Channel Avatar

Bisrat Mezmur Tube-ብስራት መዝሙር @UChQGXXJAB9AWlVUsf3ZWB_w@youtube.com

2.2K subscribers - no pronouns :c

Welcome to Bisrat Mezmur Tube -ብስራት መዝሙር , Subscribe to get


Welcoem to posts!!

in the future - u will be able to do some more stuff here,,,!! like pat catgirl- i mean um yeah... for now u can only see others's posts :c

Bisrat Mezmur Tube-ብስራት መዝሙር
Posted 1 day ago

"ኢየሱስ ትዳሬን ያጣሁበት ሥም፤ ከሥራ የተገፋሁበት ሥም ዓለም አንቅራ ትትፋኝ እንጂ ቢመች ባይመችም ስሙን መጥራት አላቆምም።" (አስቴር በዳኔ)

ብዙ ጊዜ ሚዲያ ላይ የሚዘዋወሩ ቃለ-ምልልሶችን አያለሁ። አንድ የታዘብኩት ነገር ምን እንደሆን ልንገራችሁ፦ "እግዘብሔርን ማመን፤እግዚአብሔር እንደዚህ አድርጎልኝ፤ ለእግዚአብሔር መታዘዝ፤ እግዚአብሄር የሚወደውን መስራት"
ምናምን ምናምን ብለው ሰዎች ሲናገሩ ከሥር ያለው ኮሜንት ጠቅላላ ሙገሳና አድናቆት ብቻ ነው። "አቤት ለእግዚአብሔር ያለው/ ያላት ፍቅር" ብለው ውዳሴ ያዘንቡላችኃል።

ሁሉም እግዚአብሔር ስትሉ ምንም አይላችሁም አብሮ ሁላ ሊል ይችላል።

ትልቅ ልዩነት የሚፈጠረውና የስድብና የትችት ናዳ የሚዘንብባችሁ ግን
....ኢየሱስ ... ያላችሁ እንደሆነ ነው። እና እንዲህ እላለሁ

ኢየሱስ ከሥሞች ሁሉ በላይ የሆነ ሥም
ኢየሱስ ከዘለዓለም ሞት የዳንኩበት ስም
ኢየሱስ ትዳሬን ያጣሁበት ሥም
ኢየሱስ ከብዙ ሥራ የተገፋሁበት ሥም
ኢየሱስ ጸጋና ሞገስ ኃይልና ጥበብ ብርታትና ተስፋ ያገኘሁበት ሥም ኢየሱስ
ዓለም አንቅራ ትትፋኝንጂ በሚመችም በማይመችም ሰዓት ስሙን መጥራት አላቆምም።

ኢየሱስ
ኢየሱስ
ኢየሱስ

በስምህ አላፍርም እወድሃለሁ አመሰግናለሁ

‪@BisratMezmur‬

3 - 0

Bisrat Mezmur Tube-ብስራት መዝሙር
Posted 1 week ago

#አስቸኳይ_መልእክት
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሁሉም ዞኖች ለምትገኙ የካውንስሉ አባላት

1 - 0

Bisrat Mezmur Tube-ብስራት መዝሙር
Posted 2 weeks ago

አንድ ነቢይ በፓትሮል መታጀቡ አይግረማችሁ፣ መታጀብ ከፈለጋችሁ ስራ ስሩ"


ነቢይ ኢዩ ጩፋ፤ ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ለተሰነዘረበት ቅሬታ በሰጠው ምላሽ፤ “አንድ ነብይ በፓትሮል መታጀቡ አይግረማችሁ፣ መታጀብ ከፈለጋችሁ ስራ ስሩ፣ የክርስቶስ አገልጋይ መጣ ሲባል ማርሽ ባንድ አይደለም ካላንደር ሁሉ ሊዘጋ ይችላል” ብሏል።
"ብታምኑም ባታምኑም በኢትዮጵያ ምድር በራሳቸው ጄት እየተንቀሳቀሱ የሚያገለግሉ አደገኛ ሰዎች ይነሳሉ" ያለው ነብይ ኢዩ፤ "ከዚህ በኋላ የሚኖሩ ፕሮግራሞች ከዚህ የበለጠ ይሆናሉ" ብሏል፡፡


