፉ
- ልጆቹንም በስሜ ለሚሰይም
- በበዓሌም ቀን በማኅሌት ለሚያመሰግን
#አቤቱ_ዐይን_ያላየውን_ጆሮ_ያልሰማውን_በሰውም_ልቡና_ያልታሰበውን_በጎ_ዋጋ_ስጣቸው ።

በአማላጅነቴም የሚታመነውን ሁሉ
ከሲኦል ነጻ አድርገው ከአንተ ጋር የደረሰብኝን
ረኃቡንና ጥማቱን መከራውን ሁሉ አስብ አለችው ።

+ + + + + + +

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንዳልሽው ይሁንልሽ
#የሰጠሁሽም_ቃል_ኪዳን እንዳይታበል በራሴ ማልኩልሽ አላት ።

+ + + + + + + + + +

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም
ጣዕሟን በአንደበታችን ፤ ፍቅሯን በልባችን ያሳድርልን
ጽኑ ቃል ኪዳኗ በአማላጅነቷ ከምናምን ከህዝበ ክርስቲያን ጋር ለዘላለም ጸንቶ ይኑር 🙏

ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሣሉት
ዲ/ን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ

61 - 0

ወልደሰንበት woldesenbet ቅዱስ ሚካኤል ፣ ጠባቂየ ።
Posted 1 year ago

መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ። ኤፌሶን 6፡12

12 - 1

ወልደሰንበት woldesenbet ቅዱስ ሚካኤል ፣ ጠባቂየ ።
Posted 1 year ago

+   #ተክለሃይማኖት ሆይ
+   ከፀሐይ እና ከጨረቃ ሥነ ፀዳል ይልቅ
+ በክርስቶስ ሥነ ጸዳል ለተዋበው ፊትህ
  ሠላም እላለሁ

22 - 2