Channel Avatar

ETH ADDIS @UC2fkc9ommqLD2rVsb5BAVxQ@youtube.com

72K subscribers - no pronouns :c

This is the official youtube channel of ETH ADDIS. ETH ADDI


Welcoem to posts!!

in the future - u will be able to do some more stuff here,,,!! like pat catgirl- i mean um yeah... for now u can only see others's posts :c

ETH ADDIS
Posted 4 years ago

ኢትዮጵያ ወደፊት ከምትጠብቃቸው ሚሊየኖች ወድ ልጆቿ አንዱ ከ2 ክፍል ወደ 5ኛ ክፍል የተሸጋገረው። 2ተኛ ክፍል እያለ 8 ክፍሎችን ፊዚክስና ሒሳብ ያስተምር የነበረው፤ የራሱን ሳተላይት በዚ ዕድሜው እየሠራ ያለው ከውዶችና ምርጦች ልጆቻችን አንዱ ሕፃን ቅዱስ። ነገ ኢትዮጵያን የሚረከቧት እነዚህ ምርጦች መሆናቸውን ሳስብና የእነዚህን ድንቅ የሆነ ጉዞ ማስቀረት የሚችል ምንም ምድራዊ ኃይል እንደሌለ ሳስብ ... ሕፃናት ሆይ አይዟችሁ ነገ ለእናንተ ብሩህ ይሆናል።
For more content, please subscribe to አንድሮሜዳ Andromeda by Doctor Rodase Tadesse www.youtube.com/channel/UCFKn...

326 - 13

ETH ADDIS
Posted 4 years ago

[ለሁላችሁም ምስጋናን በአክብሮት ስለማቅረብ]
🌞 መልካምና ቅን ልብ ያለው ሰው ሁሌም አንድ ሰው መልካም ነገር ሲሠራ ማበረታታት ልማዱ ነውና እጅግ መልካም የሆነ ሕሊና ስለነበራችሁ ሁላችሁም ደስታችሁን አክብሮታችሁን ስለላካችሁልኝ እኔም በታላቅ አክብሮትና ፍቅር ሁላችሁንም እጅ እነሣለሁ።

🌞 በፀሐይ ግርዶሽ ዙርያ ከዓመት በፊት በአንድሮሜዳ መጽሐፍ እና በማሕበራዊ ሚዲያዎች ከምርጡ ሳይንቲስት ከዶክተር ጌትነት ፈለቀ ጋር ስንናገርና ግርዶሹም እየተቃረበ ሲመጣ ብዙዎች ወዳጆቼ ባይሆንስ የሚል ሐሳብ ውስጥ በመግባት በጣም አስበውልኝ እንደነበር አሁን ተረድቻለሁ። ለዚህም ሐሳባችሁ የኢትዮጵያ አምላክ ዋጋችሁን ይክፈላችሁ።

🌞 ዕውቀት፣ እውነት ጨርሶ የማያቃቸው ጥቂቶች ግን ጨርሶ አይፈጠርም በማለት ካልተከሠተ ነቀፋን ትችትን ለማዝነብ ዝግጅት ላይ ነበሩ። ነገር ግን ከፀሐይ ጋር ያለን ቀጠሮ የማይዛነፍ በብዙ ምስጢር የተሰናሰለ በሳድሲት፣ በኃምሲት፣ በራብዒት፣ በሣልሲት፣ በካልዒት፣ በኬክሮስ የተቀመረ መሆኑን ከዕውቀት መራቅ ክፉ ነውና አልተረዱትም። ቢሆንም በዚህ አልከፋም ብርሃን ዕውቀትን እንዲያገኙ ለነርሱ ከመጸለይ በቀር።

🌞 ፀሐይ በጨረቃ ተጋርዳ ብትጨልምም መልሳ ከተጋረደችበት ወጥታ ብርሃኗን አንጸባርቃለች ዛሬም የኢትዮጵያ ምርጥ የአባቶቻችን ጥበብና ዕውቀት ሥልጣኔና ምስጢር እንዳይገለጽ ብዙ ጨለማዎች ተጋርደው ለዘመናት ቆይተው ነበር።

🌞 ነገር ግን ላስተዋለ ሰው ፀሐይ ኢትዮጵያችን ያላትን የራሷን ምስጢር እንዳታወጣ የጋረዷትን ጨለማዎች ሁሉ በከፍተኛ ፍጥነት አርቃ በልዕልና ብርሃኗ ላይ ለመቀመጥ ትላንት [ሀ] ወይም [፩] ብላ ቀመሯን ጀምራለች። ምልክቷንም አሳይታለች።

🌞 ፀሐይ ኢትዮጵያን የሚመጥናት ዕውቀት፣ ከፍታ፣ ሥልጣኔ፣ እውነት፣ እምነት፣ አመክንዮ፣ ፍቅር፣ ብርሃን ነው እንጂ ዝቅታ፣ ውርደት፣ ሐሰት፣ ድንቁርና፣ ማታለል፣ ጠብ ክርክር፣ ምቀኝነት፣ ጨለማ አይደለምና ከዚህ በኋላ ማንም ላይጋርዳትና ላያዋርዳት በከፍታ ሰገነቷ ላይ የምታበራበትና እንደ ጥንቱ ዓለምን በሥልጣኔ የምትመራበት ጊዜዋ ነው።

🌞 ፀሐይ ትላንት በጨለማዋ ሰዓት ከጎንና ከጎንዋ ሜርኩሪና ቬነስን አድርጋ በምሥራቅ አቅጣጫ ከፊት ለፊቷ ደግሞ ማርስን፣ ጁፒተርን፣ ሳተርንን አሰልፋ እንደታየች ፀሐይ ኢትዮጵያም በመከራዋ ሰዓት ምርጥ ልጆቿን የምትሰበስብበት ደጋፊዎቿን ከፊቷ የምታቀርብበት ሰዓቷ ነው።

