Channel Avatar

Afro Media 🎥 @UCAcHIic-AHQZQR9YQMwyxUA@youtube.com

8K subscribers - no pronouns :c

we are here to deliver emazing videos by eritrean and ethiop


Welcoem to posts!!

in the future - u will be able to do some more stuff here,,,!! like pat catgirl- i mean um yeah... for now u can only see others's posts :c

Afro Media 🎥
Posted 5 months ago

ወጣት ሶፎኒያስ አስራትን ገድለው ተሽከርካሪውን ዘርፈው የተሰወሩ ወንጀል ፈፃሚዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
******************

ወጣት ሶፎኒያስ አስራትን ገድለው ተሽከርካሪውን ዘርፈው የተሰወሩ ማንነታቸው ያልታወቁ ወንጀል ፈፃሚዎችን በ48 ሰዓት ውስጥ ከዘረፉት ተሽከርካሪ ጋር በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ወንጀሉን የፈፀሙ አካላትን ለመቆጣጠር የምርመራና የክትትል ቡድኑ ሌት ከቀን በመስራት ውጤት ማምጣቱ ተገልጿል፡፡

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው አሽከርካዎች ማሰልጠኛ አካባቢ ወደ አቦ ቤተ-ክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ላይ ወጣት ሶፎኒያስ አስራት ተገድሎ ይገኛል፡፡

የወጣቱ መገደል ሪፖርት የደረሰው አዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ እና የክትትል ቡድኖችን በማዋቀር የገዳዮቹን ማንነት ለማወቅ ወንጀለኞቹን ህግ ፊት ለማቅረብ ወደ ስራ ይገባል፡፡

ሟች ወጣት ሶፎኒያስ መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ.ም ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ናሆም ሆቴል አካባቢ ከሌሊቱ 8፡00 ሰዓት ላይ ማንነታቸው የማይታወቁ ሦስት ግለሰቦችን በግል በተደረገ ስምምነተ ያለአፕልኬሽን ምዝገባ በኮድ 2 ቪትዝ አሳፍሮ ወደ ቦሌ ሚካኤል ለማድርስ መሄዱን ጉዳዩን ለመመርመር የተቋቋመው የምርመራና የክትትል ቡድን አባላት ባሰባሰቡት ማስረጃ ያረጋግጣሉ፡፡

ወንጀል ፈፃሚዎቹ ወንጀል ለመፈፀም አቅደው እና ተደራጅተው የትራንስፖርት አገልግሎት ፈላጊ መስለው ሹፌሩን በመቅረብ ካሳፈራቸው በኋላ አንገቱን በገመድ አንቀው በመግደል አስክሬኑን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ አካባቢ ወደ አቦ ቤተክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ላይ በመጣል አይነቷ ቪትዝ የሴሌዳ ቁጥር ኮድ 2A 93488 ተሽከርካሪ ጨምሮ ሁለት ሞባይል ስልኮችን ዘርፈው ይሰወራሉ፡፡

ፖሊስ ወንጀሉ ከተፈፀመበት ጊዜ አንስቶ ቀን ከሌት ባደረገው ብርቱ ክትትል ልዩ ልዩ ፖሊሳዊ ቴክኒኮችን በመጠቀም ወንጀል ፈፃሚዎቹ የሰረቁትን ተሽከርካሪ፣ ሦስቱን ዋና ወንጀል ፈፃሚዎች እና የሰረቁትን መኪና እንዲሁም ሶስት አባሪዎቻቸውን ጨምሮ መያዙን አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም ከወንጀል ፈፃሚዎቹ እጅ ላይ ባለቤታቸው የማን እንደሆኑ የማይታወቁ 7 የስልክ ሲም ካርዶችን ይዞ ምርመራው መቀጠሉን ጨምሮ ገልፆል፡፡

ምንም እንኩዋን ወንጀሉ በስውር የተፈፀመና ማንነታቸው የማይታወቁ ቢሆን በተደረገ ብርቱ ክትትል ወንጀል ፈፃሚዎችን በ48 ሰዓት ጊዜ ውስጥ በመለየት ሦስት ዋና ወንጀል ፈፃሚዎችንና ሦስት ግብራበሮቻቸውን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ጠቅሷል፡፡

በመጨረሻም ለዚህ ስራ ስኬታማነት ቀና ትብብር ላደረጉ አካላት አዲስ አበባ ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቦ የምርመራ ሥራው እንዳበቃ የፍርድ ሂደት ውጤቱን በቀጣይ ለህዝብ እንደሚገለፅ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
#seifuonebs #ethiopia #ethiopiannews #abelbirhanu #Eritrean #amharic #newethiopianmusic

0 - 0

Afro Media 🎥
Posted 5 months ago

♦ አሽከርካሪውን ገለው መኪናውን ቪትዝ (ኮድ 2 A 93488 ) ይዘው ተሰወሩ " 😭😭😱😱😱😱😭😭😢

ሶፎንያስ አስራት ይባላል የ24 አመት ወጣት ሲሆን ማክሰኞ ለሊት 8 ላፍቶ አካባቢ ሁለት ወንድ እና አንድ ሴት ኖሆም ሆቴል አካባቢ የሰፈሩ ስም ላፍቶ ቦሌ ሚካኤል ውሰደን ብለውት ጓደኞቹን ደርሼ መጣው ብሎ እንደወጣ በዛው ቀረ።

በማግስቱ እናቱ ስልኩ ላይ ስደውል አይሰራም ጓደኛው ጋር ስደውል ቦሌ ሚካኤል ብሎ እንደወጣ እና እንዳላገኘው ይነግራታል።

የፈለገ ነገር ቢፈጠር ከእናቱ ጋር ይደዋወል ነበር የልጇ ደብዛ መጥፋት ያስጨነቃት እናት ቦሌ ፖሊስ ጣብያ ሄዳ ትጠይቃለች የተመዘገበ ነገር ካለ እናሳውቅሻለን ይሏትና ተመልሳ ላፍቶ ፖሊስ ጣብያ ሄዳ ጠየቀች እነሱም ተመሳሳይ ነገር ነገሯት እና የአቃቂን ቃሊቲን ስልክ ይሰጧታል።

ስደውል ስልኩን ለሌላ ሰው ስጪ ብለው ያለውን ነገር ማለትም ወጣቱ መገደሉን እና አስክሬኑ ማሰልጠኛ አካባቢ እንደተገኘ እንዲሁም ለምርመራ ጳውሎስ እንደተወሰደ ይነግሯታል።

ዛሬ 5 ሠሀት አካባቢ አስክሬን ተቀብለው ወደ መኖርያ ቤት ወደ ላፍቶ ኮንደሚኒየም ወሰዱት ገዳዮቹ አልተገኙም መኪናውንም ይዘው መሠወራቸውን የሟች ሶፎንያስ የቅርብ ወዳጆች መረጃውን ለየኔታ ቲዩብ አድርሰዋል።
#Ethiopian #seifuonebs #abelbirhanu #Eritrean #ethiopianmusic #ethiopiannews

1 - 0

Afro Media 🎥
Posted 5 months ago

Free Bekele Bekele Weya በላይ በቀለ ወያ ፍቱት 💚💛❤
#Ethiopian #humanity #abelbirhanu ##seifuonebs #ethiopianpolitics #Ethiopian

5 - 0