ነቢይ ኢዩ ጩፋ በመቋጫውም፤ "የበሻሻው ዐቢይና የሾላው ነቢይ በተራ ጫጫታ አይጠፉም" ሲል ምላሽ ሰጥቷል፡፡
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ካውንስል ባወጣው መግለጫ፤ ፖሊስ አገልጋዮችን ከማጀብ እንዲታቀብ ያስጠነቀቀ ሲሆን፤ አንድን አገልጋይ በጦር መሳሪያ ማጀብ እንደ ወንጌል አማኝ በፍፁም ተቀባይነት የሌለውና ከአስተምሮት ውጪ መሆኑን አስታውቋል፡፡


‪@BisratMezmur‬

5 - 0

Bisrat Mezmur Tube-ብስራት መዝሙር
Posted 2 weeks ago

#በማይናማር በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የሟቾች ቁጥር ከ1 ሺህ ማለፉ ተገለጸ

#በማይናማር በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የሟቾች ቁጥር 1 ሺህ 7 መድረሱን እና ወደ 2 ሺህ 389 የሚሆኑት የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው እንዲሁም 30 የሚሆኑት የደረሱበት አለመታወቁን የአካባቢው ባለስልጣናት ገልጸዋል፡፡

የንብስ አድን ሰራተኞችም በፍርስራሽ ሥር የሚገኙ በህይወት ያሉ ሰዎችን ለማትረፍ ርብርብ እያደረጉ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በትናንትው እለት በሬከረተር ስኬል 7.7 በተመዘገበ ርዕደ መሬት የተመታችው ማይናማር፣ እስከ ዛሬ የዘለቀ ከፍተኛ ጉዳት ማስተናገዷ ተገልጿል፡፡

ርዕደ መሬቱ በታይላንድ ባንኮክ በፈጠረው ንዝረትም ህንፃዎች የተደረመሱ ሲሆን፣ 15 ሰዎች በፍርስራሽ ሥር መታፈናቸውን እና 100 ሰዎች ደግሞ የደረሱበት አለመታወቁ ተነግሯል፡፡

በአደጋው የማይናማር ሁለተኛዋ ትልቋ ከተማ በሆነችው ማንዳላይ ከ1 ሺህ 500 በላይ ቤቶች መውደማቸው መገለጹን ቢቢሲ ዘግቧል።

በዚህም ጎረቤት ሃግራት የነፍስ አድኑን ጥረት ለማገዝ ርብርብ እያደረጉ ሲሆን፣ ለዚህም የሚያግዝ የሰብኣዊ ድጋፍ እና ጊዛዊ ሆስፒታሎችም እየተዘረጉ መሆኑ ተነግሯል፡፡

‪@BisratMezmur‬

3 - 0

Bisrat Mezmur Tube-ብስራት መዝሙር
Posted 2 weeks ago

#ነቢይ ኢዩ ጩፋ በካውንስሉ ታግዷል

#ክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቸርች በካውንስሉ በምዝገባ ቁጥር 03111 የተመዘገበች የሃይማኖት ተቋም መሆኗ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ ቤተክርስቲያኒቱ የካውንስሉ አባል ስትሆን ልታከናውናቸው ከሚገቡ መመሪያዎችና ደንቦች መካከል አንዱ የካውንስሉ አባላት ስነ ምግባር መመሪያ ሲሆን በስነ ምግባር መመሪያው አንቀጽ 9.3 ላይ የስነ ምግባር ግድፈቶች ተበለው በዝርዝር የተገለጹትን ተግባራት በቤተክርስቲያኒቱ መሪ መፈጸሙን አረጋግጠናል።