🌞 ግርዶሹና ጨለማው ከፀሐይዋ ፊት ለፊት የተጋረደው ለጥቂት ሰዓት ነው። ብርሃኗ ግን ዘላቂ ነው። አሁንም ፀሐይ ኢትዮጵያችን ከፊት ለፊቷ የሚመጣባትን ፈተናን መሻገሯና ማብራቷ ለወዳጆቿ ደስታ ለሚጠሏት ግን አስደንጋጭ መርዶ ነው።

🌞 የሠኔ 14ቱ ግርዶሽ መቼም በምድራችን የማይደገም ነው ምክንያቱም መስመሩን የሠሩት ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ መሬት ብቻ ሳይሆኑ ሰመር ሶልስቲስ፣ ስካይ ክሮስ፣ የሚልክዌይ (የፍኖተ ሐሊብ) ማዕከል፣ ጋላክቲክ ፕሌንና ሁሉም ፕላኔቶች መሆናቸውና ሳክሪድ ጂኦሜትሪን በሰማይ ላይ መሥራታቸው በቀላሉ የሚታይ አይደለም፤ አስተዋይ ልብ ያለው ሰው አእምሮውን አስፍቶና በጥበብም ተራቅቆ ለሚመረምር በቅርብ ሊሆን ያለውን የዓለምን ሁኔታ በደንብ ይረዳበታል እላለሁ።

🌞 ሁላችሁንም እወዳችኋለሁ የዕውቀትና የእውነት ብቻ ተባባሪዎች እንድትሆኑ እንጂ የድንቁርናና የሐሰት ተባባሪ መቼም እንዳትሆኑ ወንድማዊ ምክሬን አቀርባለሁ።

305 - 49

ETH ADDIS
Posted 4 years ago

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል አደረሳችሁ!
Happy Easter!

19 - 0

ETH ADDIS
Posted 4 years ago

18 - 2

ETH ADDIS
Posted 4 years ago

3 - 0

ETH ADDIS
Posted 4 years ago

0 - 0

ETH ADDIS
Posted 4 years ago

4 - 0

ETH ADDIS
Posted 4 years ago

0 - 0

ETH ADDIS
Posted 4 years ago

ልና ሚስት ቤት ቀይረው አዲስ ሰፈር ገብተዋል ።
በነጋታው ቁርስ እየበሉ ሚስት በመስኮቱ በኩል ልብስ እያጠበች ያለችን ጎርቤቷን እየት አድርጋ «ልብስ አስተጣጠብ አችልም እዴ? እየው ቆሻሻ ልብስ ታሰጣለች !» አለችው ለባሏ! ባሏ ቀና ብሎ መስኮቱን አንዴ እየት አደረገና ምንም ሳይናገር ወደ ቁርሱ ተመለሰ ። ይሄ ነገር ለብዙ ቀናት ተደጋገመ !! አንድ ቀን ጦዋት ሚስት «ኧረ ጎርቤቴ አለፈላት ዛሬ ንፁህ ልብስ አሰጣች ። ለመሆኑ በትክክል ማጠብ ማን ያስተማራት ይመስክሃል?› አለች በአድናቆት ባል ከቁርሱ ቀና ብሎ ሚስቱን አየት አደረገና «ትላንት ማታ መስኮቱን ወልውዬ አፅድቴዋለሁ » ብሎ መለሰላት ።

👉ቁም ነገሩ ፦ በህይዎታችን ውስጥ ሁል ጊዜ የሌላውን ችግር የምናይበት መስኮት ከጉድፍ እና ከአቧራ የፀዳ መሆኑን ማወቅ አለብን! !
አለበለዚያ በእራሳችን ጉድፍ ሰዎችን ያለ እግባብ መውቀስ እንጀምራለን ።

8 - 2

ETH ADDIS
Posted 4 years ago

የዶክተር ያለህ
ከተዋወቅን ስድስት ወር ሆኖናል፡፡ በጣም እንዋደዳለን፡፡ ቁንጅናዋ በጣም ያስገርማል፡፡ ቶሎ እንድንጋባ ትፈልጋለች፡፡ እኔ ደግሞ ለትዳር የሚሆን የገንዘብ አቅም የለኝም፡፡ በምሠራበት ድርጅት የሚከፈለኝ ደመወዝ ለእኔም አይበቃኝም፡፡ በዚያ ላይ እሷ ሥራ የላትም፡፡ ሥራ ፈልጋ እንድትቀጠር፣ እኔም የተሻለ ነገር እስካገኝ ድረስ እንታገስ ብላትም ልትሰማኝ አልቻለችም፡፡ ቤተሰቦቿ እንድታገባ ግፊት እያደረጉባት ነው፡፡ ሃብታም ባል ሊያመጡላት እንደሚፈልጉ አውቃለሁ፡፡ ግን ቅድሚያ ለራሷ ምርጫ ሰጥተው እየጠበቋት ነው፡፡ ቶሎ የማልወስን ከሆነ እንዳትሄድብኝ ፈራሁ፡፡ አቅም ሳይኖረኝ የችግር ኑሮ ውስጥ መግባት ደግሞ አልፈለግኩም፡፡ በተጨማሪም ትንሽ የትውውቅ ጊዜ ብናሳልፍ ደስ ይለኛል፡፡ ግራ ገብቶኛል፡፡ ምን ልወስን?
ሳሚ ከአ/አ

7 - 4