Channel Avatar

Yegna @UCJEDlaADDfbpjGvvKuQFNbw@youtube.com

187K subscribers - no pronouns :c

Yegna - meaning ‘ours’ in Amharic is a brand that inspires p


Welcoem to posts!!

in the future - u will be able to do some more stuff here,,,!! like pat catgirl- i mean um yeah... for now u can only see others's posts :c

Yegna
Posted 3 months ago

በቅርብ ቀን!! የየኛ ውሎ የሬዲዮ ፕሮግራም እንዳያመልጣችሁ!!

ቅዳሜ 4 ሰዓት በፋና ብሄራዊ ሬዲዮ እንዲሁም እሁድ 9 ሰዓት በፋና 98.1 ሬዲዮ ላይ ተከታተሉን!

#የኛ_ውሎ #ዛሬ_ለነገ #የኛ #bestfootforward #yegna #yegna_welo

19 - 0

Yegna
Posted 10 months ago

የኛዎች አዲስ ዜና አላቸው!! ዜናቸውን ሊያካፍሏችሁ፣ ያሏችሁን ጥያቄዎች ለመመለስ እንዲሁ ከናንተ ጋር ጭውውት ለማደረግ 'እሮብ መጋቢት 10 ከቀኑ 9 ሰዓት' ላይ በዩቲዩብ ላይቭ ቀጥታ መስመር ላይ ከች ይላሉ። እንዳያመልጧችሁ!

395 - 12

Yegna
Posted 3 years ago

https://youtu.be/zPLb67TGVrA

74 - 0

Yegna
Posted 3 years ago

በየኛ ድራማ ምዕራፍ አራት ላይ የምታውቋት ሳራ የአረብ አገር ኑሮዋን እና ወደ አገሯ ከተመለሰች በኋላ የምትመራውን ኑሮ አጠር አጠር ያሉ ከድራማው የተወሰዱ ቅንብሮችን ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ወደናንተ እናደርሳለን።

በተጨማሪም ሳራ ያጋጠሟትን የተለያዩ ፈተናዎች፣ ፈተናዎቹንም ለመወጣት የወሰደችውን መንገድ እንዲሁም ሌሎች ሃሳቦች ላይ ተዋንያኖቹ የሚያደርጉትን ውይይት በዩትዩብ ላይቭ ተከታተሉን።

ዩትዩብ ላይቭ እሮብ 12 ሰዓት ላይ እንዳያመልጣቹ!

1.8K - 87

Yegna
Posted 4 years ago

ምዕራፍ 4 ከአሁኑ ዕሁድ (ጥር 16 ) ጀምሮ ወደናንተ ይደርሳል።
የኛዎችም ዛሬ ልክ እንደትላንቱ በተመሳሳይ ሰዐት ከቀኑ 9:30 ጀምሮ በዩቲዩብ ላይቭ ቀጥታ መስመር ላይ ከች ይላሉ
እንዳያመልጣቹ!!

895 - 23

Yegna
Posted 4 years ago

ሰላም ሰላም! በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የኛ የሁላችንም ታሪክ አራተኛ ምዕራፍ የቲቪ ድራማ ዕሁድ (ጥር 16) ይጀምራል!!

ይህንንም በማስመልከት የምትወዷቸው የየኛ ተዋናዮች በዩቲዩብ ላይቭ - ነገ ሐሙስ ከ 9:30 ጀምሮ ከናንተ ጋር ቆይታ ያደርጋሉ ፤ ነገ በቀጥታ እስከምንገናኝ ያሏችሁን ጥያቄዎች ከታች ፃፉልን።

2.6K - 117

Yegna
Posted 4 years ago

በሴቶች ላይ የሚፈፀም ጾታዊ ጥቃት ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰት ነው። በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች የተለያዩ ሲሆኑ እነዚህ ጥቃቶች ሞትን ጨምሮ በሴቶች ላይ አካላዊ፣ ስነ-ልቦናዊ፣ እንዲሁም የስነ-ተዋልዶ ጤና ቀውስ ሊያስከትሉ ይችላሉ። የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ደግሞ ሴቶች ላይ የሚፈፀመው ፆታዊ ጥቃት እንዲባባስ ሲያደርግ፣ ወንዶችም የችግሩ ሰለባ
መሆናቸው አልቀረም። አለም አቀፍ ፆታዊ ጥቃትን ለመቃወም የሚደረገው የ16 ቀናት ንቅናቄ ዛሬ ጀምሯል።

የኛዎች ምን ይበጃል ታዲያ? ጾታዊ ጥቃት ቢደርስብኝ ወይም እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቢያጋጥሙኝ ምን ማድረግ
አለብኝ ብላቹ ጠይቃቹ ታቃላቹ? ይህንን ጭንቀት የሚያቃልል መረጃአዘጋጅተንላችሁዋል documentcloud.adobe.com/link/track?uri=urn:aaid:sc…ከዚህ በተጨማሪ t.me/kelelaguides/%E1%8A%A8%E1%88%88%E1%88%8B የልጆችን ወሲባዊ ጥቃት መከላከያና፤ ጥቃት የደረሰባቸውን መርጃ መመሪያን በማንበብ ተጨማሪ መረጃ ያግኙ።

15 - 1

Yegna
Posted 4 years ago

ፍቅር ህልሟ ነፍስ አልባ እንዳይሆን ጠንክራ ለመስራት ትሞክራለች፤ እስኪ እናንተም አስራዎቹ ላይ አልማችሁ ያሳካችሁት ወይ መሆን የተመኛችሁትን አካፍሉን።
#የኛ_ገፅ #የኛ #Yegna

574 - 18

Yegna
Posted 4 years ago

እስኪ የሃይስኩል ትዝታችንን እናውሳ... የአለምና ፍቅር የባንድ ምስረታ የሃይስኩል ትዝታችንን በወፍ በረር ቅኝት እንድናወሳ አድርጎናል። እስኪ የልጅነት ትዝታችሁን አጋሩን

552 - 23

Yegna
Posted 4 years ago

ዛሬ አለም አቀፍ የሴት ልጆች ቀንን እያከበርን ነው።
የሴት ልጆች የቤት ውስጥ የስራ ጫና ከልጅነታቸው ጀምሮ እንደሚጀምርና ይህም ጫና በጉልምስና እድሜያቸው እየጨመረ እንደሚሄድ ጥናቶች ያሳያሉ፤ ለምሳሌ እድሜያቸው ከ10-14 አመት ውስጥ ያሉ ሴት ልጆች በእነሱ እድሜ ክልል ካሉ ወንዶች ጋር ሲነጻጸር 50% በመቶ የሚሆነውን ጊዜያቸውን የቤት ውስጥ ስራ በመስራት ያሳልፋሉ ይህ ደግሞ በትምህርትና በአስተዳደጋቸው ላይ ምን አይነት ተጽእኖ እንደሚያስከትል መገመት አያዳግትም፤ ግን እስከመቼ? ተወያዩበት ሀሳባችሁን አካፍሉን

#የኛ_ገፅ #የኛ #IDG #Yegna

455 - 15