Channel Avatar

DW Amharic @UC3-RNH75BEZslJLEoIAxa2A@youtube.com

30K subscribers - no pronouns :c

ስለ ኢትዮጵያ እና መላው ዓለም በየቀኑ ከመሀል አውሮጳ የምናስተላልፈውን የዕለቱን ዋና ዋና ዜና


About

ስለ ኢትዮጵያ እና መላው ዓለም በየቀኑ ከመሀል አውሮጳ የምናስተላልፈውን የዕለቱን ዋና ዋና ዜና ለማድመጥ አለያም ለመመልከት ይከተሉን ። ዶይቸ ቬለ (DW) በዓለም የሚከሰቱ የሰበር ዜና መረጃዎችን ከስር መሰረታቸው በጥልቀት በመፈተሽ ያቀርባል ። ተመልካቾቻችን ጉዳዬ የሚሏቸውን ርእሰ ጉዳዮች ወኪሎቻችን ከቦታው ዝርዝር ትንታኔ በመሥራት ያቀርባሉ ። ዶይቸ ቬለ በ30 ቋንቋዎች የሚያሰራጭ የጀርመን ዓለም አቀፍ ጣቢያ ነው ። በኢትዮጵያ፤ በአፍሪቃ እና መላው ዓለም የሚከሰቱ ማኅበራዊ፤ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ መረጃዎችን የጀርመን እና የሌሎች ምልከታዎችን በማሰናሰል በገለልተኛነት እንዘግባለን ። በአፍሪቃ ቀንድ፦ በኤርትራ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ ጅቡቲ የሚከሰቱ ጉዳዮችን እንዘግባለን ።

ዶይቸቬለ በተለያዩ ሰዎች እና ባሕሎች መካከል ያሉ ልዩነቶች ግንዛቤ እንዲያገኙ አበረታታለሁ ብሎ ተስፋ ያደርጋል ። በጀርመን መንግሥት የገንዘብ ድጋፍ ቢያገኝም የዶይቸ ቬለ ሥራ ቁጥጥር የሚደረግበት በዶይቸ ቬለ ደንብ ነው ። ያ ማለት ዘገባዎቻችን ምንጊዜም ከመንግሥት ጫና ነጻ ናቸው ። እዚህ የምትሰጧቸው አስተያየቶችን እና የምታደርጓቸው ውይይቶች ንጹሕ እና በመከባበር ላይ የተመሠረቱ እንዲሆኑ በትህትና እንጠይቃለን ። ለተጨማሪ መረጃ ከታች የሚገኘውን የዶይቸ ቬለ የሥነ-ምግባር ደንብ (Netiquette) መመልከት ትችላላችሁ ።