Channel Avatar

ምሥራቀ ፀሐይ የመጻሕፍት ጉባዔ ቤት @UCOE5nJz4TbZIvr6SjFHREGA@youtube.com

8.5K subscribers - no pronouns :c

ይህ ቻናል የምሥራቀ ፀሐይ አቡነ ቶማስ መታሰቢያ የመጻሕፍት ትርጓሜ ጉባዔ ቤት ነው። ቻናሉ መስ


Welcoem to posts!!

in the future - u will be able to do some more stuff here,,,!! like pat catgirl- i mean um yeah... for now u can only see others's posts :c

ምሥራቀ ፀሐይ የመጻሕፍት ጉባዔ ቤት
Posted 1 week ago

ዘመን አንተ ነህ (ዘመንሰ ለሊከ )
ዛሬ የእድሜያችን አንዱ ቀን ነው ፡፡ ዓመቱ ደግሞ ከእድሜያችን አንዱ ዓመት ነው፡፡
ማንም የሚጓዘው ወደ እድሜ መዳረሻው ነው፡፡ ያለ ዓመት በዘለዓለማዊነት ለመኖር በአሁን መሥራት ግድ ነው፡፡
አሁን ራሱ እየኖርበት ያለው ሰዓት ነው፡፡ትናንት ታሪክ፣ አሁን ኑሮ፣ ነገ ተስፋ ናቸው፡፡
የአሁን የመኖር ሁኔታ ለነገው ዋዜማ ነው ዋዜማውም አይነታ ይሆናል የዘመን አይነታውም ዋዜማ ይሆናል ይህም ያልፋል ያማልፈው ዘመነ እግዚአብሔር ነው፡፡ አሁን የሚለወጠው ሰው ሲለወጥ ነው ያለዚያ ግን የዘመን ቁጥር ነው፡፡
የኛ ቤተ ክርስቲያን በአምስት ነገሮች ትገለጣለች።፦ ልጆቿንም ትመራለች፦
በሐዋርያዊ ትውፊት
በኦርቶዶክሳዊ አረዳድ
በኅብረታዊ ትርጉም
በመዳን ትምህርት መለኪያ
በተስፋ ነጽሮት
መጻሕፍትን እና የመጻሕፍት የሆነውን ሁሉ እንዲህ በነዚህ ትረዳዋለች።
የሌላ የሆነውን ደግሞ በዚህ አንጥራ ትለያለች ስትሻም ታወግዛነች።
በዚህ መርምራም ትቀበላለች፡፡
ከዚህ የተነሣ ማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ ሰዉ ሁሉ የእምነቱ መለኪያ ማጥሪያ ወንፊት ሊኖረው ይገባል።
ያለፈው እና የሚመጣው ዘመን ትይዪ ናቸው፡፡
ቤተ ክርስቲያናችን የሚመጣው ዘመን ቅዱስ ነው ያለፈው ዘመን ግን ርኩሥ ነው ብላ አታስተምርም።
ምክንያቱም የተኖረበትን ዘመን እንጂ ያልተኖረበትን ዘመን በሰንሰለታዊ ቅብብሎሽ በሕይወት ፈተና ተፈትና ገና ስላልተቀበለችው ነው።አዝማነ መንግሥተሰማያትን ግን በተስፋ ቅድስና ደጅ ትጸናለች፡፡
ስለሆነም ሁሌም የቀደመው ታሪክ ክፉውም ሆነ በጎው መምህራችን ነው።
ትናንት እና አሁን ለኛ ምክርም ተግሣጽም ነው
ዕውቀት እና መረዳት
መረዳት እና እምነት
እምነት እና ሥራ
ሥራ እና ተስፋ፦ ዘመንን ያለፈ ዘመነኛ ያደርጋል፡፡ " ከእናንተ ጋር ተመርጣ በባቢሎን ያለች ቤተ ክርስቲያን ልጄም ማርቆስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።"
1ኛ ጴጥ 5፥13
ከትናንት የማይማር ትናንት ብቻ ነው፡፡
ትናንት መሠረት፣ ዛሬ ግድግዳ፣ ነገ ጣሪያ ነው፡፡

43 - 1

ምሥራቀ ፀሐይ የመጻሕፍት ጉባዔ ቤት
Posted 1 month ago

የኔታ መዝገበቃል
ህጻናት ላይ የምትሰራ ሃገር ራሷን ትገነባለች ህጻናት ላይ የማትሰራ ሃገር ራሷን ታፈርሳለች" መምህር መዝገበ ቃል /የወለህ ነቅዓ ሒወት የአራቱ ጉባኤ ቤት መምህር

ሰቆጣ፣ ሐምሌ 23/2016 ዓ.ም (sekota ketema communication) በዋግ ኽምራ ሃገረ ስብከት የወለህ ነቅዓ ሒወት የአራቱ ጉባኤ ቤት ከሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በዋግ ስዩም አድማሱ ወሰን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለተማሪዎች የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት እየሰጠ መሆኑን የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት አስታወቀ።

የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት ሲወስዱ ተገኝተን ካነጋገርናቸው ተማሪዎች መካካል የ8ኛ ክፍል ተማሪ ታምር ግርማ የወለህ ነቅዓ ሒወት ጉባኤ ቤት በሂሳብና በእንግዘኛ የትምህርት አይነቶች የማጠናከሪያ ትምህርት መሰጠቱ ጊዜየን በአልባሌ ቦታ እንዳላሳልፍ ከማድረግ ባለፈ ቀጣይ ዓመት በክልል ደረጃ ለሚሰጠው የሚኒስትሪ ፈተና እንድንዘጋጅ ያግዘናል ብላለች፡፡