በመሆኑም ጉዳዩ በካውንስሉ ሥነ መለኮት ኮሚሽን እና የሕግ ኮሚሽን ታይቶ በሚመለከታቸው አካላት የመጨረሻ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ የቤተክርስቲያኒቱ ፈቃድ ታግዶ የሚቆይ ሲሆን ሁሉም የካውንስሉ አስተዳደራዊ መዋቅሮችና የሚመለከታችሁ የመንግስት አካላት ይህንንና ከዚህ በኋላ የሚተላለፉ ውሳኔዎችን እንድታስፈጽሙ በግልባጭ ተመዝግቦላችኋል፡፡

‪@BisratMezmur‬

4 - 0

Bisrat Mezmur Tube-ብስራት መዝሙር
Posted 3 weeks ago

#የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን🙏

#የእናንተን የደጋጎች ምርቃት እና ፀሎት ሰምቶ በመንታ ልጆች ( ወንድ እና ሴት ) ባርኮኛልና እንኳን ደስ አላችሁ።

‪@BisratMezmur‬

17 - 0

Bisrat Mezmur Tube-ብስራት መዝሙር
Posted 3 weeks ago

የፕሮፌሰር ኤልሳቤጥ ወልደጊዮርጊስ ወልደዮሐንስ አጭር የህይወት ታሪክ
***************

ፕሮፌሰር ኤልሳቤጥ ወልደጊዮርጊስ ከእናታቸወ ወ/ሮ ዋካ ድንቄ እና ከአባታቸው ብላታ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ ግንቦት 1 ቀን 1948 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ።

ከአምስት ወንድሞቻቸው እና አንዲት እህታቸው ጋር በአዲስ አበባ ያደጉትና የቤተሰቡ የመጨረሻ ልጅ የሆኑት ኤልሳቤጥ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በናዝሬት ት/ቤት ተምረዋል።

በከፍተኛ ትምህርት ደግሞ በአሜሪካ ሞርጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚከስ ትምህርት ተከታትለው በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀዋል። በዚህ ሙያቸውም እዚያው አሜሪካ በተለያዩ ባንኮች አገልግለዋል።

በተለይ ለሥነ-ጥበብ እና ለታሪክ በነበራቸው ልዩ ዝንባሌ እንዲሁም እስክንድር ቦጎስያንን ከመሳሰሉ ሰዓሊዎች እና የጥበቡ ማኅህበረሰብ ጋር በነበራቸው የጠበቀ ወዳጅነት ወደ ጥበቡ ዓለም በመሳባቸው፤ ማስተርሳቸውን በሙዚየም ጥናት ከኒውዮርክ ዩኒቨርሲቲ፣ ዶክትሬታቸውን ደግሞ በሥነ-ጥበብ ታሪክ እና ሂስ ከኮርኔል ዩኒቨርሲቲ በ2000 ዓ.ም አግኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሥነ-ጥበብ ታሪክ ላይ በማተኮር ለዶክትሬት መመረቂያ ያካሄዱት ጥናት እና ምርምር እና ያዘጋጁት የመመረቂያ ጽሑፍ በ2011 ዓ.ም ‘Modernist Art in Ethiopia' በሚል ርዕስ ለታተመው መጽሐፋቸው ዋነኛው እርሾ ነበር።

ይህ በኦሃዮ ዩኒቨርሲቲ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትብብር ለህትመት የበቃው መፅሐፍ በርካታ አንባቢ ያተረፈና በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅናና ሽልማት የተቸረው ሰነድ ለመሆን በቅቷል።

ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁም ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናት እና ምርምር ተቋምን የመምራት ኃላፊነት ተረክበው ከ1996 እስከ 2002 ዓ.ም በዳይሬከተርነት አገልግለዋል።

በዚህ የኃላፊነት ዘመናቸው የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም የዳርፉርን ጉዳይ ጨምሮ ወሳኝ በሆኑ ዓለም እና ሀገር አቀፋዊ አጀንዳዎች ዙሪያ ጉባኤዎችን እንዲያሰናዳ አስችለዋል።

