Channel Avatar

Arada FM 95.1 - አራዳ ኤፍኤም 95.1 @UC179XdOUyhT5maadM-Nu3Uw@youtube.com

20K subscribers - no pronouns :c

This is the official Arada FM 95.1 YouTube Channel . Arada F


Welcoem to posts!!

in the future - u will be able to do some more stuff here,,,!! like pat catgirl- i mean um yeah... for now u can only see others's posts :c

Arada FM 95.1 - አራዳ ኤፍኤም 95.1
Posted 6 months ago

አራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ከአድማጭ ተከታዮቹ ጋር አንድ ዓመት

አራዳ ኤፍ ኤም 95.1 በተሟላ አቅም መደበኛ ስርጭቱን በይፋ የጀመረበትን 1ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በሃገር ውስጥና በውጭ ለሚገኙ አድማጮቹ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ሲያስተላልፍ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል።

አራዳ ኤፍ ኤም 95.1 መደበኛ ስርጭቱን በይፋ የጀመረው መጋቢት 4 ቀን 2015 ዓ.ም ነበር።

ጣቢያው አሁን ካሉት ይዘቶች በተጨማሪ ተደራሽነቱን ይበልጥ የሚያሰፉና ተቀባይነቱንም የሚያሳድጉ አዳዲስ ጉዳዮችን ለመጀመር ዝግጅቱን ያጠናቀቀ ሲሆን ከሬዲዮ በተጨማሪ በማህበራዊ ትስስር ገፆቹም አዳዲስ ይዘቶቹን ደረጃ በደረጃ የሚያቀርብ ይሆናል።

በመዝናኛ እና በቢዝነስ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው አራዳ ኤፍ ኤም 95.1 በህብረተሰቡ ውስጥ ያሉ በጎ ዕሴቶች የበለጠ እንዲጎለብቱ፣ በመተሳሰብ ላይ የተመሰረተ ኑሮ ለመምራት የሚያስችሉ ጉዳዮች ከፍ ብለው እንዲወጡ እንዲሁም መሰረታዊ ችግሮችን በነፃ ሀሳብ በማንሸራሸር የመፍትሄው አካል ከሚሆኑ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ቀጣይ ስራዎችን ይሰራል።

አራዳ ኤፍ ኤም 95.1 በመዝናኛው ዘርፍ በአድማጮች ዘንድ በሬዲዮ ድራማ ያለውን ሰፊ ፍላጎት ለመመለስ ላለፉት 40 ዓመታት በሬዲዮ ድራማዎቹ በሰራቸው ስራዎች ከሚታወቀው አንጋፋውና ተወዳጁ ደራሲ፣ አዘጋጅና ተዋናይ ኃይሉ ፀጋዬ ጋር አዲስ የሬዲዮ ድራማ ለማቅረብ የሚያስችል የሥራ ሥምምነት አድርጓል።

በቅርቡ የተለየ ሀሳብ ያለው ተከታታይ የሬዲዮ ድራማውን በአራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ማቅረብ እንደሚጀምር ስንገልጽ ታላቅ ደስታ ይሰማናል።

በተጨማሪም በመልካም ስራዎቻቸው በአድማጮች ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኙ ተፅዕኖ ፈጣሪ ፕሮግራም አዘጋጆች በአራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ዝግጅቶቻቸውን ማቅረብ ይጀምራሉ።

ይህ ደግሞ ጣቢያው በአጭር ጊዜ ውስጥ በአድማጮች ዘንድ ያገኘውን ተቀባይነት የበለጠ ያሳድገዋል ብለን እናምናለን።

በሀገራችን ሰፊ ደጋፊ ያላቸውና የተመረጡ የእግር ኳስ ጨዋታዎችንም በሬዲዮ፣ ቴሌግራምና በዩ ቲዩብ በቀጥታ በማስተላለፍ የስፖርት ቤተሰቦች ከአራዳ ጋር ውለው እንዲያመሹ፣ እንዲዝናኑ፣ ቁም ነገር እንዲጨብጡና እንዲሸለሙ ማድረጋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።

በመጨረሻም ባለፈው አንድ አመት መርጠው ላደመጡን ውድ አድማጮች፣ አብረውን ለሰሩ አምራችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች፣ የፋይናንስና የኢንሹራንስ ተቋማት፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከፍተኛ ምስጋናችንን እያቀረብን፥ በዚህ አጋጣሚ ሌሎችም ተቋማትና ድርጅቶች ከጣቢያችን ጋር እንዲሰሩ የአክብሮት ጥሪያችንን እናቀርባለን።


አራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ፤ ውለው የሚያመሹበት!

Telegram:t.me/Arada_Fm

Website:aradafm.com/

Facebook: www.facebook.com/aradafm95.1/

Youtube:youtube.com/@aradafm95.1

Tiktok:www.tiktok.com/@aradafm95.1

@Arada_Fm

45 - 0

Arada FM 95.1 - አራዳ ኤፍኤም 95.1
Posted 10 months ago

ለዓመታት በጥልቅ የእግር ኳስ የቀጥታ ሥርጭት ትንተና የምታውቁት እና የምትወዱት 4-3-3 ከፊታችን እሁድ ጀምሮ በአራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ወደ እናንተ መድረስ ይጀምራል።

አሰልጣኝ ሚሊዮን ጉግሳ እና ባልደረቦቹ በከፍተኛ ጉጉት የሚጠበቀውን የማንቸስተር ደርቢ ከጨዋታ በፊት ከሚሰጡ ሰፋፊ ትንተናዎች፣ በጨዋታው ጣልቃ ከሚቀርቡ ታክቲካዊ ዕይታዎችና ከጨዋታው በኋላ ከሚኖሩ ድህረ ጨዋታ ነጥቦች ጋር ይጠብቃችኋል።

ቆይታችሁን በአራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ላይ እንድታደርጉ ተጋብዛችኋል!

Telegram:t.me/Arada_Fm
Website:aradafm.com/
Youtube:youtube.com/@aradafm95.1
Tiktok:www.tiktok.com/@aradafm95.1
አራዳ ኤፍኤም 95.1 ፤ ውለው የሚያመሹበት!

3 - 1