ሌላው የአምስተኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ተማሪ ተዋሕዶ ሃይማኖት ከአለማዊ ትምህርት ጎን ለጎን መንፈሳዊ ትምህርቶችን እንድንማር ምቹ ሁኔታ መፈጠሩ የቤተ-ክርስቲያኗን እውቀት እንድንቀስምና በሥነ-ምግባር ታንፀን ከአሰብነው አላማ እንድንደርስ ይረዳናል ብሏል፡፡

በተለይም ክርስቲያናዊ ስነ ምግባር መማራችን መልካም ያልሆኑ ስነ ምግባሮችን አስወግደን መልካም ስነ ምግባር እንድንላበስና በአለማዊ ትምህርታችንም ጠንክር እንድንማር አግዞናል ሲሉ የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት የሚወስዱ ተማሪዎች ተናግረዋል፡፡

በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የማጠናከሪያ ትምህርት እየሰጠ የሚገኘው የ4ኛ አመት የዩኒቨርስቲ ተማሪ የሆነው መምህር ያሬድ ጣምተው ህፃናት ነገን አውቀው ዛሬ ላይ በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ የማጠናከሪያ ትምህርት እየሰጠሁ ነው በማለት ገልጿል፡፡

‹‹በጎነት ለራሱ ነው› ያለው መምህር ያሬድ የማጠናከሪያ ትምህርት ከመስጠት ባሻገር 6ኛና ለ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና የሚያዘጋጁ ጥያቄዎችንም በመሥራት የበኩሌን አሻራ እያሳረፍ ነው ብሏል፡፡

በዋግ ኽምራ ሃገረ ስብከት የወለህ ነቅዓ ሒወት የአራቱ ጉባኤ ቤት መምህር የሆኑት መምህር መዝገበቃል ገ/ሕይዎት ጉባኤ ቤቱ የቤተ-ክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የሚያስጠብቁ ደቀ መዛሙርትን ከማፍራት ባሻገር ከሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የክፍል ደረጃቸው ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ለሆኑ ተማሪዎች የክረምት የማጠናከሪያ እየሰጠን ሲሆን አላማውም የነገ ሃገር ተረካቢ የሆኑ ህጻናት አልባሌ ቦታ እንዳይውሉና የክረምት ጊዜያቸውን በትምህርት እንዲያሳልፉ ለማድረግ ነው ብለዋል።

"ህጻናት ላይ የምትሰራ ሃገር ራሷን እየገነባች ነው ህጻናት ላይ የማትሰራ ሃገር ራሷን እያፈረሰች ነው" ያሉት መምህር መዝገበ ቃል ነገ ራሱን፣ ቤተሰቡን፣ ማህበረሰቡን ብሎም ሃገሩን የሚጠቅም ትውልድ ለመገንባት ህጻናትን በእውቀትና በስነ-ምግባር ኮትኩቶ ማሳደግ አስፈላጊ በመሆኑ ህጻናት ላይ ሥራ እየሰራን ነው ሲሉ ገልጸዋል።

የግብረ ገብነት ትምህርት መማር ቤተሰብንና ጎረቤትን ከማክበር ይጀምራል ያሉት መምህር መዝገበቃል ከኢትዮጵያ አልፎ ለዓለም የሚተርፍ ትውልድ ትውልድ ለማፍራት ህፃናትን በስነ-ምግባር አንፆና ገንብቶ ማሳደግ ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በስነ-ምግባር የተባላሸ ትውልድ ቤተሰቡንም ሆነ ሃገሩን የወላድ መካን ያደረገ በመሆኑ ከትውልዱ ያጣነውን መልካም ሥራ ለመመለስ የግብረ ገብ ትምህርት ለመስጠት ተገደናል ብለዋል፡፡

በሒሳብ ፈጠራ ችሎታው የተራቀቀና ሃገር በቀል የሆነው የግዕዝ ቋንቋ ያወቀና በሁሉም የትምህርት አይነት ውጤታማ የሆነ ትውልድ መገንባት አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ትውልድ የመገንባቱ ሂደቱ ዛሬ ተጀምሮ ነገ የሚቆም ሳይሆን የዘወትር ተግባር ሆኖ የሚቀጥል በመሆኑ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል በማለት የአራቱ ጉባኤ መምህር የሆኑት መምህር መዝገበቃል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ቤት ኃላፊ አቶ ታምሩ ካሳሁን በከተማ አስተዳደሩ ባሉ ትምህርት ቤቶች በልዩ ሁኔታ 6ኛ፣ 8ኛና 12ኛ ክፍል ክልላዊና አገር አቀፍ ተፈታኝ ተማሪዎችና በ2016 የትምህርት ዘመን ክፍተት ያለባቸውን ተማሪዎች በመለየት በ2017 የተሻለ የትምህርት ዝግጅት እንዲኖራቸው ከ8 መቶ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት እየሰጠን እንገኛለን ብለዋል።

የማጠናከሪያ ትምህርቱ አላማ ተማሪዎች
ቀጣይ የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ለማድረግ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ የመጣውን የትምህርት ጥራት ለማሻሻል ታሳቢ ያደረገ ነው ሲሉ አቶ ታምሩ ገልጸዋል።

ትምህርት ተቋሙ የማጠናከሪያ ትምህርት የሚሰጥ የሰው ሃይል በማስተባበርና የተለያዩ ግብአቶችን በማሟላት የመማር ማስተማር ሥራውን ያስጀመሩ መሆኑን የጠቆሙት ኃላፊው የዚህ እድል ተጠቃሚ ያልሆነ ተማሪዎች ከዚህ ሰዓት ጀምሮ የማጠናከሪያ ትምህርቱን መውሰድ ይኖርበታል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
#በጌትነት አጉማስ