ተቋሙ ከዚያ ቀደም የነበረውን የረዥም ጊዜ ልምድ እና እውቀት መሰረት በማድረግ ይበልጥ እንዲደራጅ እንዲሁም ክብሩን እና የዕውቀት ሃብቱን እንዲያሳድግ ጉልህ ድርሻ አበርክተዋል።

በመቀጠልም በዩኒቨርሲቲው የቴአትር ጥበባት ማዕከል፣ የያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት እና የአለ ሥነ-ጥበብና ዲዛይን ት/ቤት ተቀናጅተው “እስክንድር ቦጎስያን የክወና እና የዕይታ ጥበባት ኮሌጅ" እንዲቋቋም በማስቻል ኮሌጁ ከተመሰረተበት ከ2001 እስከ 2004 ዓ.ም በዲንነት አገልግለዋል።

በተጨማሪም በአለ የሥነ-ጥበብና ዲዛይን ት/ቤት የፊልም እና የሥነ-ጥበብ ድኅረ ምረቃ ትምህርት ከፍልን በማቋቋም ሂደት የበኩላቸውን ሚና ተጫውተዋል። በዚሁ ትምህርት ክፍል በማስተማር የተማሪዎቻቸው የሥነ-ጥበብ እሳቤ፣ ዕውቀት እና ልምምድ እንዲዳብር የነበራቸው አስተዋጽኦ ከልዩ ሙያዊ አበርከቶዎቻቸው አንዱ ሲሆን፣ ይህንኑ ተግባራቸውን አሁን በተለያዩ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ከፍተኛ ደረጃ የደረሱ የቀድሞ ተማሪዎቻቸው በኩራት የሚመሰከሩት ዕውነት ነው።

ፕሮፌሰር ኤልሳቤጥ ለሀገሪቱ ብቸኛ የሆነው የዘመናዊ ሥነ-ጥበብ ቤተ-መዘክር ገብረ ክርስቶስ ደስታ ማዕከል መስራቾች መካከልም አንዷ ናቸው። ቤተ-መዘክሩ ከተቋቋመበት ከመስከረም 2001 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ዙሮች ሁለት ጊዜ በዳይሬክተርነት መርተውታል። በዚሁ ወቅት እንደተለመደው በርካታ ትዕይንቶችንም አዘጋጅተውበታል። ከእነዚህም መካከል በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ዕውቅና ያካበቱትን የትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ጁሊ ምህረቱን እና ዴንማርካዊ አይስላንዳዊውን አላፉር ኤልያሰንን ጨምሮ የስመ ጥር ሰዓልያን ሥራዎችን ጭምር ለህዝብ ዕይታ አቅርበዋል።

ፕሮፊሰር ኤልሣቤጥ ዘመናዊነት በኢትዮጵያ፣ ዘመናዊ ሥነ-ጥበብ እና ከተሜነትን ጨምሮ በተለያዩ ማህበረሰብ ተኮር ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ ሲምፖዝየሞች፣ ኮንፍረንሶች እና ውይይቶችን አዘጋጅተዋል።

ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ የባህል አምባ እየሆነች በመጣቸው በተባበሩት ዐረብ ኢምሬትስ የሻሮዣ ከተማ በሚገኘው ዓለም ዐቀፍ ጥናት ዩኒቨርሲቲ (Global Studies University) የአፍሪካ ኢንስቲትዩት የአሊ መዝሩዊ ቀዳሚ ከፍተኛ ፌሎ በመሆን ተቀላቅለዋል።

በተቋሙ የድኅረ ምረቃ እና የዶክትሬት ትምህርት ክፍል ምሥረታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉ ሲሆን፤ በተጓዳኝ የሂውማኒቲስ ትምህርት ክፍልን በመምራት፤ ካሪኩለም በመቅረፅና በማስተማር አዲስ ለተከፈቱት የትምህርት መርሐ-ግብሮች አገልግሎት ሰጥተዋል።

