in the future - u will be able to do some more stuff here,,,!! like pat catgirl- i mean um yeah... for now u can only see others's posts :c
#መሸጥ__የለመደ … ⁉️
ያዋጣልʔ አይኑን በለው!
#ሐኪሞች ደሞዝ ጭማሪ ጠየቁ
(ቤተመንግስቱ ይሸጥ!)
#አስተማሪዎች ኑሮ ተወደደባቸው
(አድዋ ሙዚየም ይሸጥ!)
#ሾፌሮች ቤንዚን ተወደደብን አሉ
(ስቴዲየም ይሸጥ!)
#ገበሬዎች ማዳበሪያ ተወደደብን አሉ
(ህዳሴ ግድብ ይሸጥ!)
#ሴቶች የበርበሬ ዋጋ አበደ አሉ
(የተተከለው 400 ቢሊየን ችግኝ ይሸጥ!)
#ተማሪዎች የታክሲ ዋጋ አማረረን አሉ
(እንጦጦ ፓርክ ይሸጥ!)
#ህጻናት የወተት ዋጋ ንረት አስለቀሰን አሉ
( ዲጂታል ኢትዮጵያ ይሸጥ!)
#ፖሊሶች ወንጀለኛ በዛ ሲሉ አማረሩ
(የድሮን ፋብሪካው ይሸጥ!)
#ነጋዴዎች ግብር ተቆለለብን እያሉ ነው
(ኮሪዶር ልማቱ ይሸጥ)
#ደላሎች የደንብ አስከባሪ ወከባ አላናቃንቅ አለን አሉ
የመንገድ ዳር ንጽህና ቤቶች ይሸጡ!
- - - - - ጠየቁ
- - - - - ይሸጥ!
- - - - - - አማረሩ
- - - - - - - ይሸጥ!
ኢትዮጵያ ሰላም ራቃት
(ኢትዮጵያም ትሸጥ!)
መሸጥ የለመደ … እናት ሀገሩን ሊሸጥ ይጋፋል!
#ZMan
871 - 34
ዛሬ ጠዋት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በኩል በይፋ የተከፈተውን #ID4Africa2025 በማስተናገዷ፣ #ኢትዮጵያ ኩራት ይሰማታል። ID4Africa ማኅበረ ኢኮኖሚያዊ ልማትን፣ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን እና ሰብአዊ ጥረቶችን የሚያበረታቱ ጠንካራ እና ኃላፊነት የሚሰማቸው የማንነት ዐውዶችን በመገንባት፣ የአፍሪካ ሀገራትን ለመደገፍ ቁርጠኛ የሆነ የፓን አፍሪካ እንቅስቃሴ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመክፈቻ ንግግራቸው ኢትዮጵያ ከተበታተነው የመታወቂያ ሥርዓት አልፋ፣ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ወደተጀመረው አስተማማኝ፣ ሁሉንም ያካተተ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ መሸጋገሯን አጽንዖት ሰጥተዋል። ለፋይዳ እስካሁን ከ15 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተመዝግበዋል። 90 ሚሊዮን ሰዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ እየተሠራ ነው፡፡ ፋይዳ ሁሉም ዜጎች - በተለይ ሴቶች፣ ወጣቶች እና የተፈናቀሉ ማኅበረሰቦች አስፈላጊ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ እንደሚያደርግ አሳውቀዋል።
እንደ ፋይናንስ፣ ጤና እና ትምህርት ባሉ ቁልፍ ዘርፎች የተቀናጀው ፋይዳ፣ 9.6 ትሪሊዮን ብር በዲጂታል ግብይት እንዲዘዋወር እያገዘ መሆኑንም ገልጸዋል።
#Ethiopia, through the Office of the Prime Minister, is proud to host #ID4Africa2025, which officially opened this morning in the presence of Prime Minister Abiy Ahmed. ID4Africa is a pan-African movement committed to supporting African nations in building robust and responsible identity ecosystems that drive socio-economic development, digital transformation, and humanitarian efforts.
In his opening address, Prime Minister Abiy Ahmed emphasized Ethiopia’s transition from a fragmented ID system to Fayda—a secure, inclusive digital ID initiative launched under the Digital Ethiopia 2025 strategy. With over 15 million people already enrolled and a target of 90 million, Fayda is connecting all citizens—particularly women, youth, and displaced communities—to essential services.
Integrated across key sectors such as finance, health, and education, Fayda is already enabling 9.6 trillion birr in digital transactions.
#PMOEthiopia
448 - 0
#ሀሳብ_ምጥን
#1. ኢትዮጵያ አዲስ ሪኮርድ አስመዘገበች፡፡
በትላንትናው እለት በአፍሪካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ 1ሺ500 ድሮኖች የተለያዩ ትርኢት ያሳዩ ሲሆን ይህም ትርኢት በአፍሪካ ትልቁ እንደሆነ ታውቋል፡፡ በትርኢቱ ላይ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) እና ም/ጠ ሚንስትር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ ትላልቅ ባለስጣናት ተገኝተዋል፡፡
#2. በትግራይ ክልል በድጋሚ የተቃውሞ ሰልፍ ተቀሰቀሰ፡፡
ከቀናት በፊት የደብረፂዎንን መግለጫ የሚቃወም ሰልፍ በማይጨው የተካሄደ ሲሆን፤ በትናንትናው እለትም ይህ የተቃውሞ ሰልፍ በራያ መሆኒ ከተማ ተካሂዷል፡፡ በሰልፉ ላይ የተለያዩ መፈክሮችን ይዘው የወጡት የመሆኒ ከተማ ነዋሪዎች፤ "የራያ ህዝብ ድምፅ ይከበር፣የደብረፂዮንን መግለጫ አጥብቀን እንቃወማለን፣ በመስዋዕትነት ስም ህዝብ መማገድ ይቁም" ሲሉ የደብረፂዮንን ቡድን ተቃውመዋል፡፡
#3. ፈረንሳይ በሴኔጋል የሚገኙ ወታደሮቿን አስወጣች፡፡
ከዚህ ቀደም የቡርኪናፋሶው ፕሬዝዳንት ትራዎሬ የፈረንሳይ ወታደሮችን ከሃገሩ ማስወጣቱ የሚታወስ ሲሆን፤ ይህንንም የትራዎሬን ተግባር ሴኔጋል አስቀጥለዋለች፡፡ በትናንትናው እለትም በዳካር ወደብ የሚገኙትን የፈረንሳይ ወታደሮችን ለሶስተኛ ጊዜ ማጣታቸውን በሴኔጋል የሚገኘው የፈረንሳይ ኤምባሴ አስታውቋል ፡፡
#4. ሩሲያ በዩክሬን ባገረገችው ጥቃት የዘጠኝ ሰዎች ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
ሞስኮ ዛሬ ማለዳ ዩክሬን በምትገኘው ቢሎፒሊያ ከተማ ሲጓዝ በነበረ የህዝብ አውቶብስ ላይ በተፈጸመች የድሮን ጥቃት ዘጠኝ ሰዎችን መግደሏን ኬቭ አስታውቃለች። ጥቃቱ የተፈፀመው የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በቱርክ ኢስታንቡል ውይይት እያደረጉ ባለበት መሆኑን ቢቢሲ፣አልጀዚራ እና ስካይ ኒውስን ጨምሮ በርካታ መገናኛ በዙሀኖች ዘግበዋል፡፡
51 - 0
Hasab Meda is One of Ethiopian News Channel