132 - 1

ምሥራቀ ፀሐይ የመጻሕፍት ጉባዔ ቤት
Posted 1 month ago

ሰው ምንድን ነው???
በዓለምስ ምስጢራዊዉ ቦታ የሚባለው ማን ነው?? በዓለም መካነ ምስጢር የሚባለው፣ ከሰው አእምሮ መልቶ የፈሰሰው እደ እግዚአብሔር ነው ፡ በፈጣሪው ፡ እጅ፡ ደግሞ ፡ ከአፈር ፡ እንደ ተፈጠሩ ፡ ግኡዛን ፡ ፍጥረታት፡ ጠጠር ፡ ብረት፡ እሳር ፡ ቅጠል ፡ ወርቅ ፡ብር፡ ነፍሳት፡ ሳይሆን ። በአርአያ እግዚአብሔርና፡ በአምሣሉ ፡ የተፈጠረ፡ ፍጹም ፡ባለ አእምሮ ፡ የምስጢር ፡ተካፋይ ፡ የሆነ ፡ ሰው አለ፡በእርግጥ ብዙ የምስጢር ማሕበራት የምስጢር ቦታዎች ቢኖሩም ሰው እንጅ እግዚአብሔር አልሰወራቸውም ሰው ግን እግዚአብሔር የሠወረው ። ሞሳድና ሲአ ኤ በስለላ። የዚህ ዓለም ጠቢባን ፡ አንዱ ጥርሱን ፡ አንዱ ሆዱን ፡ አንዱ ቆዳውን ፡ ተካፍለው ያልደረሱበት ፡ ፍኖተ_ ነፋስ ነው ። የሰው፡ ደግሞ፡ የምስጢራዊነቱ ፡ ቦታ ፡ የነፍሱ ፡ ዓለምነት ፡ ነው። ለዚህኮ ነው፡ እንኳን ፡ሰይጣን ፡ሰው ፡በሰው ፡ሲቀናና ፡የሚኖረው ። ዳዊትም፣ በመደነቅ ፡ እግዚአብሔር ፡ጆሮውን ፡ዘንበል፡ አድርጎ ፡ሀሳቡን፡ የሚሰማለት ፡ሰው ፡ምንድን ፡ነው?? ታሰበው ፡ዘንድ ፡ሰው ፡ምንድን፡ ነው? ሀሳቡን፡ የሚፈፅምለትስ፡ ሰው፡ ምንድን፡ ነው?? ፀሐይ ፡ነዳጅ ፡ሙላኝ ፡ሳትል ፡የምታበራለት፡ ሰማይ፡ የማያረጅበት ።ንቦች ባንድ፡ ቀፎ ፡ተሰባስበው ፡ማር ፡የሚሸምኑለት፡ እንሥሣት እሳር፡ ተመግበው ፡ወተት ፡የሚያፈልቁለት ፡ ምድር፡ የአበባ፡ እድሜዋን ፡የምትገብርለት ፡አንዱ ፡ ዘመን ፡እንዳይሰለቸው፡ ወደ ሌላው፡ ዘመን ፡የሚያሸጋግረው፡ ዘመን፡እንደ ከራድዮ የሚታደስለት ። ካለመኖር ፡ወደመኖር ፡ከዘርና ፡ከደም ፡ወደ ጽንስ፡ ከፅንስ ፡ወደ ህጻንነት፡ ከህጻንነት ፡ወደ ወጣትነት፡ ከወጣትነት ፡ወደ አባትነት። ከሕይወት ፡ወደሞት ፡ከሞት፡ ወደሕይወት ፡ ከዚህ ዓለም ፡ ወደ ገነት ፡መንግሥተ ሠማያት ። የሚያጓጉዘው ።የፈጣሪው ፡የኇላ፡ ደጀን ። ለአካላቱ፡ መለዋወጫ ፡የሌለው፡ ድንቅ ፡ፍጥረት ፡ነው ።
ሰው፡ ደግሞ፡ ተሰርቶ ፡የሚያልቀው ፡በትምህርት፡ ነው።
፩ ለትምህርት፡ ያለን ፡ አስተያየት፡ ትክክለኛ ፡ከሆነ፡ ማናቸውም ፡የሕይወት ፡ችግር ፡ሊፈታ ፡ይችላል ።ሰው ከሙሉ ፡ የሠውነት፡ ደረጃ ፡የሚደርሰው፡ በትምህርት ነው ። ፡ጵላቶን እንዲህ፡ ይላል። ሰው ትክክለኛውን ትምህርት ያገኘ እንደ ሆነ ፡ ለስላሳና እግዚአብሔርን የሚመስል ፍጥረት ነው ። ትምህርት ያላገኘ እንደሆነ ግን በምድር ላይ ካሉት አራዊት ሁሉ የባሰ ነው። በማሰብ የደከሙ ሰዎች ለዓለም ህያው መሥዋእቶች ናቸው ። የሥራቸውን ነጸብራቅም የዓይን ግርዶሽ የጨለማው መብረቅ ፡ ዓይንን መጨፈን ፡ የዘመን የአካል ብሌት ። የእድሜ መጋረጃ ፡ አይጋርደውም።
፠ ሠውን ከሁለት ይከፍሉታል አንደኛው ዕለታዊው ቅጽበታዊው ሁኔታው ነው ። ሁለተኛው ግን በምኞቱ መሠረት የገዛ ራሱ ሥዕል አምሮ ሠምሮ ህፀፅ ጉድለት ሳይኖረው ተውቦ የሚታየው ነው ፡ከዚህ ካልደረሰ እረፍት ሰላም የለውም ። ይሔም ፡ኩፋሌ መንፈስ፡ ነው ፡ ፡
፠ ሰው ፡መሆን፡ ውድ ፡ነው፡ ፈጣሪ ፡የባሕርይ፡ ገንዘቡን፡ ተካፋይ ፡ በማድረግ ፡ የገዛው፡ለዚህ ነው ። እራሴን የገዛሁት ፡ ሲመስለኝ ፡ሌላ፡ከባድ ፡ዋጋ ፡የሚጠይቀኝ ። ዘመኔን በሙሉ እራሴን የምገዛበት መልካም ዋጋ ስፈልግ የምኖረው ። በዓለምም እራሳቸውን የሚሸጡ እንጅ የሚበዙት ። እራሳቸውን፡ የሚገዙ ፡ ስውራን፡ ባህታውያን ናቸው ። አይገኙም ።
፨ ከዚህ ዓላማ የሚያደርሱን፡ አንደኛው፡ ትምህርት ፡ነው። ሁለተኛው፡ ትምህርት፡ ነው። ሦስተኛውም ፡ትምህርት፡ ነው። እንደ እሥራኤላውያን ተጓዦች አምደ ደመና ፡ አምደ ብርሀን፡ አምደ እሳት፡ ሆኖ ይመራናልና ። እነዚያ አእማድ በሌሊትም በመዐልትም እየመሩ መዓርና ወተት ወደ ሚፈስባት አድርሰዋቸዋል ። እኛም ሁለት ስዕል አለን አንደኛው ። በዐይነ ሥጋ የምናየው የሲና በረሐ የአህዛብ ጦርነት ሲሆን በዐይነ ሕሊና የምናየው ደግሞ መዐዛ ገነት ጣእመ መንግሥተ ሠማያት ዝማሬ መላእክት ነው። የሠው ልጅ እውቀት ፡ቆራጥነት፡በእምነት ጽኑነት፡ ወይም በደስታ ቤተ መንግሥት በሚኖሩ። ሥልጣን ፡ብልፅግና ፡ክብር፡ ጤንነት፡ እንከን፡ የሌለው፡ ኑሮ ፡ለሚባሉ ፡ የመንፈስ ሀብታት፡ ቅጥረኛ ፡ ነው ። ነገር ግን ፡የሰብእናችን፡ ፍላጎቱን መቀደስና መባረክ ፡ካልተቻለ ፡ወደ ትዕቢትና ፡አመፅ፡ ማዘበሉ ፡ አይቀርም ። ሰብእናችን፡ የበጎ ፡ነገር ፡አፍቃሪና ተምሳሌት፡ የሚሆነው ፡ፍላጎቱ ፡መልካም ፡ሲሆን ፡ነው ።
፠ የሰው ፍላጎቱ መልካም ይሆን ዘንድ የማሰብ ምንጮቹ ምን ምን መሆን አለባቸው ???
፩ መጽሐፈ ስነፍጥረት ። አፈጣጠሩ አመጣጡን መረዳት
፪ ከቅዱሳት አምላካውያት መጻሕፍት ። ከመጻፍ ቃል አትውጡ ይላልና
፫ የአበው መገለጥና የአበው መሠረተ እምነቶች ናቸው።፨

