🔥🔥🔥WELCOME TO AL- FARUK MULTIMEDIA PRODUCTION🔥🔥🔥
አል ፋሩቅ መልቲሚዲያ ኘሮዳክሽን ቀደምት የሆነ ኢስላማዊ ፊልሞች ትርጉም : መንዙማና ነሺዳ እንዲሁም ዘርፈ ብዙ ኢስላማዊ የኪነጥበብ የስነ ፅሁፍ ስራዎች ከድሮዎቹ የቴኘና የዴክ ካሴቶች ጀምሮ በማዘጋጀት ለህዝብ ያደረሰ አንጋፋ ተቋም ነዉ::
አሁንም በዘመኑ የመገናኛ ብዙሀን ቴክኖሎጂ እርምጃ እኩል በመራመድ በዩቱብ ገፁ የተለያዩ ኢስላማዊ መሰናዶዎችን መንዙማና ነሺዳዎችን ጨምሮ ለህዝብ እያደረሰ ያለ ተቋም ነዉ::
ራዕይ
በኢስላም ኪነ ጥበብ ዘርፍ እስልምናና እሴቶቹን እንዲሁም በሀገራችን ቱባ የሆነዉን ኢስላማዊ ታሪክ በላቀ ጥረት በማዘጋጀትና በተለያዩ ቋንቋዎች ለዐለም በማድረስ ግንባር ቀደም ሆኖ መገኘት !
ስለ ህጋዊነት
አልፋሩቅ መልቲሚዲያ ኘሮዳክሽን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ
በንግድ ፍቃድ ቁጥር AA/AR/01/14/670/886967/2014
በንግድ ምዝገባ ቁጥር AA/AR/01/0003238/2014
እና በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር 0073764307 ተመዝግቦ በንግድ ብሮድካስት አገልግሎት : የበይነ-መረብ መገናኛ ብዙሀን ስራዎች : በሚዲያ መገናኛ ኘሮግራም ማዘጋጀትና ማሰራጨት ስራዎችና በራዲዮና ቴሌቭዥን ኘሮግራም ቀረፃና ስርጭት ስራዎች ላይ ተሰማርቶ በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል::
ዓላማ
በኢስላም ኪነ ጥበብና ቅርስ አጠባበቅ ላይ የጎላ ተሳትፎ በማድረግ አሻራችንን ማሳረፍ !
የእስልምና ሁለንተናዊ ልቀት በየዘርፉና በየሚዲያው በኩል ማስተዋወቅ!
እስልምና ተኮር ጥናትና ምርምሮች እንዲጎለበቱ የበኩላችንን ሚና መወጣት!