Channel Avatar

Yealem tube የዓለም ትዩብ @UCDF1-ET3nI4zusimI3lQ-ug@youtube.com

233K subscribers - no pronouns :c

የዚህ ዮትዩብ ገጽ ዋና አላማ የሰውን ልጅ ሁሉ ይጠቅማል ብለን ያሰብነውን ኢትዮጵያዊ ሥርዓትን


Welcoem to posts!!

in the future - u will be able to do some more stuff here,,,!! like pat catgirl- i mean um yeah... for now u can only see others's posts :c

Yealem tube የዓለም ትዩብ
Posted 8 months ago

እንኳን ለቅዱስ ዑራኤል አመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳቹ አደረሰን!
መልዐኩ ቅዱስ ዑራኤልና አገልግሎቱ በጥቂቱ
✍ ዑራኤል የሚለው ስም "ዑር"እና ኤል ከሚለው ሁለት ቃላት የተመሰረተ ነው ። ትርጉሙም ብርሃነ ጌታ አምላክ  ብርሃን ነው ማለት ነው።
✍ ቅዱስ ዑራኤል ከ7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ መብረቅና ነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ ነው።በመሆኑም መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበቁ ነጓድጓድ ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል። (መጽሐፈ ሄኖክ ፮፥፪)
✍ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ከወዳጇ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከእየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ግብጽ ስትሰደድ መንገድ እየመራ፤ ከእስራኤል ወደ ግብጽ ከዚያም ከእመቤታችን ጋር በሀገራችን ኢትዮጵያ እየመራ ያመጣት መልአክ ነው።
✍ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ ሆኖ በተሰቀለበት ጊዜ፥ክቡር ደሙ በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ በብርሃን ነሳንስ የረጨው እሱ ነው።
✍ ለነብዩ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋ ልቦና ያጠጣው፥ጥበብን ማስተዋልን የሰጠው የጠፉ መጽሓፍት በቃሉ አስታውሶ እንደገና ያጻፈው የረዳው መልአክ ነው(ዕዝ፲፫፥፴፱)
✍ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና ትዕዛዝ ብዙ ድርሰት የደረሱት መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ጽዋ ህይወት ስላጠጣቸው ነው።
✍ በዓላቱም በዓመት 3ናቸው
፩...ጥር። 22 በዓለ ሲመቱ፤
፪....መጋቢት 27 የጌታችንን ደም በዓለም የረጨበት፤
፫...ሐምሌ 21 እና 22 ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ።
✍ በጸሎቱ የተማጸነ ከእግዚአብሔር አምላክ በረከትን ፣ምህረትን የሚያሰጥ አዛኝ ጠባቂ ና የዋህ መልአክ ነው።በተለይም ህጻናትን የሚጠብቅ የሚለምኑትን ሁሉ የሚሰማ ፥ኃጢአተኞች ካሉበት ቦታ እኔን ላከኝ እያለ አምላኩን የሚማጸን አዛኝ የዋህ መልአክ ነው።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

26 - 0