76 - 7

ምሥራቀ ፀሐይ የመጻሕፍት ጉባዔ ቤት
Posted 1 month ago

ኦርቶዶክሳዊ ሰው የተማረው የሚረዳው የሚያደርገው በመወሰኛ ዐዋቂ ልቡ ነው። በዐዋቂ ልቡ በሕገ ልቡናነት ክሡታዊ እና ጠባይዓዊ እምነቱ አለ። ክፉ እና በጎን የምታውቅ ነፍሱ መወሰኛ ልቡ ናትና። "ወልቡ ለብእሲ መንፈሱ ይእቲ- የሰው ልቡ ነፍሱ ናት" ሃይ.አበ. ፳፭፥፳፮ እንዲል። በክሡታዊ እምነቱ ደግሞ ተግባረ ውስጥ እና ተግባረ አፍአን ይሠራል። ከልቡናው የተረፈውን አፍ ይናገረዋልና። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአይሁድን ከልቡናቸው አፍልቀው እነሆ ዓለሙ ሁሉ ተከተለው፤ እኛን የጾም ቆሎ የበዓል ዶሮ የሚለን የለም ብለው ስላደረጉት መጥላት፣ ቅንዐት፣ ምቀኝነት በገሠጸበት አንቀጹ "እስመ እምተረፈ ልብ ይነብብ አፍ ኄር ብእሲ እምሠናይ መዝገበ ልቡ ያወፅኣ ለሠናይት ወእኩይሰ ብእሲ እምእኩይ መዝገበ ልቡ ያወጽኣ ለእኪት- ከልብ የተረፈውን አፍ ይናገራልና መልካም ሰው ከልቡ መልካም መዝገብ መልካም ነገርን ያወጣል፤ ክፉ ሰውም ከክፉ መዝገብ ልቡ ክፉ ነገርን ያወጣል" ማቴ. ፲፪፥፴፭ እንዳለ ያልተረገዘ አይወለድም፤ ያልታሰበም አይነገርም። የልብ ደስታ ከፊት የልብ ኀዘንም በፊት እንደ ሚገለጸው ሁሉ፤ ከልብ የተረፈው ከአንደበት አይታጣም። "ደስ ያለው ልብ ፊትን ያበራል፤ በልብ ኀዘን ግን ነፍስ ትሰበራለች" ምሳ. ፲፭፥፲፫ እንደተባለ ሕዋሳተ አፍአ ለሕዋሳተ ውስጥ ሲታዘዙ ፊት ይበራል፤ ሕዋሳተ ውስጥ ለሕዋሳተ አፍአ ሲገዙ ደግሞ ነፍስ ትጠቁራለች። ለኦርቶዶክሳዊ ሰው እውነተኛው ርቱዕ ተግባረ እምነቱ የግለሰቡ ከልቡና መረዳት ወደ አርአያነት ሕይወት የመገለጥ ልዕልናው ነው። በዚህ ዓለም ለሱታፌ መንፈስ ቅዱስ የሚኖረውም እንደ ትምህርተ ቀኖናው በተመጠነ፣ በተለካ፣ በተወሰነ፣ በሚያድን ግለሰባዊ እና ኅብረታዊ የቀኖና ሕይወት ነው። ኅብረታዊ ቀኖና ማለት ከመወለድ እስከ መሞት ከዓመት እስከ ዓመት እንኖርበት ዘንድ በቤተ ክርስቲያን የጉባኤ አዋጅ የተደነገገው ክርስቲያናዊ ሕይወት ነው። ግለሰባዊ ቀኖና ማለት በግላችን ስለሠራነው የኀልዮ የነቢብ እና የገቢር በደል በአበ ነፍሳችን በኩል በሚታዘዝልን የንስሓ ሕይወት መመላለስ ነው።
ለኦርቶዶክሳዊ ሰው በወንጌላዊነት የተለካ የተመጠነ ሕይወት ርቱዕ ቀኖናዊነት ነው። ቢያጣም የማያንሰው ቢኖረውም የማይተርፈው አንዱ ላንዱ ረድኤተ ልቡና የሆነበት ቀኖና ነው። "የእነርሱ ትርፍ ደግሞ የእናንተን ጉድለት እንዲሞላ በአሁኑ ጊዜ የእናንተ ትርፍ የእነርሱን ጉድለት ይሙላ፡፡ በትክክል እንዲሆን እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ ብዙ ያከማቸ አላተረፈም ጥቂትም ያከማቸ አላጎደለም።" ፪ ቆሮ. ፰፥፲፭ አንዱ በከብት በጉልበት ለሌላው ይተርፋል። ሌላው ደግሞ በጾም በጸሎት ለሌላው ይተርፋል። በአንዱ ልቡና አንዱ በኅሊና ህልው ሁኖ ያስብበታል። ኦርቶዶክሳዊነት የኅሊና ህልውና፣ የክርስትና ህልውና ነውና። አንዱ በአንዱ በሐዋርያዊት ኅሊና፣ በፍቅረ መስቀል፣ በክርስቶስ ራስነት ይኖራል።