በዚያው ሥራቸው እያሉም መጋቢት 7 ቀን 2017 ዓ.ም በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

‪@BisratMezmur‬

2 - 0

Bisrat Mezmur Tube-ብስራት መዝሙር
Posted 4 weeks ago

አባባ ባንጫ ያያ :- ወደ አምላካቸውና አባታቸው ሄደዋል

ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሚል ስያሜና "ወልድ ያለዉ ሕይወት አለዉ የሚል የተከፈተ መጵሀፍ እንድሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ገዥ ሀሳብ የሰጠ የወንገል አርበኛ ከዚህ አለም ጣጣ አረፉ።

ዳሞት ጋሌ ወረዳ ሞኮኒሳ ወይጌ ቀበሌ ተወልደው አለምን ዞሮ ያገለገሉ እኚህ ወንገል አርበኛ ከ137 ዓመታቸዉ ቡሃላ ወደ ቀደሙት አባቶችና ወደ ፃድቃን ሄዱ፣በተዘጋጀላቸው አልጋቸዉም ላይ ተኙ።

አባባ ባንጫ ያያ የመጀሪያዉ የኢትዮጵያ ቃለሕይወት ቤተክርስቲያን ዋና ፕረዚዳንት እና በ1954 ዓ.ም ቀዳማዊ ኃ/ስላሴ ሸንጎ በመሰየም የቤተክርስቲያን ስያሜን አስችሎ የተከራከሩ እና በዚህም ምክንያት የታሰሩ ጀግና አባት ናቸዉ።

ወላይታ ወንገልን በ1919 ዓ.ም ስቀበል አባባ ባንጫ የ32 ዓመት ወጣት ናቸዉ። ቀዳሚ አማኝም አገልጋይም ናቸዉ። በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች ህብረት ኦርቶዶክስ ተዋዶ የበላይ ጠባቂ ሆኖ ለሎች በሱ ስር እንድተዳደሩ የወጣዉን አዋጅ በመቃወም የታሰሩ ተመቱና የተንገላቱት እዉቅ አርበኛ ናቸዉ ። ከእሳቸው ቡሃላ የኢትዮጵያ ቃለሕይወት ፕረዚዳንትነት ቦታ ለመምራት እድል አላገኘችም ።

አባባ የወላይታ አዉራጃን መርተዋል ። የጫራቄ ማህበርን ከ40 ዓመታት በላይ በዋና ፀሐፍነት የመሩና በንጣዋ ጃጋሬንና ማርታኒያዋ ሾንጋን እንድሁም ሊሊአዋ ዳልከን ጨምሮ ብዙ አባቶችን የሰበኩና የመዳንን መንገድ ያሳዩ እንድሁም የጠመቁና ደቀመዝሙር ያደረጉ ጀግና አባትም ናቸዉ።

‪@BisratMezmur‬

6 - 0

Bisrat Mezmur Tube-ብስራት መዝሙር
Posted 1 month ago

በዎላይታ ዞን በደረሰ የመኪና አደጋ የ15 ሰዎች ህይወት አለፈ
********************

በዎላይታ ዞን ዳሞት ወይዴ ወረዳ በዴሣ ከተማ በደረሰ የመኪና አደጋ የ15 ሰዎች ህይወት ማለፉ ታውቋል፡፡

አደጋው ከአርባምንጭ ወደ ሻሸመኔ ከተማ ሲጓዝ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ ማምሻውን መድረሱን ፤ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሩ “በዚህ አሰቃቂና እጅግ ልብ ሰባሪ አደጋ ከሟች ወገኖቻችን በተጨማሪ በ27 ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል አደጋ ደርሶ ህክምና እየተደረገላቸዉ ይገኛል” ብለዋል፡፡

በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች ወዳጅ ዘመዶችም ርዕሰ መሥተዳድሩ መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

‪@BisratMezmur‬

4 - 1