97 - 4

ምሥራቀ ፀሐይ የመጻሕፍት ጉባዔ ቤት
Posted 1 month ago

የጥንቱን ወደ አሁኑ የአሁኑን ወደ ጥንቱ።
ጥንታዊ የአብነት ትምህርት ቤት
፩ኛ.፦ከቤተ ቀጢን ጉባኤ ቤት ከዕብራይስጥ ወደ ግዕዝ ከሚተረጉምበት ጉባኤ ጀምሮ ሀገርን የሠሩ ምሁር አማኞች ተገኝተው ፍትህ ርትዕን አስፍነው ሀገርን አስከብረው ኑረዋል።ከእነ ዮቶር ጉባኤ በኋላ በታሪካችን የታወቀው የጎላው የአክሱም ቤተ ቀጢን ጉባኤ ቤት ነው።ቤተ ቀጢን ማለትም ህሊናቸው የቀጠነ፣ረቂቅ ነገር የሚመረምር፣የሰላ፣የመጠቀ፣ሲር ያለ ድምጽን የሚረዳ፣ቤት ማለት ነው።ከዚህ ጉባኤ ተምረው ወጥተው ሀገር የመሩ ትውልድን ያስተማሩ አበው በጣም አያሌ ናቸው።ለምሳሌ እነ፣እነ ጌዴዎንን፣እነ ሊቀ ካህናት ኤፍሬምን፣እነ አዛርያስን፣እነቅዱስ ያሬድን መጥቀስ ይቻላል።
፪ኛ.፦የቅዱስ ያሬድ ጉባኤ ቤት።ይሄ ጉባኤ በበዳግማዊ ምድራዊ ኪሩብ በሊቁ በቅዱስ ያሬድ ተጀምሮ ሁላዊ ሀገራዊ ሁኖ ትውልድ የቀረጸ የመጣ እስከ አሁንም ያለ ተመትሮ እያስተማረ ያለ ጉባኤ ቤት ነው።በማይቋረጥ የቀለም ልደት ሊቃውንቱ ተወልደውበታል።
፫ኛ.፦የወላዴ አበው አባ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞ ጉባኤ ቤት ነው።አንዱ የኢትዮጵያውያን አባቶች የቆብ ሐረገ ትውልድ የሚመዘዘው ከዚህ ጉባኤ ቤት ነው።ዕንጦንስ መቃርስን፣መቃርስ ጳኩሚስን፣ጳኩሚስ ቴዎድሮስ ሮማዊን፣ቴዎድሮስ አባ አረጋዊን፣አባ አረጋዊ ኢትዮጵያውያን አባቶችን በምንኩስና ወልደዋል።ይሄንን መሠረትነት ይዞ ሥርዓተ አስኬማ የሚፈጸመውም በዚሁ ገዳም ነው።በርካታ አባቶች፣ ቅዱሳት መጻሕፍት ስለሚገኙበት እና የጽህፈት ትምህርት ይሰጥበት ስለነበር ብዙ አባቶች ወደዚያ ጉባኤ ቤት እየሄዱ ይማሩ ነበር። ለምሳሌ፦አቡነ ኢየሱስ ሞዓ የመነኮሱትም የተማሩትም ከዚህ ነው።
፬.ኛ፦ጉባኤ ወላዴ አእላፍ ኢየሱስ ሞዐ ነው፡፡በማዕከለ ሀገር በተተከለው የሐይቅ ደብረ ነጎድጓድ ጉባኤ ቤት በርካታ አበው ተምረውበታል።በአንድ ወቅት ብቻ ስምንት መቶ ምሁራን ቅዱሳን አባቶችን ያስገኘ ጉባዔ ቤት።ለምሳሌ፦እነ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣እነ አቡነ ሠረቀ ብርሃን፣አቡነ በግዑ፣አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣አቡነ ሂሩተ አምላክ፣አቡነ ብንያሚን..ተጠቃሾች ናቸው።
፭ኛ፦ጉባኤ ወላዴ አእላፍ አባ መድኃኒነ እግዚእ‹ አድኃኒ እግዚእ› ጉባኤ ቤት ነው።ርዕሰ ሀገር ከሆነችው ከጥንታዊቷ ከአክሱም ከተማ ወጣ ብሎ በተተከለ ደብረ በንኮል ገዳም ብዙ ቅዱሳን ሊቃውንት ተምረውበታል።ለምሳሌ፦የአቡነ አሮን፣የአቡነ መርቆሬዎስ፣የአቡነ ዘካርያስ፣የአቡነ ገ/ክርስቶስ፣የአቡነ ዳንኤል ዘፀአዳ ፣አ.ሳሙኤል ዘቆየጻ፣ አ. ሳሙኤል ዘጣሬጣ፣ አ.አሳይ ዘማን እንዳባ፣ አ.ሳሙኤል ዘዋልድባ ፤ አ.ዮሐንስ ዘጉራንቋ ፣ አ.ታዴዎስ ዘባልተዋር፣አ.ያፍቅረነ እግዚእ ዘ ጉጉቤ..የመሳሰሉ ሀገር የሠሩ ትውልድ የቀረጹ አባቶች ተምረውበታል።
፮ኛ፦ጉባኤ ወላዴ አእላፍ አባ ኤዎስጣቴዎስ ነው።ይህ ጉባኤ በተለይም የጥንቱን፣ሀማሴን፣በቅላን፣ሀገረ ጉዛይን፣ባሕረ ነጋሽን፣ማዕበላን፣ ይዞ ያስተማረ ጉባኤ ነው።ለምሳሌም፦እነ አባ ፊልጶስ፣አ.አብሣዲ፣አ. መርቆሬዎስ፣አ.ማቴዎስ፣አ.በኪሞስ፣አ.ገ/አምላክ፣አ. ገ/ ኢየሱስ፣ አ.ገ/ መስቀል፣አ.ፄዋ ወንጌል፣አ.ማትያስ ቆዝሞስ፣አ.ያፍቅረነ እግዚእ፣ አ.ቴዎድሮስ፣አ.ሰይፈ ሥላሴ፣አ.ዮሐንስ፣አ.እንድርያስ..ተምረውበታል።ትውልድ ቀርጸው ሀገር ሠርተው አስረክበዋል።
፯ኛ፦ጉባኤ የወላዴ አዕላፍ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጉባኤ ቤት ነው።መሐል እና ደቡብ ኢትዮጵያን ባማከለ ስብከተ ወንጌልን ያስፋፉት አባት ያስተማሯቸው የወንጌል ልጆቻቸው የጉባኤው ፍሬ ናቸው።እነ አቡነ ኤልሳዕ፣አ.ዜና ማርቆስ፣አ.ቶማስ፣አ.ስምዖን፣አ.ተስፋ ሕፃን፣አ.ይትባረክ፣አ.ተስፋ ሥሉስ፣ አ.ክርስቶስ ቤዛነ፣ አ.መስቀል ሞዐ፣አ.ክርስቶስ ሞዐ፣አ.ኤዎስጣቴዎስ፣አ.ማርቆስ፣አ.ፊልጵስ፣አ.አድኃኒ፣አ. አኖሬዎስ፣ አ.ኢዮስያስ፣ አ.ማትያን፣ አ.ዮሴፍ፣ አ.ገ/ክርስቶስ፣አ.ታዴዎስ፣ አ.አኖሬዎስ ካልዕ፣ አ.ቀውስጦስ፣ አ.ዮሐንስ፣ አ.መርቆሬዎስ.የፈለቁበት ጉባኤ ቤት ነው።
፰ኛ፦የአባ በጸሎተ ሚካኤል ዘደብረ ጎል ጉባኤ ቤት ነው።በመካከለኛው ወርቃማው ዘመን ብዙ ሥራ ከሠሩ አባቶች አንዱ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ናቸው።ከዚህ ከደብረ ጎል ጉባኤ ቤት፦ አቡነ ያዕቆብ ግብፃዊ በ፲፪ ኖሎት በ፸፪ ቀሲሳን፣እነ አቡነ አሮን ዘዳሬትወይም አሮን መንክራዊ ተገኝተው የዕውቀት፣የወንጌል፣የጽድቅ ጨው ሁነው ሀገርን ትውልድን ቀድሰዋል።
፱ኛ.፦ጉባኤ ደብረ እገዚእ፣ጉባኤ ጋስጫ ነው።በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አስተማሪነት በንጉሥ ድልነዓድ ጊዜ በተተከለ ደብረ እግዚአብሔር ላይ የነበረው ጉባኤ ቤት ብዙ አስተዋጽኦ አድርጓል።ኋላም በደብረ ባሕራይ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ብዙ መጻሕፍት እየጻፉ አስተምረዋል።በጊዜው እነ አባ ጽጌ ድንግልም ጉባኤ ተክለው ሲያስተምሩ ከሰዓት ከሰዓት በወግዳ ሜዳ(ወተት ሜዳ)እየተገናኙ ያስተምሩ ነበር።
ይቀጥላል...
ኑ የጥንቱን ወደ አሁኑ የአሁኑን ወደ ጥንቱ እንመልስ። የንታ ገብረ መድህን

93 - 4

ምሥራቀ ፀሐይ የመጻሕፍት ጉባዔ ቤት
Posted 1 month ago

ሞት ርሥት ነው።አሟሟት ግን ውሳኔ ነው።
እንደ ሥውራን ቅዱሳን ወደ ብሔረ ሕያዋን ካልተወሰደ በስተቀር እስከ ጊዜው ድረስ ነፍስ ከሥጋ መለየቷ አይቀርም።
የዚህ ዓለለም የኑሮ ዘመን ሊያጥርም ሊረዝምም ይችላል መምሸት መንጋት ነው።
በፈቃድህ ለወደድኸው ላመንህበት ጉዳይ መሞት ግን የሰማዕትነት ውሳኔ ነው።
አማረም መረረም ሞት አይቀሬ ነው።በማይቀረው ሞት ላይ መሠልጠን ግን ክርስቶሳዊነት ነው።
ሕፃኑ ቂርቆስ እና እናቱ ኢየሉጣ ያደረጉት ይሄንን ነው።በፈቃዳቸው ሞትን ሠለጠኑበት ጥርስ የሌለው አንበሳ አደረጉት።ላመኑበት ተላልፈው ተሰጡለት።
ላለመሞት አንጥርም ብንጥርም አይቀርምና።ወስነን ላመንበት ለመሞት ግን እንጥራለን ሰማዕትነት ነውና።ከሞቱ አሟሟቱ ማለት ይሄ አይደል?
የሰማዕታቱ ከሞታቸው አሟሟታቸው ያስቀናል ምን ያህል ሞትን እንደናቁት ያሳያልና።ሕይወታቸው የሚሰብከን ይሄንን ነው።
ክርስቶስ በመስቀል ተሰቅሎ ደሙን አፍስሶ ምእመንን ሲዋሐድ አይተው ደማቸውን አፍስሰው ተዋሐዱት።በፈቃዱ መከራ ተቀብሎ ምእመንን ሲወሐድ አይተው ጭንቅ ጭንቅ መከራን ተቀብለው ተዋሐዱት።
ለሁሉ አምላክ ሁለንተናቸውን ሰጥተዋልና ምንም ያጡት ነገር የለም።ይሄው እኛ እንኳ ቅዱሳን ሰማዕታት ብለን በክብር እንጠራቸዋለን።
መከራ ላለመቀበል ጥረት ማድረክ የክርስቶስን መስቀል መግፋት ነው።ወይም ከሞት በኋላ ሕይወት የለም ብሎ መካድ ነው።
የጸናች ህሊና ግን ከሰማዕታቱ ጋራ አብራ ትኖራለች።

78 - 4

ምሥራቀ ፀሐይ የመጻሕፍት ጉባዔ ቤት
Posted 1 month ago

ሁሉም ወደ አብነት
በጦርነት ምክንያት የሕፃናት እድሜ ያለ ትምህት ለምን ያልፋል?
ባለፉት ዓመታት በተደረገውና በሚደረገው ጦርነት ምክንያት የሕፃናት እድሜ በሰቀቀን እና በሰቆቃ ከትምህርት ውጪ ሁኖ አልፏል።የመማር ጊዜያቸውን የጦርነት ዜና ብቻ እየሰሙ ማደጋቸው ለነገዋ ሀገራችን መልካም አይሆንም።
ይሄው ባይጠቅምም ቢጠቅምም ይማሩበት የነበረው ትምህርት ቤታቸው ዝግ ነው።አምና እንዲሁ በባዶው እንደከረሙ በሚመጣው ዓመትም እንዲሁ ያለ ትምህርት እንዳይከርሙ በከተማውም በገጠሩም በየአቆራቢያው የአብነት ትምህርት እየተማሩ እንዲከርሙና በከንቱ እድሜያቸውን እንዳያባክኑ እናድርግ ግዴታ መሆን አለበት።
ትምህርት ቤት እያለን ለምን ትምህርት ያቆማሉ? በዓላማ ትምህር ቤቶች ከተዘጉ በዓላማ ማስተማር አይሻልም።
ስለሆነም የነፍስ አባቶች፣መርጌቶች በየደብራቸውና በየሚያቀርባቸው ቦታ እንዲያስተምሩ እናወያይ።የሁሉም አስተማሪ ሰው ዓይን ከጥንተ ትምህርት ላይ እንዲሆን አስተማሪዎችን በሚቸግራቸው በመደጎሞ እናበረታታ።
ልጅ ያለው ሰው ሁሉ ነገን የሚናፍቅ ሁሉ የነገ ሕፃናት አብነት ትምህርት እንዲማሩ ድርሻው ሊወጣ ህሊናው ግድ ይለዋል። ቢያንስ የፊደል እጅ እግር ለይተው እንዲያነቡ ለኋላም ትምህርታቸው እንዲረዳቸው እንምከር።
ከተቻለም ከአብነት ትምህርት ብዙ በረከት ስላለው በዚያው ልሕቀት ሊያመጡ ይችላሉ።በሥነ ምግባር የታነጹ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰውን የሚያከብሩ ልጆች ይሆኑልናል።ሁላችንንም ስለሚመለከተን በየአካባቢያችን እናነቃቃ።
ጥንቱንም የትምህርት ምኒስተር ሁና ትውልድ ስትቀርጽ የኖረችው ቤተ ክርስቲያን ነበረች ናትም።ሰይፍ ቢመዘዝ ከአፎቱ ጥጃ ቢሳሳት ከእናቱ ነውና።ሕፃናቱን ወደ እናታቸው ትምህርት ቤት እንውሰዳቸው።
ካስተማርናቸው በትናንት አበርክቶት ይበረክታሉ፦
በሀገር አንድነት ነጻነትና ክብር ፣በመልካም አስተዳደርና የፍትሕ ርትዕ ሕግን በመሥራት፣ በትምህርት ዘርፍም ሙሉ ትምህርት፣ ፍጹም የግዕዝ ቋንቋን ከነ ፊደሉ፣በጤና አምስት ሺህ ዓመት የጤና አገልግሎት በመስጠት፣ በባህልና ማኅበራዊ ኑሮ ፣በኪነ ጥበብ፣ የስም አወጣጥ ከነ ምሥጢሩ፣ሥነ ፈለክ ከነ ጥቅሙ፣ በቅርስና ቱሪዝም፣በብዝሐ ሕይወት ጥበቃ፣ የዘመን አቆጣጠር፣ሥነ ጽሑፍ ከነጠባዩ ከነ ሙያው ፣ሚልየን ብራና መጻሕፍትን በመጻፍ ፣ኪነ ጥበብ በየዓይነቱ፣ ወግ ፣ቅኔ፣ፈሊጥ፣ሥነ ግጥም.... ምሥጢር ከነምልክቱ..ያበረከተው አብነት ትምህርት ነው። ልጆቻችን ይሄንን ካበረከተው ትምህርት ቤት ገብተው ይሄንን ይማሩ።
ምን አልባትም ይሄ የመጨረሻችን ሞት እንዲሆን እየጸለይን የነገ ልጆችን ለነገዋ ሀገር እና ቤተ ክርስቲያን እንዲደርሱ እጃችን ላይ ባለው ትምህርት ቤት እናስተምራቸው።

66 - 4

ምሥራቀ ፀሐይ የመጻሕፍት ጉባዔ ቤት
Posted 1 month ago

እንኳን ለሊቀ መለአክ ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በአል አደረሳችሁ
በዚችም ቀን ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ በሰማዕትነት መከራ ተቀበሉ ። ይህም ሕፃን ዕድሜው ሦስት ዓመት ሲሆነው ከሮሜ አገር ወደሌላ ሀገር እናቱ ይዛው ሸሸች በዚያም የሸሸችውን መኰንን አገኘችው ። ሰዎችም ነገር ሠሩባት ወደርሱ አስቀረባትና ስለ አምልኮ ጠየቃት እርሷም መኰንን ሆይ ዕድሜው ሦስት ዓመት የሆነው ሕፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እርሱን ጠይቅ አለችው ። ሕፃኑም ወደአለበት ጭፍራውን ልኮ ወደርሱ አስመጣው ሕፃኑንም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና አንተ ደስተኛ ሕፃን ሆይ እንዴት ነህ አለው ። ሕፃኑም መልሶ አዎ ለእኔ ደስታ ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ኀዘንና ልቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው መጽሐፍ ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏልና አለው እግዚአብሔር ኃይልና ንግግርን ሰጥቶታልና ብዙ ተናገረ በዚያም ያሉትን እስከ አስደነገጣቸው ድረስ ንጉሡን መኳንንቱንና ጣዖታቱን ረገማቸው ከብርታቱም የተነሣ አደነቁመኰንኑም በአፈረ ጊዜ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይ ታላላቆች የማይችሉትን ታላቅና አስጨናቂ የሆነ ሥቃይን አሠቃየው እናቱንም ከርሱ ጋር እንደ እርሱ አሠቃያት እግዚአብሔርም ያለምንም ጉዳት ያነሣቸው ነበር ። ብዙዎች አሕዛብም ይህን አይተው አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አምነው በሰማዕትነት ሞቱ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበሉ ። በሕፃኑ ላይም የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አደረበት ። ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶችንም አደረገ ብዙዎች በሽተኞችንም አዳናቸው ። ከዚህም በኋላ መኰንኑ በታላቅ የናስ ጋን ውስጥ ውኃ ጨምረው በእሳት ያፈሉት ዘንድ አዘዘ የፍላቱም ድምጽ እንደ ክረምት ነጐድጓድ ሆነ ያን ጊዜም ፍርሀትና የሃይማኖት ጉድለት በእናቱ ላይ ደረሰባት ሕፃኑም ስለ እናቱ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ። ያን ጊዜ ጌታችን ልቧን ወደ ሰማይ አሳርጎ ለቅዱሳን ሰማዕታት የተዘጋጁ የብርሃን ማደሪያዎችን አየች ከዚህም በኋላ ጸናች እግዚአብሔርንም አመሰገነችው ልጅዋንም ልጄ ሆይ ከእንግዲህ አንተ አባቴ ነህ እኔም ልጅህ ነኝ አለችው ።ያቺ ከኔ የተወለድክባትም ቀን የተባረከች ናት አለች ወደዚያ ወደ ጋኑ ውስጥ በገቡ ጊዜም የውኃው ፍልሐት እንደ ንጋት ጊዜ ውርጭ ቀዘቀዘ ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የእሳቱን ኃይል አቀዝቅዞታልና ። ከዚህም በኋላ መኰንኑ ሥጋቸው ተቆራርጦ እስከሚወድቅ ድረስ በመቃጥን ውስጥ አድርገው እንዲጐትቷቸው አዘዘ ከእግዚአብሔርም የታዘዘ መልአክ አዳናቸው መኰንኑም በታላቅ ሥቃይ ያሠቃያቸው ዘንድ አስቦ እስኪመክር ድረስ በወህኒ ቤት ዘጋባቸው ያን ጊዜም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሕፃኑ ቂርቆስ ወርዶ አጽናናው አረጋጋውም ። ስሙን ለሚጠራና መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጠው ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ቂርቆስና በኢየሉጣ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን ።

118 - 5

ምሥራቀ ፀሐይ የመጻሕፍት ጉባዔ ቤት
Posted 5 months ago

እናታችን ለቅድስት ኪዳነ ምህረት በጸሎቷ ታስበን

111 - 11

ምሥራቀ ፀሐይ የመጻሕፍት ጉባዔ ቤት
Posted 1 year ago

እንኳን ለበአለ ጴጥሮስ ወጳውሎስ አደረሳቹ

120 - 21